Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,886 episodes available.
January 27, 2026የበረዶ ውሽንፍርና ቀዝቃዛው የሰሜኑ ንፍቀክበብ የክረምት ይዞታዓለማችን ፅንፍ የወረገጡ የአየር ጠባይ ሁኔታዎችን ማስተናገድ ከጀመረች ሰነበተች። በበጋው ወቅት በኃይለኛ ሙቀት የሚጨነቁት በርካቶቹ ሃገራት በአሁኑ የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ የክረምት ወራት ደግሞ ከፍተኛ ቅዝቃዜን እያስተናገዱ ነው።...more0minPlay
January 27, 2026የብሔራዊ ባንክ አዲስ መመሪያ በንግድ ሥርዓት ማሻሻያ እና በዋጋ ንረት ስጋት መካከልየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኢትዮጵያ አሁን እየተተገበር ባለው የንግድ ሥርዓት ላይ ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል የተባለለትን አዲስ መመሪያ አውጥቶዋል ። በብሔራዊ ባንክ የቅርቡ አስገዳጅ ውሳኔ መሰረት፦ ባንኮች ከውጭ ወደ ሀገር ወስጥ ለሚገቡ የተመረጡ ምርቶች የውጭ ምንዛሪ ሲፈቅዱ አስመጭዎች በሚያቀርቡት የክፍያ ሰነድ ላይ ተመስረተው አይደለም።...more0minPlay
January 27, 2026ናዚ የፈፀመው የሆሎኮስት እልቂት መታሰቢያ በአዲስ አበባጀርመን በናዚ በተመራበት ወቅት 6 ሚሊዮን አይሁዶች በጅምላ የተገደሉበት የሆሎኮስት እልቂት ዛሬ ማክሰኞ በአዲስ አበባ ታሰበ ። በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪቃ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አፍሪቃ አዳራሽ ውስጥ በተከናወነው የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት "ጀርመን ለሆሎኮስት ያላትን የማይለወጥ እና ዘላለማዊ ኃላፊነት ተቀብላለች" የሚለው መልዕክት ጎልቶ ተሰምቷል ።...more0minPlay
January 27, 2026የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አቅርቦት እና የሚነሱበት ጥያቄዎችየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ ዓመት በቤቶች ልማት አቅርቦት ላይ አተኩሮ እየሠራ እንደሆነ አመልክቷል ። ነዋሪዎች እና የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች እንደሚሉት ግን አሁን አሁን በከተማዋ እየተስተዋሉ የሚገኙት የቤት ልማት አቅርቦቶች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን በርካታውን ማኅበረሰብ የሚያቅፉ አይደሉም ።...more0minPlay
January 27, 2026ብርቱ የበረዶ ወጀብ በአሜሪካ ያደረሰው የሕይወትና ንብረት ጥፋትበአሜሪካ በተከሰተው ብርቱ የበረዶ ወጀብ እና ቅዝቃዜ በትንሹ 21 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ ። በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትንና የታቀዱ በረራዎችን ያስተጓጎለው በረዷማውና ቀዝቃዛው የአየር ሁኔታ፣ እስከ ያዝነው ሳምንት ድረስ ሊዘልቅ ይችላል የሚል ትንበያ አለ ።...more0minPlay
January 26, 2026ማሕደረ ዜና፣አንድ ዓመት ከትራምፕ «አሜሪካ ትቅደም» መርሕ ጋርዋይት ሐዉስ ላወጣዉ ዘገባ በ365 ቀናት 365 ድሎች የሚል ርዕሥ ሰጥቶታል።ከ365ቱ ድሎች ቀዳሚዉ የአሜሪካ የምጣኔ ሐብት ዕድገት አይደለም።ትራምፕ ሥደተኞችን ለማባረር ያወጁት ደንብ ገቢራዊነት እንጂ።በዘገባዉ መሠረት ባለፈዉ አንድ ዓመት «ሕገ ወጥ» የተባሉ 2.6 ሚሊዮን ሥደተኞች አንድም ተይዘዉ ሁለትም መታሰርን ፈርተዉ ከአሜሪካ ተባርረዋል።...more0minPlay
January 26, 2026የጥር 18 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባማንቸስተር ዩናይትድ ከስምንት ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መድፈኞቹን በገዛ ሜዳቸው ድል ማድረግ ተሳክቶለታል ። ሊቨርፑል በበርመስ ሽንፈት ቀምሷል ። ቸልሲ ዳግም ድል ቀንቶታል ። መሪው ባዬርን ሙይንሽን ሽንፈት ሲያስተናግድ፤ ላይፕትሲሽ በስምንት ደቂቃዎች ሦስት ግቦችን አከታትሎ ከመረብ በማሳረፍ የማጥቃት ብቃቱን ዐሳይቷል ።...more10minPlay
January 26, 2026ምርጫ እና የመገናኛ ብዙኃን ያሉበት ወቅታዊ ኹኔታ«ሚዲያ የሌለበት ምርጫ ምርጫ ሊባል አይችልም»የሚለው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ በፍቃዱ ኃይሉ በኢትዮጵያም ይሁን በሌላ ቦታ «ከምርጫ ጋር በተያያዘ መገናኛ ብዙኃንን የማዋከብ ሥራ የተለመደ የሆነው ለዚህ ነው» ይላል።...more4minPlay
January 26, 2026የፖለቲካ ምኅዳር እያጨለሙ ያሉ ችግሮች ገጥመውናል" - 8 ፓርቲዎችፓርቲዎቹ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ያለፓርቲው ዕውቅና በየ ዕጃቸው ባለው ስልክ ገብተው ራሳቸውን ከዕጩነት እንዲሠርዙ እንዲያደርጉ የሚያስችል አማራጭ መሰጠቱ "ገዢው ፓርቲና ካድሬዎቹ በሀብትና ጥቅማ ጥቅም ወይም በሥልጣን፣ በእሥራት፣በነፍስ በማስፈራራት እንዲያስለቅቋቸው በማመቻቸት ሆን ተብሎ የገባና የተናበበየ ፖለቲካ ሴራ" ነው ብለዋል...more4minPlay
January 26, 2026የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያና የባለሙያ አስተያየትመንግስታቸው በአየር ኃይል አቅም ማሳደግ ላይ አተኩሮ የሚሰራበትም ዋናው ምክንያት መስዋእትነትን ለመቀነስ ወሳኝ በመሆኑ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ኢትዮጵያ ከወዳጆቿ ጋር ለመስራት በሮቿን አብዝታ እንደምትከፍት ጠቁመዋል።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,886 episodes available.