Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,886 episodes available.
January 18, 2026ዉይይት፣ የትራምፕ አስተዳደር ርምጃ፣ የዓለም ሕግና ሥርዓት እንዴትነትየትራምፕ መስተዳድር የቬኑሱዌላን መሪ ማገት ብቻ ሳይሆን የነዳጅ ሐብቷንም ተቆጣጥሯል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ማዱሮን ከማሳገታቸዉ በፊት የየመን ሁቲዎችን፣ የሶማሊያ፣ የኢራቅ፣ የሶሪያና የናጄሪያ ሸማቂዎችን አጠፋለሁ በሚል ሐገራቱን በተደጋጋሚ ደብድበዋል።እስራኤልን አግዘዉ ኢራንን ደብድበዋልም።...more0minPlay
January 18, 2026የከተራ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነውበኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የከተራ በዓልን በድምቀት እያከበሩ ነው። በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው ወደ ጥምቀተ ባህሩ እየተጓዙ መሆኑን ከተለያዩ ከተሞች ያገኘናቸው መረጃዎች ያመለክታሉ ።...more0minPlay
January 17, 2026የሱዳን ስደተኞች ብርቱ ሥጋት ተጋርጦባቸዋል፦ ተመድበርስ በርስ ጦርነት በምትታመሰው ሱዳን አፋጣኝ የምግብ ርዳታ ባፋጣኝ ካልቀረበ ክምችቱ የፊታችን መጋቢት ወር ማገባደጃ ላይ ሊሟጠጥ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አድርጓል የተመድ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ፎልከር ቱይርክ ሱዳን ውስጥ ከ50 በላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አወያይተዋል ።...more3minPlay
January 17, 2026የዩጋንዳ ምርጫ ወዴት?ከ40 ዓመታት በላይ ሐገሪቱን ያስተዳደሩት የ81 አመቱ የኡጋንዳ ፕረዚደንት ዩዌሪ ሙሰቨኒ ሐሙስ ዕለት በተካሄደም ምርጫ ማሸነፋቸውን የሐገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ይፋ አደረጓል። ዩጋንዳ ውስጥ ሐሙስ በተከናወነው አገር አቀፍ ምርጫ ከ81 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ሰባት እጩዎች ተፎካክረው ነበር ።...more7minPlay
January 17, 2026በምርጫ ቦርድ እውቅናው የተሰረዘው ሕወሓት፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ያወጡትን መግለጫ ነቀፈበኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ሑመራ ከተማን ከጎበኙ በኋላ ያወጡት መግለጫ፤ በፕሪቶሪያ ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ፈራሚዎች መካከል አለ ያለውን "ሰፊ ክፍተት ከማጥበብ ይልቅ የሚጎዳ ሂደትን የበለጠ ሊያባብስ እንደሚችል" ሕወሓት ባወጣው መግለጫ ገለልጿል።...more4minPlay
January 17, 2026“ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከቀዳሚ አጀንዳዎቼ አንዱ ነው” ዶናልድ ትራምፕየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአባይ ውሃ ባለድርሻነት ለዘለቄታው እልባት እንዲያገኝ በሚል፤ ግብጸጽ እና ኢትዮጵያን ዳግም ወደ ድርድር ለስገባት አገራቸው አሜሪካ ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቁ፡፡ትራምፕ ይህንን ያሉት ለግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱፈታ አልሲሲ ብለው ትሩዝ ሶሻል በሚባለው የማህበራዊ መገናኛ ዘዲያቸው ላይ ባጋሩት ደብዳቤ ነው።...more5minPlay
January 17, 2026የ81 ዓመቱ የኡጋንዳ ፕረዚደንት ዩዌሪ ሙሰቨኒ በዘንድሮው ምርጫ ማሸነፋቸውን ይፋ ተደረገከ40 ዓመታት በላይ ሐገሪቱን ያስተዳደሩት የ81 አመቱ የኡጋንዳ ፕረዚደንት ዩዌሪ ሙሰቨኒ ሐሙስ ዕለት በተካሄደም ምርጫ ማሸነፋቸውን የሐገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ይፋ አደረገ። ሙሰቬኔ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያሸነፉት 71.65 በመቶ የመራጩ ድምጽ በማግኘት ሲሆን ቀንደኛ ተቀናቃናቸው ቦቢ ዋይን ደግሞ 24.72 በመቶ አግኝተዋል ነው የተባለው።...more0minPlay
January 16, 2026ተወዳጁ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየበሀገርፍቅር ትያትር «ፍሬሽ ማን» በተሰኘው የመድረክ ሰራው ከህዝብ ጋር የተዋወቀው ሁለገቡ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ፣ ኤፍቢ አይ አንድ እና ሁለት ፣ሲቲ ቦይስ፣ሳልነግራት፣ ያንቺው ሌባ ሚስተር ኤክስ፣ ቾምቤ እና ሌሎችም በተመልካች ዘንድ የማይዘነጉ የመድረክ እና የፊልም ስራዎች ይታወሳል።...more7minPlay
January 16, 2026ስኮላርሺፕ በጀርመን፥ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በዶይቸ ቬለ አካዳሚዶይቸ ቬለ አካዳሚ ውስጥ በአሁኑ ወቅት የድኅረ ምረቃ ትምህርታቸውን ከሚከታተሉ ኢትዮጵያውን ወጣቶች መካከል አንዱን ለዛሬ የወጣቶች ዓለም እንግዳችን አድርገናል ። እስካሁን በአካዳሚው ስላገኘው ትምህርት፣ ወደፊት ምን እንዳቀደ እና ስኮላርሺፑን እንዴት እንዳገኘ ያዋየናል ። ሙሉ ዘገባውን ታች ባለው ማገናኛ በድምፅ ያድምጡ ።...more0minPlay
January 16, 2026በትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ በ7 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋልበወረዳው የሰደዋሬ ቀበሌ ነዋሪዎች ሁለቱን ወጣቶች ደግሰው ከዳሯቸው ገና ሳምንት አልሞላቸውም ፡፡ የሚያውቋቸው እንደሚሉት ሙሹሮቹ ከሀዋሳ ወደ በንሳ በሚወስደው አውራ ጎዳና ዳርቻ ላይ በምትገኝ የሳር ጎጆ ውስጥ የጫጉላ ጊዚያቸውን በማጣጣም ላይ ነበሩ ፡፡...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,886 episodes available.