Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,881 episodes available.
February 05, 2026የመጭውን ጠቅላላ ምርጫ የፀጥታ ኹኔታ የተመለከው ውይይትብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድባቸውን አካባቢዎችን "የፀጥታ ኹኔታ" በተመለከተ "ከባለድርሻ አካላት ጋር" ሰሞኑን ውይይት አድርጓል።ውስን የመገናኛ ብዙኃን ለመክፈቻው ብቻ ተጠርተው ውይይቱ ላይ ባልተጋበዙበት በዚህ ውይይት ላይ ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ?...more0minPlay
February 05, 2026ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ እና የፀጥታው ተግዳሮትኢትዮጵያ በቀጣይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት መሆኗን በምርጫ አስፈጻሚው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል አሳውቃ እየተንቀሳቀሰች ነው፡፡ በዚህ ላይ አስተያየታቸውን የሚሰጡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫውን ለማድረግ አስቻይ የፀጥታ ሁኔታ የለም በማለት ቅሬታ እያቀረቡ ነው፡፡...more0minPlay
February 05, 2026ብሔራዊ ቋንቋና ገለልተኛ የሕዝብ ቆጠራን ጨምሮ 17 አጀንዳዎች ለምክክር ኮሚሽን ቀረቡበቅርቡ ከመንግሥት ጋር "የሰላም ስምምነት" መፈረሙን የገለፀው "የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት" የተባለዉ ታጣቂ ኃይል አካል የሆነ ቡድን "አማርኛ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን፣ ገለልተኛ የሕዝብ ቆጠራ እንዲከናወን የሚሉትን ጨምሮ 17 አጀንዳዎችን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማስረከቡን ገለፀ።...more0minPlay
February 05, 2026የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ በ9ኛ እና በ11ኛ ክፍል የታሪክ መጽሐፍት ውስጥ የተወሰኑ ምዕራፎችን አገደበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ በ9ኛ እና በ11ኛ ክፍል የታሪክ መጽሐፍት ውስጥ የሚገኙ የተወሰኑ ምዕራፎች ለተማሪዎች እንዳይሰጡ አገደ ፡፡ መምሪያው እገዳውን የጣለው በመማሪያ መጽሀፍት ውስጥ “ የውሸት ታሪኮች” ተጽፈዋል በሚል ነው ፡፡...more0minPlay
February 05, 2026በገዳ ስርዓት ላይ በርካታ ጥናቶችን ያደረጉት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ሲታወሱየኦሮሞ የገዳ ስርዓትን ለግማሽ ምዕተ-ዓመት በማጥናት ለዓለም ያስተዋወቁት ትውልደ ኤርትራዊው ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ህልፈተ ህይወታቸው መሰማቱ በበርካቶች ዘንድ ሀዘን ፈጥሯል፡፡ተመራማሪው የገዳ ስርዓት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ ትምህርት እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ አይነተኛ ሚና መጫወታቸውም ይነገራል።...more0minPlay
February 04, 2026የግል አበዳሪዎች ኢትዮጵያን ሊከሱ እንደሚችሉ ቢገልጹም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአከፋፈል ሽግሽግ ይጠብቃሉጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን ዕዳ ለማሸጋሸግ በሚደረገው ጥረት “በሁለት ዓመት ይከፈል የነበረው ዕዳ እንደየአበዳሪው ሁኔታ እስከ 15 ዓመት እንዲራዘም ሥምምነት” መፈጸሙን ተናግረዋል። የግል አበዳሪዎች ግን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ያደረጉት ሥምምነት ውድቅ ከሆነ በኋላ በእንግሊዝ ፍርድ ቤት ክስ ሊመሠርቱ እንደሚችሉ ገልጸዋል።...more11minPlay
February 04, 2026አማራ ክልል በጦርነት ትምህርት ቤት መዘጋትና በሴቶች ላይ ያለ እድሜ የግዳጅ ጋብቻበአማራ ክልል ትምህርት ቤቶች በጦርነት ምክንያት በተዘጉባቸዉ አካባቢዎች ያለ እድሜ እና የግዳጅ ጋብቻዎች በሴቶች ላይ እንደሚፈፀም ተገለፀ ። በአማራ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ የህፃናት መብትና ደህንነት ማስከበር ዳይሬክተር በበኩሉ ከባለፈዉ ዓመት ጋር ሲነፃፀር 24 ህፃናት ያለ እድሜ ጋብቻ እንደተፈፀመባቸዉ መረጃ እንደደረሰው ገልጧል ።...more4minPlay
February 04, 2026የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ይዞታ እና የአገራት ፍላጎትየቻይና፣ የጀርመን፣ የዩናይትድ ኪንግደም፣ የየዩናይትድ ስቴትስ፣ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች፣ አማን እና ኖርዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አሊያም ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ በላከቡት ባለፈው የጎርጎሪዮሱ አንድ ወር ብቻ ዘርፈብዙ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ስለመደረጋቸው ተወስቷል ።...more5minPlay
February 04, 2026የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ጉባዔ በየትኞቹ ጉዳዮች ላይ መከረ ?«በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የነዳጅ አቅርቦት አለመኖር የልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸምን እያስታጎለ ይገኛል» ሲሉ የክልሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አመለከቱ ። በጉባኤው ሰላምን የማጽናት ፣ የገቢ አሰባሰብ ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት እና በየከተሞች የተካሄዱ የኮሪደር ሥራዎችን በተመለከተም ተነስቷል ።...more5minPlay
February 04, 2026የኤርትራ ጦር ትግራይ ውስጥ ፈጽሟል ስለተባለው ውድመት የተሰጡ አስተያየቶችየኤርትራ ጦር ሠራዊት አክሱም ከተማ ውስጥ ወጣቶችን «መረሸኑን»፣ በሽሬ፣ አድዋ እና አዲግራት ከተማች ደግሞ የንብረት ውድመት ማድረሱን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማክሰኞ ጥር 26 ቀን፣ 2018 ዓ.ም አረጋግጠዋል ። የኤርትራ መንግሥት ቃል ዐቀባይ የማነ ገብረ መስቀል የጠቅላይ ሚኒስትሩን ማብራሪያ «ውሸት» ነው ሲሉ አጣጥለውታል።...more5minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,881 episodes available.