Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,886 episodes available.
December 27, 2025በፖለቲካ ምክንያት በእሥር ላይ ያሉ ሰዎች እንዲፈቱ ተጠየቀበፖለቲካ እና በማንነት" ምክንያት ለእሥር የተዳረጉ ያላቸው ፖለቲከኛች እና የመገናኛ ብዘኃን ባለሙያዎች እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ጠየቀ። ፓርቲው አመራሮቹ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እሥረኞችን ከጎበኙ በኋላ ባወጣው መግለጫ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች የግፍ እሥር እንዲቆም መሥራት ይጠበቅባቸዋል ሲል ጠይቋል።...more0minPlay
December 27, 2025እስራኤል ለሶማሌላንድ የሰጠችው እውቅና ምን ያስከትል ይሆን?እስራኤል ለምስራቅ አፍሪካዊቷ ራስ ገዝ ግዛት ሶማሌላንድ የአገርነት እውቅና የሰጠችው የመጀጀመሪያዋ አገር መሆናን ተከትሎ ውዝግብ የማያጣው የአፍሪካ ቀንድ በብዙ እያወዛገበ ነው፡፡ የእስራኤልን እውቅና ተከትሎ በመላው ዓለም የተለያዩ ድምጾች እየተሰሙ ሲሆን በሀርጌሳ ደግሞ ደማቅ ሕዝባዊ የደስታ ትዕይንት ታይቷል።...more0minPlay
December 27, 2025የአፍሪካ ሕብረት፤ እስራኤል ለሶማሊላንድ ነጻ ሉአላዊት ሐገር አድርጋ እውቅና መስጠቷን አወገዘየእስራኤል የእውቅና መስጠት መግለጫን ተከትሎ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ ዛሬ እንዳስታወቁት የእስራኤልን ድርጊት ሕገወጥ ሲሉ አውግዘውታል።...more0minPlay
December 26, 2025ከ27 ዓመታት በኋላ ወደአገራቸው የተመለሱት የመጀመሪያው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳት እንዴት ይታወሳሉ?የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት አቶ ሀሰን አሊ ከ27 ዓመታት በኋላ ትናንት ሓሙስ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ወደ አገርቤት ተመልሰዋል፡፡ አቶ ሀሰን ከኢህአዴግ ጋር በገቡት የፖለቲካ ችግር ከስደት ትናንት ወደ አገር ቤት ሲመለሱ የወቅቱ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡...more0minPlay
December 26, 2025ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ታዳጊዎች የወላጆች ምክርን እንዴት ይመለከቱታል?ወላጆች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክሮችን ሊለግሱ ይችላሉ፡፡ ይሁንእንጂ ታዳጊዎች ወላጆች በሚሰጧቸው ምክሮች እና ተግፃፆች ላይ የተለያየ አረዳድ አላቸው ፡፡ አንዳንዶች ፤ ቤተሰብ ሁልጊዜ ልክ ነው ታዳጊዎች ቤተሰቦቻቸውን መስማት አለባቸው ሲሉ ሌሎች ደግሞ ልጆች የማያምኑበት ነገር ሲኖር ሀሳባቸው መግለጽና ማስረዳት አለባቸው ይላሉ ፡፡...more0minPlay
December 26, 2025የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች የዘላቂ የመንግስት ድጋፍ ጥያቄበሰሜንና ደቡብ ወሎ በካምፕ ዉስጥ የሚገኙ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች መንግስት ድጋፍ እያደረገልን ቢሆንም ዘላቂ መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል አሉ። ተፈናቃዮቹ በነፍሰ ወከፍ 15 ኪሎ በቆሎ በየወሩ እየደረሳቸዉ ቢሆንም ለአመታት ተረጂ መሆናቸው ለስነ ልቦናዊ ጉዳት እንደዳረጋቸው ተናግረዋል።...more0minPlay
December 26, 2025በትግራይ ክልል ለረሃብ ለተጋለጡ ተፈናቃዮች ሰብአዊ ድጋፍን በሚመለከት የተፈጠረው ውዝግብበትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ "የፖለቲካ ፍላጎት" ማራመጃ እየሆነ ነው ሲል የፌዴራል አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ገለፀ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ግን በክልሉ ወደ "አንድ ሚልዮን የሚሆኑ ተፈናቃዮች በካምፖችና ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው ያለ በቂ ሰብአዊ ድጋፍ በአስከፊ የኑሮ ሁኔታ" እየኖሩ ነው ብሏል።...more0minPlay
December 26, 2025በክልሉ በጉልበት ስራ ላይ የተሰማሩ ተፈናቃይ ሕጻናት ዕጣ ፈንታቸው አሳሳቢ ነው መባሉከትግራይ ክልል ደንጎላት እና አማራ ክልል ከዋግ ህምራ ብሄረሰብ ዞን ፃግብጂ ወረዳ የመጡ ህፃናት ለልመና እድሜያቸዉን ለማይመጥን ስራ እየተዳረጉ ነዉ ተባለ ። ህፃናቱ በደሴ ከተማ የተለያዮ አካባቢዎች ይህንን ተግባር ሲፈፅሙ እድሜያቸዉ ከ8 እስከ 12 አመት ይሆናል።...more0minPlay
December 26, 2025የብር የመግዛት አቅም መዳከም በሀገሪቱ ኤኮኖሚ ላይ ምን አስከተለ?የኢትዮጵያ ብር በዓለማቀፍ ደረጃ በመግዛት አቅሙ እጅግ ደካማ ከተባሉ የመገባያ ገንዘቦች ከቀዳሚዎቹ ተርታ መሰለፉ ተዘግቧል፡፡ ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ላይ ዘገባዎችን የሚያወጣው ብሉምበርግ ከሰሞኑ እንደዘገበው የኢትዮጵያ ብር ከአርጄንቲናው ፔሶ እና ከቱርክዬ ሊራ በመቀጠል በፍጥነት እየተዳከመ የመጣ ገንዘብ ብሎታል፡፡...more4minPlay
December 25, 2025የተፈናቃይ ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦትና ሰሞነኛ ኹኔታበግጭት፣ በጦርነት እና መሰል አስገዳጅ ችግሮች ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ኹኔታ ሰሞኑን ብርቱ መነጋገሪያ ሆኗል።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,886 episodes available.