Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.
December 19, 2025የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ለዩክሬይን 105 ቢሊዮን ዶላር ለማበደር ተስማሙየአውሮጳ ህብረት መሪዎች ለዩክሬን የ 105 ቢሊየን ዶላር ወይም 90 ቢሊዮን ዩሮ ለማበደር ዛሬ አርብ ስምምነት ላይ ደረሱ። ይህ ብድር ዩክሬይን ያለባትን የበጀት እጥረቶች ይሸፍናል ተብሏል። ይሁንና መሪዎቹ በአዉሮጳ ሃገራት የተያዙ የሩስያ ቱጃሮች ንብረቶችን ለዩክሪይን ይዋል በሚለዉ ላይ አልተስማሙም።...more0minPlay
December 19, 2025በሰንዳፋ በአሰቃቂ የተገደለችዉ የሁለት ታዳጊዎች እናት ጉዳይበኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰንዳፋ ከተማ ሰኞ ምሽት በጾታዊ ጥቃት የተገደለችው እናት ጉዳይ በበርካቶች ዘንድ ኀዘን እና ቁጣን ቀስቅሷል።...more0minPlay
December 19, 2025ስለ 7ኛዉ ብሔራዊ ምርጫ ቀን እና ተያያዥ ጉዳዮች ምን ያህል ሕዝብ ያውቃልየኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የ 7ኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ከሁለት ሳምንት በፊት ለሕዝቡ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።ስለምርጫውና ተያያዥ ዝርዝር ጉዳዮች ምን ያህል ኅብረተሰቡ ግንዛቤ አለው?...more0minPlay
December 19, 2025ህጻናትን ጨምሮ በሕገ ወጥ መንገድ ለመኮብል የሞክሩ ከ700 በላይ ወጣቶች መያዛቸዉበሕገ ወጥ መንገድ ከተለያዩ የኢትዮጱያ ክልሎች ደላላ አማካኝነት ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለመኮብለል በማሰብ በጉዞ የነበሩ ኮብላዮች በአፍር ክልል በአደኣር ፓሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል የሕገ ወጥ ፍልሰተኞቹ ከትግራይ አማራና ኦሮምያ ክልል የመጡ ናቸዉ። ከነዚህ ሕገ ወጥ ኮብላዮች መካከል እድሜያቸው ከ13 --15 ዓመት የሚሆናቸው ህፃናት ይገኙበታ።...more0minPlay
December 19, 2025ሀገራዊ ፖሊሲዎች ሲወጡ ወጣቶች ያላቸው ድርሻመቀመጫውን ናይሮቢ ኬንያ ያደረገውና ለትርፍ ያልተቋቋመው የአፍሪካ የማኅበራዊ እና የአስተዳደር ጥናት ትብብር የተባለው ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአሥር የአፍሪካ አገሮች የሚከናወን ወጣቶች ላይ ያተኮረ አንድ ጥናት ጀምሯል።...more0minPlay
December 19, 2025የአራት ሀገራት የሰብአዊ መብት ተቋማት ስደተኞችን የተመለከተ ጥሪኢትዮጵያን ጨምሮ የኬንያ፣ የሞዛምቢክና የዛምቢያ ብሔራዊ የሰብአዊ መብት ተቋማት የስደት መተላለፊያ የሆኑ የደቡባዊ ቀጣና የስደት ፖሊሲዎችን እንዲከተሉ በጋራ ጠየቁ። ተቋማቱ ባወጡት መግለጫ መንግሥታት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ የስደተኞች ብዝበዛን፣ ጾታዊ ጥቃትን፣ የዘፈቀደ እሥራትንና መድልዎን የሚገቱ ስምምነት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።...more0minPlay
December 18, 2025በጋምቤላ ክልል ውጥረት ሰፍኗል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩየጋምቤላ ክልል መንግስት ባወጣው መግለጫ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በክልሉ የጸጥታ ችግር የፈጠሩ አካላትን አድኖ በመያዝ ላይ መሆኑንና በርካቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስረድቷል፡፡ ‹‹ከጸጥታ ኃይሎች ውጪ የትኛውንም የጦር መሳሪያ ይዞ የሚገኝ አካል ላይ የጸጥታ ኃይሎች አስፈላጊውን እርምጃ›› ይወስዳሉም ሲል ገልጿል፡፡...more0minPlay
December 18, 2025ኢትዮጵያ ዉስጥ ታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ፤ የመገናኛ ብዙኀን ነጻነት እንዲከበር ተጠየቀበኢትዮጵያ ዉስጥ ስድስት ጋዜጠኞች ታስረዋል። ሁለት የዶይቼ ቬለ DW ዘጋቢዎች በቋሚነት ከስራ ታግደዋል። ሌሎች በፕሪስ ነጻነት ላይ የጭቆና ድርጊቶችን አይተናል። ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰዉን ማስፈራሪያና ሌሎች ነገሮችን ዘግበናል። ጋዜጠኞች ለባለሥልጣን የማይመቹ ወይም ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን ሲናገሩ በሰፊው የጥቃት ኢላማ አካል ሆነዉ እያየን ነዉ።...more0minPlay
December 18, 2025የምርጫ አስቻይ ኹኔታዎች በኢትዮጵያየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ ማድረግ ይቻላል ለሚላቸው ቦታዎች አረንጓዴ፣ ከጥንቃቄ ጋር ማድረግ የሚቻልባቸው የተባሉትን ቢጫ እና ምርጫ ማድረግ የማይቻልባቸውን በቀይ ቀለማት እንደሚበይን፣ ይህንኑም በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግም ገልጿል። ከመንግሥት መዋቅሮች ጋር ውይይት ያደረገው በዋናነት "በሰላምና ፀጥታ ሁኔታ" ላይ እንደሆነም ጠቅሷል።...more0minPlay
December 18, 2025የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዮ ዞን አጎራባች አካባቢዎች ማህበረሰቦች ግንኙነትበ6 ዓመታት እንደ ሀገር በተፈጠረ የፖለቲካ አለመረጋጋት የተከሰተው ግጭት ለበርከታ ሰዎች የህይወት ማለፍ እና ንብረትመውደም ምክንያት ነበር ያሉት በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ይፍራታ እና ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አበራ መኮነን ከአመራሩ እስከ ህዝብ የነበረው የሰላም መነጋገር ውጤታማ መሆን ችሏል ይላሉ፡፡...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.