Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,881 episodes available.
January 15, 2026የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት ፍጥጫየኢትዮጵያ ፌድራል ፖሊስ የኤርትራ መንግሥት በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች የላከው “ከ56 ሺህ በላይ የተለያዩ የጦር መሣሪያ ጥይቶችን” በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ አስታውቋል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገራቸው ቴሌቭዥን ጣቢያ የተናገሯቸው ጉዳዮችና ፌድራል ፖሊስ ያወጣው መግለጫ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ነው።...more4minPlay
January 15, 2026በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ስምንት ፓርቲዎች ሀገራዊ ምክክር በክልሉ እንዲካሄድ ለማገዝ ተስማሙበትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ስምንት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ሀገራዊ ምክክር እንዲከናወን የሚያግዝ ጥምረት መመስረታቸውን ገለፁ። ፓርቲዎቹ ይህንን ስምምነታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማስገባታቸውንም ከተጣማሪዎች አንዱ የሆነው ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ለዶቼ ቬለ አረጋግጧል።...more5minPlay
January 14, 2026ያወዛገበው የአባገዳዎች ሽምግልና ሂደትበሰላሌ ማህበረሰብ ላይ ስድብ ሰንዝሯል በተባለ አንድ ፓስተር እና በአካባቢው በማህበረሰብ መሪዎች መካከል ውዝግብ ተፈጥሮ ቆይቷል።ጉዳዩን በሽምግልና ለመፍታት የሞከሩ አባገዳዎችም ጉዳዩ በባህላዊ ሽምግልና ሊፈታ ይችላል ወይስ ወደ ፍርድ ቤት ሊወሰድ ይገባል በሚል የሽምግልና ሂደቱ አወዛጋቢ ሆኗል።...more5minPlay
January 14, 2026በኢራን የቀጠለው ህዝብዝዊ ተቃውሞ የፈጠረው የፖለቲካ ውዝግብየአውሮፓ ህብረትም ሆነ አሜሪካ ኢራን በተቃዋሚዎቹ ላይ የምታደርገውን ከባድ ጥቃት ከቀጠለች የተለያዩ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ እያስጠነቀቁ ነው። የአውሮፓ ህብረት ተጨማሪ የማዕቀብ እርምጃዎችን ለመውሰድ እያሰበች ሲሆን አሜሪካ ደግሞ ወታደራዊ እርምጃዎችን እንደምትወስድ ገልፃለች። ነገር ግን አንዳንዶች የአሜሪካ ጣልቃ እንዳትገባ እያስጠነቀቁ ነው።...more4minPlay
January 14, 2026በኤርትራው ፕረዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሰሞኑ ቃለምልልስ ላይ የተሰጡ አስተያየቶችየኤርትራው ፕረዚደንት ኢሳይያስ አፍወርቂ በሀገራቸው የቴሌቪዥን ጣቢያ በተላለፈ የሰሞኑ ንግግራቸው፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገር ውስጥ ከሚያደርገው ጦርነት ባሻገር በኤርትራም የጦርነት ዝግጅቶች እየተደረገባት ነው ሲሉ ከሰዋል። የተቃዋሚው የቀይ ባህር አፋር ድርጅት አመራር ግን የፕሬዚዳንትንት ኢሳያስን ንግግር አጣጥለውታል።...more5minPlay
January 14, 2026የሶማሊያ ካቢኔ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር የተደረጉ ስምምነቶችን እና ትብብርን በሙሉ አግዷልሶማሊያ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር የነበራትን ስምምነትና ትብብር በሙሉ ማቋረጧን አስታውቃለች።የሶማሊያ መንግሥት እርምጃዉን የወሰደዉ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚደገፈው የደቡብ የመን ተገንጣይ ቡድን መሪ አይደሩስ አል ዙባይዲን ያለ ሶማሊያ መንግሥት ፈቃድ በሞቃዲሾ በኩል ወደ አቡዳቢ መውሰዷ ከተሰማ በኋላ ነዉ።...more5minPlay
January 14, 2026የኦንላይን ግብይት ስጋቶች እና የጥንቃቄ እርምጃዎችማሽን ሰዎችን ተክቶ እንዲሰራ የሚያደርገው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በዲጅታል መንገድ ግብይቶችን ለመፈፀም አገልግሎት ላይ ይውላል። ቴክኖሎጂው የኦንላይን ግብይቶችን ምቹ እና በግለሰቦች ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ አቅርቦቶችን ለማግኘት የሚያግዝ ቢሆንም፤ የግል መረጃ ደህንነት፣ ማጭበርበር ፣ የቁጥጥር ወይም የግልጽነት ችግር ስጋቶች ናቸው።...more13minPlay
January 14, 2026ከኤኮኖሚዉ ዓለም፣ የግዙፉ አዉሮፕላን ማረፊያ ግንባታና ፈተናዎቹየኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደሚሉት በ3 ሺህ 900 ሄክታር ቦታ ላይ የሚያርፈው አዲሱ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ በሙሉ አቅሙ ሲጠናቀቅ 110 ሚሊየን ደንበኞችን በዓመት የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል...more12minPlay
January 13, 2026የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ንግግርየኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከአገራቸው ብሔራዊ የቴሌቪዝን ጣቢያ ጋር ያደረጉት ቆይታ በሚል ትናንት ይፋ በተደረገው የምስልና ድምፅ ማብራሪያ ከዓለም አቀፍ ጉዳዮች አንስቶ ስለ ቀጠናዊ ብሎም ስለኢትዮጵያ ጉዳይም ተናግረዋል ። ፕሬዚደንቱ ማብራሪያ የሰጡት የዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ ጉዳዮችን በማስቀደም ነበር ።...more0minPlay
January 13, 2026የፖለቲካ ድርጅቶች ቁጥርና ሀገር የሚገባው የፖለቲካ ምኅዳር7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ ዕቅድ ተይዟል። ሀገራዊ እና ክልላዊ የፖለቲካ ድርጅቶች በአሁኑ ወቅትም ሆነ ቀደም ብሎ እየተቋቋሙ ነው። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የምትከተለው የአብላጫ ድምፅ የምርጫ ሥርዓት ለብዙ መራጮች ድምፅ መባከን ምክንያት ሆኗል በሚል ፓርቲዎች ቅንጅት እና ጥምረት ሲመሰርቱ እየተስተዋለ ነው...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,881 episodes available.