Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,886 episodes available.
January 21, 2026የዲጅታል ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በተከታዮቻቸው ላይ ያላቸው አወንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖየቲክቶክ፣ ዩቲዩብ እና ኢንስታግራም እና የፌስቡክ ዘመን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ከተዋናዮች፣ ስፖርተኞች ወይም ከፖለቲካ መሪዎች - በተለይም በወጣቶች ዘንድ የበለጠ ተፅዕኖ እየፈጠሩ ነው። ነገር ግን የሚያቀርቧቸው ይዘቶች ጠቃሚ እና በሳል ዕይታ እና አስተሳሰብ የታከለበት ካልሆነ፣ተፅዕኗቸው በሚከተሏቸው ወጣቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።...more0minPlay
January 21, 2026የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ጉብኝትየዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ዋና ዳይሬክተር ፒየር ክሬሄንቡህል እና የጀርመን ቀይ መስቀል ዋና ጸሐፊ ክርስቲያን ሮይተር በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ላይ ናቸው። በመጭው ዓርብ ጉብኝታቸውን አጠናቀው እንደሚመለሱ ከድርጅቱ የኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።...more4minPlay
January 21, 2026ትራምፕ የገነኑበት የዳቮሱ የኤኮኖሚ ጉባኤባለፈው እሁድ ተጀምሮ የፊታችን አርብ የሚያበቃው የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ ካተኮረባቸው ቁልፍ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በአመዛኙ በሥራ ላይ በዋሉት ዓለም አቀፍ ሕጎች ላይ የሰነዘሩት ጥቃትና ይህም በዓለም አቀፍ ሰላም፣ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ይገኝበታል።...more4minPlay
January 21, 2026የድህረ ምርት ብክነትና በምግብ ዋስትና ላይ ያለው ተፅዕኖየግብርና ሚኒስቴር በድህረ ምርት የአያያዝ ጉድለት ምክንያት ከሚመረተው ሰብል ከ20 እስከ 30 %፤ አበባን ጨምሮ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው አትክልትና ፍራፍሬዎች ከ30 እስከ 50 %፤ በእንስሳት ምርት እስከ 40 % ብክነት እንዳለ አመላክቷል።...more11minPlay
January 21, 2026በጉጂ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሰዎች ሕይወት አለፈበኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሰባ-ቦሩ ወረዳ ታጣቂዎች በአንድ ምግብ ቤት ደርሰው በከፈቱት ጥቃት የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አምስት ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል። ጉዳቱ የደረሰው ጥር 10 ቀን እሑድ ከምሽቱ 3 ሰዓት ግድም ታጣቂዎች በወረዳው ሳቢቹ ቂንጣቢ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኤላ-ዲማ በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ ገብተው በከፈቱት የእሩምታ ተኩስ ነው።...more4minPlay
January 21, 2026የኔቶ አባል ሃገራትን ያወዛገበው የትራምፕ የግሪንላንድ እቅድበትራምፕ የግሪንላንድ እቅድ ምክንያት በምዕራባውያን ሃገራት መካከል የተከሰተው ቀውስ ማቀዛገቡን ቀጥሏል። ውዝግቡም በያዝነው ሳምንት ዳቮስ ስዊዘርላንድ በሚካሄደው የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ ላይ አሉታዊ ጥላውን ማሳረፉን ዘገባዎች ያመለክታሉ።...more5minPlay
January 21, 2026ከወለጋ ተፈናቅለው አማራ ክልል በመጠለያ የሚገኙ ወገኖች ጥያቄከኦሮምያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋና አካባቢው ተፈናቅለው ያለፉትን ስድስት ዓመታት በአማራ ክልል የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች የሚኖሩ ወገኖች ወደ ሆሮጉድሩና ጃርቲ ወረዳ ይመለሱ ሲሉ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ጠየቁ።...more4minPlay
January 20, 2026የደን መራቆት ለመቀልበስ የማኅበረሰብ መሪዎች አዎንታዊ ሚናየደን መመናመን እና የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች ያሳደሩት ጫና በርካታ የአፍሪቃ ሃገራትን እየጎዳ መሆኑ ይታያል። ጋና ታዲያ ማኅበረሰባዊ እሴትን የገጠማትን የደን መራቆት ለመቀልበስ ጥቅም ላይ አውላ አዎንታዊ ውጤት ማየት ጀምራለች።...more0minPlay
January 20, 2026አውሮጳንና አሜሪካን የሚያወዛግበው የትራምፕ ግሪንላንድን የመጠቅለል ፍላጎትከዩናይትድ ስቴትስ በሺህዎች ኪሎ ሜትር የምትርቀው በኮፕንሀገን ስr ያለችው ግሪንላንድ፣ ጂኦፖለቲካዊ አቀማመጥ የኃያላኑ ትኩረት ማዕከል አድርጓታል። ግሪንላንድ በዩናይትድ ስቴትስ ቁጥጥር ስር መሆን የለባትም መባሉን ተቀባይነት የለውም የሚሉት ትራምፕ በርሳቸው እቅድ ያልተስማሙትን ሀገራት በታሪፍ ጭማሪ ማስፈራራታቸውን ገፍተውበታል።...more0minPlay
January 20, 2026ግሪንላንድ - ትራምፕ እና የአዉሮጳ ህብረት መልስየአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን ህብረቱ ግሪንላንድ ውስጥ “ግዙፍ” መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ማቀዱን ተናገሩ። ኮሚሽነርዋ ይህን የተናገሩት ዶናልድ ትራምፕ የአርክቲክ ውቅያኖስ ደህንነትን ለማስጠበቅ እና የዴንማርክ ከፊል ራስ ገዝ ግዛት የሆነችዉን ግሪንላንድን ለመጠቅለል ዛቻ እያደረሱ ባለበት በአሁኑ ወቅት ነዉ።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,886 episodes available.