Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.
August 11, 2026በግልገል በለስ ከተማ በደረሰ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉበመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ታጣቂዎች ዛሬ አደረሱት በተባለ ጥቃት ከ10 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎች አመለከቱ። ጥቃቱ ዛሬ ከንጋቱ 12 ሰዓት ገደማ በመነሐሪያ እና አንድ ቤተክርስቲያን አካባቢ መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።...more0minPlay
August 11, 2026ለሰብአዊ መብት ሥጋት የደቀነ «የጦርነት አዝማሚያ» አለ ተባለ«ቅድሚያ ለሰብአዊ መብት-ኢትዮጵያ» የተባለው የመብት ድርጅት በሐምሌ እና ነሐሴ 2018 የሰብአዊ መብት ክትትል ምርመራ ዘገባው በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል አሳሳቢ ያለው "ውጥረት" መጨመሩን ገለጠ ። ሙሉ ዘገባውን በማገናኛው በኩል ይከታተሉ ።...more0minPlay
August 11, 2026ኢትዮጵያውያን ለሶማሊያ ኅይሎች ያስረከቡት የስምሪት ቀጠናበቡርሀካባ ከተማ የሚገኘውንና የአትዮጰያ ወታደሮች ከተረከቧቸው ቦታዎች አንዱ የኾነውን የስምሪት ቀጠና ሰሞኑን ለሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎች ማስተላለፉን፣ በሶማሊያ የአፍሪቃ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ተልዕኮ አሳውቋል ። ሙሉ ዘገባውን በማገናኛው በኩል ይከታተሉ ።...more0minPlay
August 11, 2026በኮሪደር ልማት ዕልባት ያላገኘው የአዲስ አበባ የጎርፍ አደጋበአዲስ አበባ በተለምዶ ጀሞ 3 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ12 ዓመት ታዳጊ በደራሽ ጎርፍ ተወስዶ መጥፋቱ፣ የከተማዋ የኮሪደር ልማት ከመሬት በታች ያለውን የጎርፍ ስጋት በዘላቂነት አለመቅረፉን አመላክቷል።...more0minPlay
August 10, 2026በሰሜን ኢትዮጵያ ድርቅ እና ግጭት ያጠላው ስጋትበሰሜን ኢትዮጵያ የሚጠበቀው የክረምት ዝናብ ባልጣለባቸው አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ የርሃብ ስጋት ማንዣበቡን ነዋሪዎች እና ባለሥልጣናት አመለከቱ። እንደ ነዋሪዎቹ አስተያየት በድርቁ ላይ በተጨማሪነት እየመጣ ያለው የግጭት አደጋ በፊናው የኅብረተሰቡን ስጋት እያናረው ይገኛል።...more0minPlay
August 10, 2026ማሕደረ ዜና፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት፣ የኃይል አሰላለፉ እንዴትነት፣ ምክንያትና መዘዙራሱን፣ ቤተሰብ፣ ዘመድ ወዳጅ፣ ሕዝብ ሐገሩን ሊጠቅም የሚችል በሺሕ የሚቆጠር ወጣት ረገፏል።ብዙ ሺዎች እጅ-እግር፣ አይን-ሌላ አካላቸዉን አጥተዋል።አርሶ ማምረት፣ ሰርቶ ማፍራት የሚችል ጎልማሳ፣ በየመጠለያ ጣቢያዉ ተማፅዋች ሆኗል።የመብት ተሟጋቾች እንዳሉት ልጃገረድ-ከባለ ትዳር ሳትለይ ተደፍራለች።...more0minPlay
August 10, 2026የነሐሴ 4 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባየዓለም እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዚደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ላይ ተቃውሞው በርትቷል፥ ለሥልጣናቸው ያሰጋ ይኾን? ኢትዮጵያ በተሳተፈችበት የኦሬጋኑ አትሌቲክስ ፉክክ ውጤቱ እንዴት ይገመገማል? ቃለ መጠይቅ አድረገናል፥ ተጨማሪ ዘገባም ይኖረናል ። ሙሉ ዘገባውን በድምፅ እና በጽሑፍ በማገናኛው በኩል መከታተል ይቻላል ።...more0minPlay
August 10, 2026«የእርሻ ማዳበሪያ አልደረሰንም» የሚሉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶአደሮችበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአርሻ ግበዓት አቅርቦት ላይ ከገበሬዎች ለሚነሳው እሮሮ ምላሽ እንዲሰጥ የክልሉ ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴዎች ጠየቁ። የክልሉ ባለሥልጣናት ከነገ ጀምሮ ሽያጩ ላይ ቁጥጥር ይደረጋል ብለዋል።...more0minPlay
August 10, 2026ኢትዮጵያ እና ኤርትራ - እያደገ የመጣው ውጥረትኤርትራ ከኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ተቃራኒ ለቆሙ የውስጥ ኃይላት የምታደርገው የፖለቲካ ድጋፍ «ቀስ በቀስ ወደ ወታደራዊ እቅድ እና ቀጥተኛ ተሳትፎ ሊያድግ ይችላል» ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ተቋም ባወጣው አንድ ጽሑፍ አመለከተ።...more0minPlay
August 10, 2026ከራያ አካባቢ በጦርነት ስጋት የወጣቶችና ሕጻናት መሰደድጦርነትን ሽሽተው አካባቢያቸውን ለቀው በቆቦ ከተማ ያሉ ወጣቶችን በየዕለቱ በማግባባት የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ ዓረብ ሃገራት እንዲጓዙ የሚያደርጉ ደላሎች ሲሳይ ሆነዋል እየተባለ ነው።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.