Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.
August 07, 2026በአማራ ክልል በግጭት ምክንያት ከ3 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳቋረጡ ነውበምስራቅ ጎጃም ዞን ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የራቁ ሲሆን፣ ለሌላ ተጨማሪ ዓመትም እንዳይቀጥል መምህራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች ኮሚቴ በማቋቋም ትምህርት ለመቀጠል ጥረት እያደረጉ መሆኑን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ መምህር ይናገራሉ።...more0minPlay
August 06, 2026" አዲስ አበባ የእኛ ነች ወይም የእኔ ነች ሊሉ ይችላሉ" ኮሚሽነር መስፍን አርአያየጉባኤው የእስከዛሬ ሂደት የተሳታፊዎች የእርስ በርስ እና ከአጀንዳዎች ጋር የመተዋወቂያ፣ ቀጥሎ በስምንቱ አጀንዳዎች ላይ የሐሳብ ማመንጫ ጊዜ ሆኖ ማለፉን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።...more0minPlay
August 06, 2026በራያ እና አላማጣ አካባቢዎች ዉጥረቱ አይሏል፤ ሴቶች ለቡድን ጾታዊ ጥቃት ተዳርገዋልበራያ አለማጣና አካባቢው ባለ የጦርነት ዉጥረት ምክንያት ከተፈናቀሉ ሴቶች መካከል በርካቶቹ ለአሰቃቂ ቡድናዊ ጾታዊ ጥቃት፣ ለአካል ጉዳትና ለሕክምና እጥረት መዳረጋቸውንና በውጤቱም ህይወታቸውን ለመምራት አስገዳጅ ወደሆነ አዲስ የሕይወት መስመር ለመግባት መገደዳቸውን ገለጹ።...more0minPlay
August 06, 2026በሮም የደመቀው የኢትዮጵያውያን የባህል እና የስፖርት ፌስቲቫልበሮም ከተማ በተካሄደው 21ኛው የአውሮፓ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ተሳትፈዋል። ዝግጅቱ የባህል፣ የአንድነት እና የፍቅር መድረክ ሆኖ ማለፉን ታዳሚዎች ገልጸዋል።...more0minPlay
August 06, 2026የአውሮጳ የሰላም ፋዉንዴሽ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የገባው ስጋትበሰሜን ኢትዮጵያ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል እያሰጋ ባለው የጦርነት አደጋ በርካቶችን ጭንቀት ውስጥ መክተቱን ከዚህ በፊት በተካሄደው ጦርነት በርካታ የጉዳት ጊዜ ያሳለፉ ተጎጂዎች ይገልጻሉ፡፡ የከዚህ በፊት የጦርነቱ ምዕራፍ ተጎጂዎቹ እንደሚሉት ሊመጣ የሚችለው አደጋም ይበልጥ ያሰጋቸዋል፡፡...more0minPlay
August 06, 2026ሲፒጄ ለ6 ሃገራት ጋዜጠኞች እውቅና ሲሰጥ በኢትዮጵያ የታሠሩት እንዲፈቱ መጠየቁመቀመጫውን ኒዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ በእንግሊዝኛ ምህጻሩ ሲፒጄ ለስድስት ሃገራት ጋዜጠኞች እውቅና ሰጠ። 16ቱ የታሰሩ ኤርትራውያን ጋዜጠኞች ናቸው። ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ዓለም አቀፍ ተቋም ኢትዮጵያው ውስጥም በእስር ላይ የሚገኙ አምስት ጋዜጠኞችን እንዲፈቱ ለሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጥሪ አቅርቧል።...more0minPlay
August 06, 2026በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው የ14 ሀገራት ቅንጅት በይፋ ከተገለጸው አላማ የሰፋ ትርጉም አለው- የፀጥታ ተንታኝሳዑዲ አረቢያ ሰሞኑን ይፋ ያደረገችው የ14 ሀገራት የባሕር ላይ እንቅስቃሴ መከላከያ ቅንጅት በይፋ ከተገለጸው አላማ የሰፋ እንድምታ እንዳለው አንድ አንጋፋ የፀጥታ ተንታኘ ተናግረዋል።...more0minPlay
August 06, 2026የዐማራ ግሎባል ፎረም የምክክር ጉባኤውን መቃወሙበኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው አገራዊ ምክክር፣ ጉባኤውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ዋና ዋና መሥፈርቶችን የማያሟላ በመሆኑ አጥብቆ እንደሚቃወም፣የዐማራ ዲያስፖራ ግሎባል ፎረም አስታወቀ።...more0minPlay
August 05, 2026ኢንተርኔት በሌለበት ሰዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው ዲጅታል አማራጮችከዓመታት በፊት ሰዎች ለመዝናኛ ብቻ ይጠቀሙባቸው የነበሩ በተለይም ኢንተርኔትን መሰረት ያደረጉ የዲጅታል ቴክኖሎጂዎች በአሁኑ ወቅት ያለ እነሱ መረጃ ማግኘት ፣ ተግባቦት፣ ትምህርት ፣ የንግድ ስራን ማሳለጥ የጤና አገልግሎት ወዘተ የማይታሰብ ሆኗል።ለመሆኑ ኢንተርኔት በሌለበት ሰዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው ዲጅታል አማራጮች የትኞቹ ናቸው?...more0minPlay
August 05, 2026የኢትዮጵያ ብር የምንዛሪ ተመን ከዶላር አኳያ በዓመት 15 በመቶ ተዳክሟልብር በአንድ ዓመት ብቻ ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን 15 በመቶ ተዳክሟል። በሐምሌ 2016 ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ የወርቅና የቡናን የወጪ ንግድ ቢያበረታታም ሸማቾችን እየተፈታተነ ይገኛል። ከዚያ ባሻገር የመደበኛ እና የትይዩ የውጭ ምንዛሪ ገበያዎች የተመን ልዩነት አሁንም በሚጠበቀው ልክ አልጠበበም።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.