Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,881 episodes available.
February 02, 2026የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስለ ሰሞኑ ኹኔታሰሞኑን የሁለት ክልሎች ይገባኛል ጥያቄ ካለባቸው አካባቢዎች ባንዱ የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት "ከፌዴራል መንግሥት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን" የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ገለፀ። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ ችግሩ የተከሰተው "መሠረታዊ" ያሏቸው የትግራይ ጥያቄዎች ዘላቂ መፍትሔ ባለማግኘታቸው ነው ብለዋል።...more0minPlay
February 01, 2026ውይይት፤ የትራምፕ ሽምግልና ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?እንዴትስ ጥቅሟን ታስከብር?የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የአባይ ውሃ ባለድርሻነት ለዘለቄታው እልባት እንዲያገኝ በሚል፤iኢትዮጵያ እና ግብፅጽን ዳግም ወደ ድርድር ለማምጣት ሀገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን ደጋግመው ገልፀዋል.።ያም ሆኖ ትራምፕ በተለያዩ ጊዜዎች የሚሰጧቸው ወደ ግብፅ ያዘነበሉ አስተያየቶች የገለልተኝነት እና የፍትሃዊነት ጥያቄ ማስነሳቱ አልቀረም።...more45minPlay
February 01, 2026የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ በትግራይ ክልል “ወደ ሰፊ ግጭት የመመለስ ሥጋት” እንዳሳሰባቸው ገለጹበኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት “በሲቪሎች ላይ ሊደርስ የሚችል ተጽዕኖ እና ወደ ሰፊ ግጭት የመመለስ ሥጋት” እንደሚያሳስባቸው የተመ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገልጸዋል። ብሪታኒያ ዜጎቿ ወደ ትግራይ እንዳይጓዙ ስትመክር የአውሮፓ ኅብረት ውጥረቱን በአፋጣኝ ማርገብ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።...more0minPlay
January 31, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ ክልል ያቋረጠውን በረራ ተከትሎ የተፈጠረው ስጋትየኢትዮጵያ አየርመንገድ መቀሌን ጨምሮ ወደ ትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚያደርገውን በረራ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ዛሬም ድረስ ተቋርጦ መቀጠሉን ተከትሎ በክልሉ ነዋሪዎች ላይ ስጋቱ አይሏል፡፡...more4minPlay
January 31, 2026በሦስት ክልሎች አዋሳኞች መብቶችን ሥጋት ላይ የሚጥሉ ኹኔታዎች ተፈጥረዋል - ኢሰመኮየኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች አንዳንድ "አዋሳኝ" ያላቸው አካባቢዎች ግጭትና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ገለፀ።...more4minPlay
January 31, 2026የፕላስቲክ ከረጢትን መጠቀም የሚከለክለው ሕግ ገቢራዊ መሆን ጀመረከዛሬ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በፕላስቲክ ከረጢት እቃ መያዝም ሆነ መሸጥን የሚከለክለው ሕግ ገቢራዊ መሆን መጀመሩን ተክተሎ ለቅጣት ይዳርጋል። አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ ተዘዋውረን በተመለከትናቸው ትልልቅ መገበያያ ሱቆች ውስጥ በተለምዶ ፌስታል የሚባለው የፕላስቲክ ከረጢት ከፕላስቲክ ውጪ በተሰሩ ከረጢቶች ተተክተው ታይተዋል፡፡...more3minPlay
January 31, 2026በአማጺው M23 ስር ያለችው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎዋ ከተማ ጎማ ከአንድ ዓመት በኋላከአንድ ዓመት በኋላ፣ ጎማ ለጦርነት ክፍት የሆነች ከተማ አይደለችም። የጸጥታ ሁኔታ ተሻሽሏል። ገበያዎች እንደገና ተከፍተዋል፣ትምህርት ቤቶችም ተከፍተዋል። ሆኖም የኢኮኖሚ ሁኔታው አሁንም አስቸጋሪ ነው። ከተማዋ አሁንም በአማፂያን ቁጥጥር ስር ነች። ከሁሉም በላይ፣ ስነልቦናዊ መዘዞች በስፋት አሉ። ጭንቀት የብዙዎች የዕለት ተዕለት እውነታ ነው።...more11minPlay
January 30, 2026በኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮች እና በትግራይ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ውጥረት ወዴት እያመራ ነው?በኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት ወታደሮች እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ተፈጠረ የተባለው ግጭት ከመቐለ እስከ አላማጣ በነዋሪዎች ዘንድ ሥጋት ፈጥሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በውጥረቱ ምክንያት በረራዎች እንደሰረዘ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል። እስካሁን ከፌድራል መንግሥት፣ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወይም ከህወሓት በኩል በይፋ የተሰጠ መግለጫ የለም።...more0minPlay
January 30, 2026ከአላማጣ ነዋሪዎች ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ሥጋት እየሸሹ መሆኑን ገለጹከአላማጣ ነዋሪዎች ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ሥጋት ወደ ሌሎች ከተሞች መሸሽ መጀመራቸውን ገለጹ። ነዋሪዎች ከከተማዋ መሸሽ የጀመሩት በመከላከያ ሠራዊት እና ፌድራል ፖሊስ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ለቆ ከወጣ በኋላ እንደሆነ ተናግረዋል።...more0minPlay
January 30, 2026በትግራይ እና አማራ አዋሳኞች ያለው ውጥረት እንዲረግብ የቀረቡ ጥሪዎችበትግራይ እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ሰሞኑን እየተስተዋለ ያለው ውጥረት እንዲረግብ ከልዩ ልዩ አካላት ጥሪዎች እየቀረቡ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ባወጣው መግለጫ የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ የሱፍ ኹኔታዎችን በቅርበት እየተከታተሉ ሲሆን የተፈጠረው ውጥረት እንዳሳሰባቸው ገልጿል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,881 episodes available.