Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.
August 09, 2026የሰሜን ኢትዮጵያ ውጥረትና የተፈናቃዮች ብርቱ ሥጋትባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ካጋጠመው የሸረሪናው ውጊያ በተጨማሪ በአላማጣ የተፈጠረው ውጥረት የተፈናቃይ ጎርፍ አስከትሏል ። ከወራት በፊት ጀምሮም ለጦርነት የሚደረገውን ዝግጅት እና አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በመሸሽ ወደ ቆቦ ከተማ የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር ጨምሯል ። ሙሉውን ውይይት በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ይከታተሉ ።...more0minPlay
August 08, 2026የሱዳን የሰላም ድርድር መክሸፍየሱዳን ጦር ተጻራሪውን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በያዝነው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ማለቂያ ድረስ ድል አደርጋለሁ ሲል ዝቷል። የሱዳን ጦር ኃይል እንደዛተው የተቀናቃኙን ኃይሎች ለማጥፋትን በተለያዩ ግንባሮች በእርምጃው እየገፋ መሆኑን የጦሩ አዛዥ ለዘጋቢዎች ተናግረዋል።...more0minPlay
August 08, 2026በኤቦላ ተሐዋሲ የሚያዙት ቁጥራቸው መበራከቱዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ክፍል የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑ እየተነገረ ነው። ከሳምንታት በፊት ተሐዋሲው በተወሰነ አካባቢ ስለመገደቡና የተያዙ ሰዎችም ቁጥር መጠነኛ ስለመሆኑ ነበር የተወራው።...more0minPlay
August 08, 2026"ፅምዶ" ስለሚባለው ጥምረት ከተለያየ አቅጣጫ እየተንፀባረቁ ያሉ አቋሞችየኢትዮጵያን መንግሥት በጋራ ለመውጋት የተቀናጀ ተብሎ የሚነገርለት "ፅምዶ" የሚባለውን ጥምረት በተመለከተ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ልዩ ልዩ አቋሞች እየተንፀባረቁ ነው። የኤርትራ፣ የትግራይ እንዲሁም የአማራ ኃይላትን ያሰባሰበ ነው የሚባለው ይህ ቅንጅት "ወደ ከፍተኛ የትግል ደረጃ" ስለመድረሱ ከትግራይ በኩል በግልፅ እየተነገረ ይገኛል።...more0minPlay
August 08, 2026የገዢው ፓርቲ የዕድገት ትልም እና አይሎ የመጣው የጦርነት ውጥረትየኢትዮጵያ መንግሥት አገሪቱን በሚቀጥሉት ጢቂትአመታት ወደ መካከለኛ የኢኮኖሚ እድገት አገር እንደሚያስገባት ደጋግሞ እቅዱን ይገልጻል፡፡ባለሙያዎች እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች አመራሮች ግን አሁን በአገሪቱ ያለው ግጭት አለመረጋጋቱ በዚህ ውጥን ላይ የሚታይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳረፉ ገሃድ የወጣ ነው በማለት በእቅዱ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ፡፡...more0minPlay
August 07, 2026በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ የሚሳተፉም የማይሳተፉም ፓርቲዎች ስለ ሂደቱ ምን ይላሉ?ከምክክሩ አስቀድመው ራሳቸውን ያገለሉ ሁለት ፓርቲዎች በሂደቱ እየወጡ ያሉ መረጃዎች "የተምታቱ ይመስላሉ" የሚል እና መድረኩ "መፍትሔ አያመጣም ብለን የወሰድነው አቋም ትክክለኛነትን ያረጋገጠ ሆኖ ነው ያገኘነው"ብለዋል። የሀገራዊ የምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርአያ ግን በተለይ ስለአዲስ አበባ እስካሁን "የተወሰነ ነገር" እንደሌለ ገልፀዋል።...more0minPlay
August 07, 2026"በስውር የአገር ማፍረስ ሴራዎች" ተጠርጥረው ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡ ፖለቲከኞች ለነሐሴ 11 ተቀጠሩችሎቱ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ለሚዲያ ሰጡት በሚል ያቀረበውን የክስ ማስረጃ ካደመጠ በኋላ "የተወሰኑ ለጥርጣሬ የሚያበቁ" ጉዳዮች ማግኘቱን ገልፆ ለነሐሴ 11 ቀጠሮ ሰጥቷል። የፖሊስ ማመልከቻ ላይ ተጠርጣሪዎቹ "የሀገርን አንድነት የሚያፈርስ ውስብስብ የሽብር ወንጀል ድርጊት" ላይ እንዳገኛቸው "ሽብር-ፈጠራ" የሚል ርእስ በሰጠው ደብዳቤ ላይ ሰፍሯል።...more0minPlay
August 07, 2026አሳሳቢው የሙስና አሻጥር በኢትዮጵያየፋይናንስ ስርዓቱን የሚያናጉ ተግባራት ላይ የተሰማሩ 169 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ውለዋል፣እንዲሁም እንደ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለው ዘርፍ 109 ተጠርጣሪዎች ተለይተው እስካሁን 91 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ተብሏል።...more0minPlay
August 07, 2026እየተለመደ የመጣው የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎትበኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች በሚደረጉ ማህበራዊ ተሳትፎዎች የወንዶች ድርሻ ጎልቶ የሚስተዋልበት አጋጣሚ የበዛ ነው ፡፡ በዘንድሮው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከተሳተፉት ወጣቶች መካከል ግማሽ ያህሉ ሴቶች ናቸው ፡፡...more0minPlay
August 07, 2026ጥቂቶችን ተጠቃሚ ያደረገው የድሬዳዋ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣከመንግስት ሰራተኞች አንዱ የተሰራው ቤት እና ቆጣቢው ተመጣጣኝ አለመሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ሊስተካከል ይገባል ብለዋል። ሌላ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው ለቤት ችግሩ መቀረፍ የተለያዩ አማራጮች መታየት እንዳለባቸው ተናግረዋል። መስተዳድሩ ለችግሩ እሰራለሁ ቢልም ነዋሪው ግን ስለገቢራዊነቱ ያለውን ከፍተኛ ስጋት ገልጿል ።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.