Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.
August 17, 2026በትግራይ ክልል የጦርነት ድባብ ያስከተው ተጽዕኖበሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ድባብ ባስከተለው ስጋት ወደ መቀለ ከሚጓዘው ይልቅ ከዚያ ወደ መሀል ሀገር የሚሄደው እንደሚበረክት የክልሉ ነዋሪዎች ገለጹ።...more0minPlay
August 17, 2026ችግር ሸሽተው ሌላ ችግር ላይ የወደቁት የትግራይ ወጣቶችበትግራይ ክልል ዳግም ያንዣበበውን ጦርነትና የግዳጅ አፈሳ በመሸሽ ወደ አዲስ አበባ ያመሩ ወጣቶች ለዳግም ችግር መጋለጣቸውን ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።ወጣቶቹ በከተማዋ ገጠመን ያሉት የመጠለያ፣ የምግብና የሥራ እጦት ጎዳና ላይ እስከማደር አድርሷቸዋል።በተለይ ሴቶች የአዲስ አበባ ኑሮ አልሳካ ሲላቸው ለሕገ-ወጥ ስደት መዳረጋቸውን ተናግረዋል።...more0minPlay
August 16, 2026ኢትዮጵያ አሰቃቂ ግፎች ከሚፈጸምበት የግጭት አዙሪት መውጣት ለምን ተሳናት?በተደራራቢ ግጭቶች ውስጥ ለተፈጸሙ ግፎች ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ፤ ተጎጂዎችም ፍትሕ ሳያገኙ ኢትዮጵያ ሌላ የጦርነት ሥጋት ተጋርጦባታል። ለበርካታ አስርት ዓመታት ስለ ዴሞክራሲ ቢሰበክም የፖለቲካ ልሒቃኑ አገሪቱን ከግጭት አዙሪት ማላቀቅ አልቻሉም። ለምን? የለየለት ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ማቆም የሚችል ወገን አለ? ወይስ ረፍዷል?...more0minPlay
August 15, 2026በቆቦ ጮቢ በር ፤ በህወሃትና በመከላከያ መካከል ዛሬ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ነዋሪዎች ገለፁየትግራይ እና አማራ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው የቆቦ አካባቢዎች ዛሬ ማለዳ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና በሕወሃት ታጣቂዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል። ነዋሪዎቹ እንዳሉት በቆቦ ጮቢ በር እና አዲስ ቅኝ በተባሉ አካባቢዎች ማለዳ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ የተጀመረው ዉጊያው ጥቂት ቆይቶ ጋብ ብሏል።...more4minPlay
August 15, 2026የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች እና ዲሞክራሲ ገጽታ ላይ ያወጣው ሪፖርትበኢትዮጵያ በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች አሁንም "ከባድ" የሚባሉ ሥጋቶች መቀጠላቸውን የአውሮፓ ሕብረት ይፋ ባደረገው ኢትዮጵያን የተመለከተ የ2025 የሰብዓዊ መብቶች እና የዲሞክራሲ ገጽታ ሪፖርት ላይ አመልክቷል።እንደ ሪፖርቱ በሰሜን ኢትዮጵያ የቀጠለው ግጭት የሰላማዊ ዜጎችን ሕይወት ጎድቷል።መፈናቀል አስከትሏል። የሰብአዊ ተደራሽነትንም ገድቧል።...more4minPlay
August 15, 2026የጊዳ አያና አንገር-ጉቴ ተፈናቃዮችና የቀጠለው የፀጥታ ስጋትበኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳአያና ወረዳ አንገር ጉቴ ከተማ ዙሪያ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ እና እሁድ የተከሰተው ግጭት በተፈጠረው አለመረጋጋት እና ስጋት ከአከባቢው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ብርቱ ችግር እንደጠማቸው ገልፀዋል፡፡እንደ ተፈናቃዮቹ ባለፉት አምስት ቀናት ገደማ በአከባቢው ተከስቶ የነበረው ግጭት የተረጋጋ ቢመስልም ስጋቱ ግን ቀጥሏል።...more4minPlay
August 15, 2026ትኩረት በአፍሪቃ፣ ኤርትራ፣የአፍሪቃ ቀንድ ሥልታዊ ግን የአባገነን ምድርእና የኤቦላ ክትባት ተስፋከሰሜን ሱዳን ጥግ ራስ ካሳር እስከ ደቡብምሥራቅ ግርጌ ጀቡቲ ጠረፍ ወይም ባብ ኤል መደብ ወሽመጥ አጠገብ ራስ ዱሜራ ድረስ የሚወርደዉ የኤርትራ የባሕር ድንበር ከ1000 ኪሎ ሜትር ይበልጣል።ጥያቄዉ ግን ከባሕር ወሽመጡ በተቃራኒ የሚዋሰነዉን ግዛት የሚቆጣጠረዉ ማነዉ-ነዉ።«የመን ናት» መለሱ ኤርትራዊዉ የፖለቲካ ተንታኝ አብዱረሕማን ሰይድ...more15minPlay
August 15, 2026ችግሮች በተባባሱባት አፍጋኒስታን የታሊባን አስተዳደር አምተኛ ዓመቱን እያከበረ ነውችግሮች ተባብሰው ከድጡ ወደ ማጡ መግባቷ በሚነገርላት አፍጋኒስታን፤ የታሊባን አስተዳደር በሀገሪቱ መንግስት ሆኖ ወደ የስልጣን የተመለሰበትን አምስተኛ ዓመት በዛሬው ዕለት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ መሆኑ ተዘግቧል።ታሊባን በሀገሪቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለሴት ልጆች መከልከልን ጨምሮ መብትን የሚገድቡ የተለያዩ ፖሊሲዎችን አውጥቷል።...more0minPlay
August 14, 2026የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ያጋጠመው ተግዳሮትየኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በአስተዳደር በደሎችና ቅሬታዎች ላይ የሚሰጣቸው ምክረ ሀሳቦች በአስፈፃሚዉ አካል እይተገበሩም ሲል አማረረ ፡፡ የተቋሙ የሥራ ሃላፊዎች እንደሚሉት አብዛኞቹ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ለተቋሙ ጥያቄዎች ምላሽ ባለመስጠታቸውና ውሳኔውንም ባለመተግበራቸው ለዜጎች መብት ጥሰት ምክንያት እየሆኑ ይገኛሉ።...more0minPlay
August 14, 2026የቻይና እና አሜሪካ ኩባንያዎች ፉክክር በቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታየአሜሪካና ቻይና ኩባንያዎች ኢትዮጵያ በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ በምታስገነባው ግዙፍ አየር ማረፊያ ላይ ለመሳተፍ እየተፎካከሩ ነው ተብሏል። የቻይና ኩባንያዎች በግንባታ ውል ጨረታ በሰፊው እተሳተፉ ሲሆን፤ አሜሪካም ቦይንግን በመሳሰሉ ታላላቅ ኩባንያዎቿ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚፈልገው ዘጠኝ ቢሊየን ዶላር ገደማ ውል ለመሳተፍ አቅደዋል።...more5minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.