Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.
August 14, 2026ባለፉት አምስት ወራት ብቻ 105 ስደተኞች መሞታቸው ተገለፀኢትዮጵያውያን በሚያዘወትሩት ምሥራቃዊ የፍልሰት መስመር ባለፉት አምስት ወራት ብቻ 106 ስደተኞች መሞታቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች መርጃ ድርጅት ገለፀ። እንደ ድርጅቱ ከአፍሪካ ቀንድ ተነስተው በጅቡቲና በቦሳሶ በኩል ወደ ባህረ ሰላጤው ሀገራት በሚደረጉ አደገኛ የስደት መስመሮች ከሚጓዙት 95 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው።...more0minPlay
August 14, 2026ሲፒጄ በእሥር ላይ ያሉ 5 ጋዜጠኞች ይቅርታ ጠይቀው እንዲፈቱ ጫና ተደርጎባቸዋል አለኢትዮጵያ ውስጥ በእሥር ላይ ያሉ አምስት ጋዜጠኞች የተከሰሱበትን የሽብር ክስ አምነው ይቅርታ እንዲጠይቁ እና እንዲፈቱ ጫና እንደተደረገባቸው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) ገለፀ።ሲፒጄ በእሥር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ገነት አስማው፣ዳዊት በጋሻው፣መስከረም አበራ እና አባይ ዘውዱ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪ አድርጓል።...more0minPlay
August 14, 2026ትሰማ፤በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ይቁም የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘመቻበኢትዮጵያ በሴቶችና ሴት ልጆች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንደ ሀገራዊ አደጋ ተቆጥሮ ምላሽ እንዲሰጠው የሚጠይቅ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ተጀምሯል ።"ትሰማ" በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ይህ ንቅናቄ በኢትዮጵያ በሴቶችና ሴት ልጆች ላይ የሚፈጸም ጥቃትን ብሔራዊ አደጋ ሆኖ እንዲታወጅ ጥሪ ለማቅረብ ነው።...more0minPlay
August 14, 2026በኢትዮጵያ ለወጣት ምሩቃን ሥራ ፍለጋ ምን ይመስላል?የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለዓመታት ያስተማሯቸውን ወጣቶች ባለፉት ወራት በተከታታይ ሲያስመርቁ ቆይተዋል። ወጣቶቹ በተማሩበት የሙያ መስክ የመሥራት ሕልማቸውን ለማሳካት፣ ኑሯቸውን ለማቋቋም እና ግፋ ሲልም ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ከምረቃ በኋላ ሥራ ፍለጋ ይጀምራሉ። ለመሆኑ ለምሩቃኑ ሥራ ፍለጋ ምን ይመስላል?...more0minPlay
August 13, 2026አፋር ክልል የተከሰተው የውኃ እጥረት የእንስሳት ሞት ማስከተሉበአፋር ክልል በተከሰተ ብርቱ የውኃ እጥረት የቤት እንስሳት እየሞቱ መሆኑን አርብቶ አደሮች ተናገሩ። በክልሉ በሚገኙ ወረዳዎች ባለፉት 12 ወራት የጣለው ዝናብ ዝቅተኛ በመሆኑ በተከሰተ ድርቅ ለውኃ እጥረት መዳረጋቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።...more0minPlay
August 13, 2026የኤሊኒኞ ተጽዕኖ ያስከተለው ድርቅ አመላካች የአየር ሁኔታበኤልኒኞ መከሰት ሳቢያ አሉታዊ ተፅዕኖ ስር ገብቷል በተባለው የተያዘው የክረምት ወቅት አጋማሽ ወራት «ከመደበኛ በታች እና በቂ ያልሆነ ዝናብ የተስተዋለበት» እንደነበር የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።...more0minPlay
August 13, 2026ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክክር ሂደቱ ላይ ያነሱት ሥጋት እና ያደረጉት ጥሪበአገራዊ ምክክር ሂደቱ እየተሳተፉ የሚገኙ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክክር ሂደቱ ላይ አለን ያሉትን ሥጋት ገለፁ። ፓርቲዎቹ ለምክክሩ ስኬት ጥሪ፣ ለኮሚሽኑ ማሳሰቢያ እና የአካሄድ እርምት በጠየቁበት መግለጫቸው «የአንድ ወገን ፍላጎትን በሌሎች ላይ ለመጫን» የሚደረግ ያሉት ጥረት ሥጋት እንደፈጠረባቸው ጠቅሰዋል።...more0minPlay
August 13, 2026የሦስት ወጣቶች ግድያ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መግለጫየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል «የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ባለመቀበል በሕዝብ ላይ ጉዳት አድርሰዋል» ባላቸው ቡድኖች ላይ እርምጃ ወሰጃለሁ ሲል የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።...more0minPlay
August 13, 2026በሰሜን ኢትዮጵያ ያጠላው የጦርነት ስጋት እና ውጥረትበሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል እና አፋር ክልል አዋሳኞች ላይ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎቹ መጠናከራቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። በአካባቢው ላይ ያጠላው የጦርነት ስጋት ነዋሪዎች እንዳይረጋጉ በማድረጉ ከቀየያቸው የሸሹ ስለመኖራቸውም እየተነገረ ነው።...more0minPlay
August 13, 2026ኢትዮጵያና ሌሎችም ሃገራት ያወጣሁትን ወጭ ይክፈሉኝ ስትል ደቡብ አፍሪካ ጠየቀችፕሪቶሪያ ጥያቄውን ያቀረበችው ሕገ ወጥ ፍልሰትን በመቃወም በሚል በሀገሪቱ የተካሄደውን ሰልፍና የተፈፀሙ ጥቃቶችን ተከትሎ ከ80,000 የሚበልጡ ፍልሰተኛችን ካባረረች ወይም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ካደረገች በኋላ ነው።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.