Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,886 episodes available.
January 01, 2026በሕገወጥ መንገድ ወደ አረብ ሃገራት ሊሰደዱ ሲሉ የተያዙ ወጣቶች ጉዳይየተሻለ የኑሮ ሁኔታን በመመኘት የማያውቁትን ሀገር የሚናፍቁ አዳጊ ወጣቶች በሕገወጥ መንገድ ወደ አረብ ሃገራት ለመጓዝ በአፋር ክልል በኩል የጂቡቲን መስመር ይጠቀማሉ። እነኝህ አዳጊ ወጣቶች በቅርብ ሰው አለያም በደላላ አማካኝነት ነው ይህንን መንገድ እንዲጓዙ የሚደረጉት።...more4minPlay
January 01, 2026የቻይና ወታደራዊ ልምምድ እና የታይዋን ማስጠንቀቂያአሮጌው ለመባል በበቃው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2025 በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ከታዩ ውዝግቦች እየተባባሰ የሄደ የሚመስለው በታይዋን ጉዳይ የቻይና እና የአሜሪካ የእጅ አዙር ፍጥጫ ነው።...more5minPlay
January 01, 2026የተከሳሾች የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት ጉዳይበሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያሉ የምክር ቤት አባላት፣ ፖለቲከኞች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እና ሌሎችም ከእሥር ሊፈቱ ነው የሚል መረጃ እየተሰራጨ ነው። የዚህን ተጨባጭነት የጠየቅናቸው ከተከሳሽ ጠበቆች አንደኛው መረጃው በስፋት እየተነገረ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን «እስካሁን የተፈታ እሥረኛ የለም» ብለዋል።...more0minPlay
January 01, 2026የሰላም ጉባኤ በጋምቤላበጋምቤላ ክልል ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለመፍታት የሰላም ጉባኤዎች በመካሄድ ላይ ናቸው። በክልሉ ርዕሰ ከተማ ከኑዌርና አኙዋክ ማኅበረሰብ የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች የሃይማኖት አባቶችን ያተሳፈ ጉባኤ መካሄዱን ያነጋርናቸው የጉባኤው ተሳታፊዎች አመልክተዋል።...more0minPlay
January 01, 2026የሰነድ አልባ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እሥር በኬኒያየኬንያ ለሥልጣናት ባለፉት 10 ወራት ብቻ ካለጉዞ ሠነድ ወደ ኬኒያ ለመግባት የሞከሩ 953 ፍልሰተኞች በፀጥታ አካላት ተይዘው በእሥር ላይ ይገኛሉ ፡፡ ከእነዚሁ ፍልሰተኞች መካከል 670 ወይም 70 ነጥብ 3 በመቶ ያህሉ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ጠቅሰዋል ፡፡ ከኢትዮጵያን ቀጥሎ ያለውን ቦታ ሶማሌዎች ቡሩንዲያዊያን እና ኤርትራዊያን ይይዛሉ ።...more0minPlay
December 31, 2025ኢትዮጵያውያን እና ያላባራው ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ይፋ ባደረገው መረጃ በጥቅምት ከኢትዮጵያ የሚነሱ ድንበር የመሻገር እንቅስቃሴዎች 26 በመቶ ጭማሪ እንዳሳዩ ገልጿል። እንቅስቃሴዎቹ በሱዳን፣ በጅቡቲ እና በሶማሊያ በኩል መመዝገባቸውን የጠቀሰው ድርጅቱ የኢኮኖሚ ጫናዎችና በግጭቶች እየጨመረ የመጣው የሰብአዊና የጥበቃ ሥጋቶች ዋና ዋና እንደሆኑ ጠቅሷል።...more4minPlay
December 31, 2025ብሪታንያንና ካናዳን ጨምሮ ዐሥር አገራት«አደገኛ» ስላሉት የጋዛ ሰብዓዊ ሁኔታ ያወጡት ማስጠንቀቂያዐሥር የበለጸጉ አገራት «አደገኛ» ስላሉት የጋዛ ሰብአዊ ሁኔታ ባወጡት የበጋራ መግለጫ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የጋዛ ህዝብ በአስቸኳይ መጠለያ እንደሚያስፈልገው የጤናና ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶችም ሊሟሉለት እንደሚገባ አሳውቀው እስራኤል በአስቸኳይ አስፈላጊ ያሏቸውን ርምጃዎች እንድትወስድም ጥሪ አቅርበዋል ።...more7minPlay
December 31, 2025የቀነኒ አዱኛ ቤተሰብን ከአርቲስት አንዱዓለም ጎሳ ጋር ለማሸማገል የተደረገው ባህላዊ የእርቅ ጥረት ለምን ተደናቀፈ?ባለፈው ዓመት ከአርቲስት አንዱዓለም ጎሳ ጋር ከሚኖሩበት ቤት 5ኛ ፎቅ ወድቃ ህይወቷ ማለፉ የተሰማው የሞዴል ቀነኒ አዱኛን ጉዳይ በባህላዊው የኦሮሞ አባገዳዎች ስርዓት በእርቅ ለመቋጨት የተደረገው ጥረት ያለፍሬ ማብቃቱን አባገዳዎች አመለከቱ፡፡የሟች አባት ደግሞ የገደለ ሳይታወቅ እንዴት ጉማ እንበላለን ብሎ ቤተሰብ ጥያቄውን ማስቀመጡን ገልጸዋል፡፡...more4minPlay
December 30, 2025በአማራ ክልል 3.1 ሚልየን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አልሄዱም ተባለበአማራ ክልል 36 በመቶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ብቻ በትምህርት ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ። በክልሉ 3.1 ሚልየን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አልሄዱም ተብሏል። በክልሉ የሚገኙ ወጣቶችም ክልሉን ለቀዉ እየወጡ ነዉ ተብሏል።...more4minPlay
December 30, 2025የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የምክር ቤት ማብራሪያኢትዮጵያ ከእስራኤል ቀጥላ «ለሶማሊላንድ እውቅና በመስጠት ሁለተኛ ሀገር ትኾን?» የሚለውን ጥያቄ አንድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዛሬ ማክሰኞ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዮስ አቀረቡ።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,886 episodes available.