Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,886 episodes available.
January 03, 2026የነዳጅ አቅርቦት ችግሩና የአሽከርካሪዎች እንግልቱ እንዴት ይፈታ?ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የነዳጅ አቅርቦት ላይ በየማደያዎቹ በሚፈጠር ችግር ከፍተኛ መጨናቅ እየታየ ነው፡፡ አሽከርካሪዎች እና የተሸከርካሪ ባለንብረቶች የነዳጅ መሸጫ ማደያዎች ላይ በየጊዜው የሚፈጠረው ማስተጓጎሎች ተጨማሪ የዋጋ ክለሳን በመጠበቅ የሚፈጠር ነው ይላሉ፡፡...more5minPlay
January 03, 2026የእስራኤል የሶማሊያ ላንድ አገርነት እውቅና የፈጠረው ውዝግብ እና የጊኒ ምርጫባለፈው ሳምንት አርብ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር ቢንጃሚን ናትናያሁ ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ከሶማሊያ ተነጥላ እራሷን ነጻ አገር በማወጅ ዕውቅና ስትሻ የቆየችውን፤ ግን በማንም ጥያቄዋ ተቀባይነት አግንቶ የማያውቀውን ሶማሊያ ላንድን እስራኤል ዕውቅና የሰጠችና በነጻ- ሉላዊ አገርነት የተቀበለቻት መሆኑን ማሳወቃቸው ውዝግብ ቀስቅሷል...more10minPlay
January 03, 2026የቬንዙዌላው ፕረዚደንት በአሜሪካ ልዩ ሐይሎች ተያዙየአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው ፕረዚደንቱ በአሜሪካ ልዩ ሐይሎች መያዛቸውን አረጋግጠው ለፈጸሙት ወንጀል «በሕግ ይጠየቃሉ »ብለዋል። የቬንዙዌላ መንግስት በበኩሉ ስለሐገሪቱ ፕሬዚደንት መያዝ እስከአሁን ያለው ነገር የለም።...more0minPlay
January 02, 2026በኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮችን በውይይት መፍታት ለምን አቃተ?በኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮችን በውይይት መፍታት ለምን አቃተ?...more0minPlay
January 02, 2026ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: በሳምንታት መጨረሻ የሚሰጡ የማጠናከሪያ ትምህርቶች ጥቅማቸው ወይስ ጉዳታቸው ያመዝናል?ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ማሽቆልቆሉን ተከትሎ መንግሥት የተለያዩ የትምህርቱ ማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ ከነዚህም አንዱ ቅዳሜ ቅዳሜ የሚሰጥ የማጠናከሪያ ትምህርት ነው። የዚህ ትምህርት ጥቅሙ ወይስ ጉዳቱ ያመዝናል?...more0minPlay
January 02, 2026የኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችአቶ አበባው ደሳለው የአብን ተመራጭ የፓርላማ አባል የፍትሕ ሚኒስትሯን ሐና አርዓያ ሥላሴን "ከፖለቲካ ጫና ወጥታችሁ እውነተኛ ፍትሕ የምታሰፍኑት መቼ ነው" ብለው ጠይቀዋል። ሚኒስትሯ "አንድ ሰው የፖለቲካ ግቡን ለማሳካት በሕገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ከሆነ ፖለቲከኛም ሆነ፣ የመንግሥት ኃላፊ የሕግ ተጠያቂነትን እናረጋግጣለን። ሲሉ መልሰዋል...more0minPlay
January 02, 2026የናፍጣ አጥረት በደቡባዊ ኢትዮጵያ ከተሞችአገልግሎቱን ባለማግኘታቸው በየከተሞቹ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከሁለት እስከ አራት ቀናት ለመሰለፍ መገደዳቸውን ለዶቼ ቬለ አስተያየታቸውን የሰጡት አሽከርካሪዎቹ “ ናፍጣ የሚገኘው በማደያዎች መልካም ፍቃድ ሆኗል ፤ከፈለጉ ይቀዱልናል ካልፈለጉ የለም ብለው ሰልፉን ይበትኑታል ፡፡ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ሊሰጡን ይገባል “ በማለት ጠይቀዋል ፡፡...more4minPlay
January 02, 2026ላሊበላ የሚሄዱ የውጭ ጎብኝዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል ተብሏልበላሊበላ ተደጋጋሚ ግጭቶች ቱሪዝምን በመጉዳታቸው ማህበረሰቡ እና አስጎብኚዎች ለከፋ ችግር ተዳርገው ነበር የሚሉት የላሊበላ አስጎብኚዎች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ እስታሉ ቀለሙ አሁን ግን ዘርፉ በመነቃቃት ላይ ነው ብለዋል፡፡ እንደየሰሜን ወሎ ዞንባህል ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ 4ሺህ የሚደርሱ የውጭ ቱሪስቶች ላሊበላን ለመጎብኘት ወደከተማዋ ገብተዋል።...more4minPlay
January 02, 2026"ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት" ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና አገኘለሦስት ዓመት ተኩል በትብብር ሲሠሩ የቆዩ አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም የመሠረቱት ይህ ቅንጅት "ኢትዮጵያ የህልውና አደጋ ውስጥ ናት" የሚለው ድምዳሜ ለመመሥረታቸው ዐቢይ መነሻ መሆኑ አስቀድሞ ተነግሯል።ከመሥራች ድርጅቶች አንዱ የሆነው እናት ፓርቲ በቅንጅቱ እንዳይቀጥል በምርጫ ቦርድ እግድ ተጥሎበታል።...more5minPlay
January 01, 2026በአቶ ታዬ ደንደዓ አዲሱ ክስ ላይ የተሰጠው ብይንየፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አንደኛ የፀረ-ሽብርና ሕገመንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ በተከሰሱበት አዲስ ክስ ላይ ዛሬ ብይን ሰጥቷል።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,886 episodes available.