Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.
August 05, 2026ኑዌር ዞን-ጋምቤላ ክልል የተከሰተዉ የዝናብ እጥረት ሰብል እያደረቀ ነዉከሰኔ ወር ወዲህ ዝናብ በወረዳው ለጥቂት ቀናት ብቻ መዝነቡን የተናገሩት ነዋሪው ከምርት በተጨማሪም ሳርና ሌሎች አትክልቶች ላይም ተጽህኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ተናገርዋል፡፡...more0minPlay
August 05, 2026በደቡብ ኢትዮጵያ የወባ በሽታ በፍጥነት እየተዛመተ ነዉበደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ2018 ዓ.ም የወባ በሽታ ህመም ምልክት አሳይተው ከተመረመሩት 2.9 ሚሊዮን ህሙማን መካከል 1.06 ሚሊዮን ሰዎች የወባ በሽታ እንደተገኘባቸው ከክልሉ ጤና ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።...more0minPlay
August 05, 2026የደቡብ ወሎ ወጣቶች አገልግሎትና የሰላም ጥሪበደቡብ ወሎ ዞን 1 ሚሊዮን የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች 1.4 ቢሊዮን ብር ግምት ያላቸውን ስራዎችን በነጻ ሰርተዋል የሚሉት የዞኑ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ምስጋናው ደምሴ ናቸው።...more0minPlay
August 05, 2026የአፍሪካ ሀገራት ድንበሮችን በግልጽ በማካለል ግጭት ማስቀረት እንደሚገባ ተገለጸኹለቱን ሀገራት የሚለየው አለምአቀፉ የድንበር መስመር በወረቀት ላይ የተሰመረው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ1963 ቢኾንም፣ በውሃው ላይ ግን ምንም መለያ ምልክት ሳይኖር ከስድስት አስርተ አመታት በላይ ቆይቷል።...more0minPlay
August 05, 2026ኢትዮጵያና ግብፅ በአባይ ወንዝ ዉኃ አጠቃቀም የገጠሙት ዉዝግብ አገርሽቷልየግብጽ የመስኖ ሚኒስትር ሀኒ ሰዊላም ትናንት ማክሰኞ ሃምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ካይሮ ውስጥ በሰጡበት የፕሬስ ኮንፌረንስ ላይ “ኢትዮጵያ ሌላ ግድብ በናይል ወንዝ ላይ እንድትገነባ አትፈቅድም” ብለው መናገራቸውን የቱርክዬ የዜና አውታር አናዶሉ ኤጄንሲ የግብጽ መመገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡...more0minPlay
August 04, 2026የሰሜን ኢትዮጵያው የጦርነት ስጋት ቀጠናዊ ስጋት ያጭር ይሆን?ባለፈው ቅዳሜ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ጠረፍ የተከሰተው ውጊያ ወደለየለት ጦርነት የሚሸጋገር ከሆነ ችግሩ ከአገር ውስጥ ስጋት ወደ ቀጣናውም ሊሸጋገር እንደሚችል ተንታኞች እያስጠነቀቁ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትና ህወሓት መካከል ሊቀሰቀስ ከጫፍ የደረሰ በመሰለው ጦርነት የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት እየታየ መሆኑን ፖለቲከኞች ይናገራሉ፡፡...more4minPlay
August 04, 2026"በቀደመው የትግራይ ጦርነት የፍትህና ተጠያቂነት ማጣት ለቀጣይ ግጭት በር ከፍቷል " አምነስቲዓለማቀፍ የሰብአዊ መብቶችን በቅርበት የሚከታተለው አምንስቲ እንተርናሽናል በትናንት ሰኞ ይፋዊ መግለጫው ። «ግጭቱ እንደ አዲስ መቀስቀሱ፣ ነዋሪዎችን ድጋሚ ለከባድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አደጋ ያጋልጣልየሚል ስጋት ገብቶኛል» ብሏል።...more6minPlay
August 04, 2026የችግኝ ተከላ፤ ቁጥሮችና ለውጦችበአረንጓዴ አሻራ መርኀግብር በአንድ ቀን ጀንበር ከ800 ሚሊየን በላይ ችግኝት በትናንትናው ዕለት ኢትዮጵያ ውስጥ መተከሉ ተነግሯል። የአፈር መሸርሸርና የደን መራቆት በከፍተኛ ደረጃ ከጎዳቸው ሃገራት አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ዘንድሮ ባጠቃላይ 800 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዟል። ለመሆኑ የተተከሉት ችግኞች በቂ ክትትል ይደረግላቸው ይሆን?...more11minPlay
August 04, 2026ሁለት ፖለቲከኞች እና አንድ ጠበቃ ታሠሩየኢሕአፓ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስሐቅ ወልዳይ እንዲሁም የፓርቲው አባል ፖለቲከኛ አበበ አካሉ በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መታሠራቸውን ፓርቲው አረጋግጧል። ጠበቃ አበራ ንጉሥ በፖሊስ ተይዘው በፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ እሥር ላይ መሆናቸውን የሙያ አጋራቸው ነግረውናል።...more4minPlay
August 04, 2026የሸረሪናው ውጊያ፣ ያሰጋው የከባዱ ጦርነት መጀመሪያ ይሆን?ውጊያ ተካሄደ ከተባለበት ከሸረሪና አካባቢ ቁስለኞችን ጨምሮ ሌሎችም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ሱዳን መግባታቸውን የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል። ከውጊያው በኋላ የትግራይ ተዋጊዎች ናቸው የተባሉ አስከሬኖች ሱዳን ድንበር ላይ መገኘታቸውንም የህክምና ምንጮች መናገራቸውም ተዘግቧል።...more6minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.