Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,881 episodes available.
February 03, 2026በኦሮሚያው ግጭት ለደረሰው ሰብአዊ ጉዳት እና የኦነሰ አዛዥ ምልከታ እና አንድምታውበኦሮሚያ ክልል ውስጥ በግጭት ውስጥ በሚፈጸመው የሰላማዊ ዜጎች ጥቃትና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ እንደማይሳተፉ የአማጺው ኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ-አነሰ) አዛዥ ተናገሩ፡፡ አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ የዓለማቀፍ ሕግ ባለሙያ ግን በኢትዮጵያ በየክልሎቹ ባሉ ግጭቶች እና ለደረሰው ጥፋት ከተጠያቂነት ነጻ ሊሆኑ እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡...more0minPlay
February 03, 2026ግጭት ሸሽተው በቆቦ የሰፈሩ ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉየኮረም፣ ወፍላ፣ ዛታና የራያ የማንነት ጥያቄ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት እንዲፈታልን እንጠይቃለን ሲሉ በሰሞኑ የህወሀት እንቅስቃሴ ከአካባቢያቸዉ የተፈናቀሉ በቆቦ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ አካሄዱ ሰልፈኞቹ ጦርነትና ስደት ብዙ ነገር አሳጥቶናል ባለፉት ስድስት አመታትም ለአራተኛ ጊዜ ተፈናቅለናል ብለዋል...more0minPlay
February 03, 2026የኔዘርላንድስ ፍርድቤት አማኑኤል ዋሊድ በመባል የሚታውቀውና ስሙ ግን ተወልደ ጎይቶም እንደሆነ በተገለጸው በኤርትራዊው የሰው አዘዋዋሪ ወንጀለኛ ላይ የ20 አመት የእስር ብይን አስተላለፈዋና ዳኛ ሬኔ ሜላርድ ተክሳሹና ግብረ አበሮቹ በስደተኖች ላይ የፈጸሟቸው ወንጀሎች ጭካኔ የተሞላባቸው መሆኑ ወንጀሉን ልዩ የሚያደረገው መሆኑን፤ ወደ ተከሳሹ በማመላክትም “አንተና ግብረአበሮችህ ገንዘብ ለማገኘት ሁሉንም የጭካኔ አይነት በስደተኖች ላይ ፈጽማችኋል” ማለታቸውን የተለያዩ ጋዜጦች ዘግበዋል።...more0minPlay
February 03, 2026በኢትዮጵያ አየርመንገድ ወደ ትግራይ መልሶ በረራ መጀመር የተፈጠረው መረጋጋትከአምስት ቀናት ገደማ የበረረራ መቋረጥ በኋላ ዛሬ ጠዋት ብቻ ሁለት በረራዎች ከአዲስ አበባ መቀሌ እና ከመቀሌ አዲስ አበባ መደረጉን የአይን እማኞች እና የበረራው ተጠቃሚዎች ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል፡፡...more0minPlay
February 03, 2026የኢትዮጵያና ኤርትራ ፀብ የተፋፋመው የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈረም ነው ፤ ጠ/ሚ ዐቢይዐቢይ በሁለቱ ሀገራት መካከል "ፀብ" የተጀመረው ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር በር የማግኘት ጉዳይ ሲመጣ ሳይሆን በሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ጦር ሠራዊት ትግራይ ክልል ውስጥ "የአንዳንድ ግለሰቦችን ቤት ማፍረስ ሲጀምር፣ ወጣቶችን በጅምላ ሲረሽን፣ ፋብሪካዎችን ሲፈታ፣ ሲሰርቅ እና ሲያፈራርስ" እንደሆነ ገልፀዋል።...more0minPlay
February 02, 2026ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ፍጥጫ፣ ዲፕሎማሲ ወይስ ዉጊያትራምፕ ራሳቸዉ ባለፈዉ ሰኔ የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል ተባባሪ ጦር ኃይል የኢራንን የኑክሌር መርሐ-ግብር ሙሉ በሙሉ አዉድመዋል ብለዋል።ትራምፕ አሁን ኢራንን ዳግም ለመዉጋት የኑክሌሩን ጉዳይ ብቻ ሰበብ ቢያደርጉ ከባለፈዉ የድል ብሥራት ቀርርቷቸዉ ጋር ሊቃረን ነዉ።ፕሮፌሰር ጄርጂስ እንደሚሉት ነጋዴዉ፣ ቀኝ ፅንፈኛ ፖለቲከኛ ሌላ ሰበብ መዘዙ።...more14minPlay
February 02, 2026የጥር 25 ቀን 2018 ዓም የስፖርት ዝግጅትበወንዶች የመጀመሪያው የማራቶን ውድድሩን ንብረት መላኩ በ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ በመጨረስ በአንደኝነት አጠናቋል። ያሲን ሀጂ በ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ ሁለተኛ ሆኗል። በዚሁ ውድድር 3ተኛ ከወጣው ከሩዋንዳው አትሌት በስተቀር ከ1 እስከ 10 ያለውን ደረጃ ያገኙት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ናቸው።...more0minPlay
February 02, 2026«ሕገ-ወጥ እስር እና እንግልት በአስቸኳይ ይቁም» ኢዜማየኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአባላቶቼ ላይ ይፈጸማል ያለው “ሕገ-ወጥ እስር እና እንግልት” በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ፡፡ “ በተለያዩ ክልሎች በፓርቲው አባላት ላይ የሚፈጸመው እሥርና እንግልት ተባብሶ ቀጥሏል “ ሲል ፓርቲው ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ ዐሳውቋል ፡፡...more0minPlay
February 02, 2026በቆቦ ከተማ የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር እና የሰብአዊ ድጋፍ መዘግየትጦርነትን በመሸሽ ከአላማጣ ከተማ፣ ራያ ባላ፣ እራያ አላማጣ፣ ኮረምና፣ ዛታ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ60 ሺህ በላይ መሆኑ ተነገረ ። ተፈናቃዮቹ በአብዛኛዉ በቆቦ ከተማ ከማኅበረሰቡ ጋር የተጠለሉ ሲሆን ባለፉት አምስት ቀናት ምንም አይነት ሰብአዊ ድጋፍ አልቀረበልንም ይላሉ ።...more0minPlay
February 02, 2026የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ስለሙስና ያስተላለፉት መልእክት አንድምታየኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከሙስና ጋር ተያይዞ ያሰሙት ንግግር በብዙ ብደነቅም በርካቶችን አወዛግቧል ። ርዕሰ መስተዳድሩ አደረጉት የተባለው ንግግር በተንቀሳቃሽ ምስል ተቆርጦ በርካቶች በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ተቀባብለውታል ።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,881 episodes available.