Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.
December 16, 2025የፓርቲው የትምህርት ፖሊሲ በትምህርት ሚኒስቴር ተግባራት ውስጥ እየተፈፀመ ነው ፤ ኢዜማኢዜማ በመጪው 7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ እንደሚሳተፍ አቋሙን ለሕዝብ ይፋ ባደረገበትና የዛሬ መግለጫው ትምህርት ሚኒስቴር በሚፈጽማቸው ተግባራት "ያልተገበርነው ይኖራል እንጂ ከተተገበረው ውስጥ የኢዜማ ፖሊሲ ውስጥ የሌለ የለም" ብሏል።...more0minPlay
December 16, 2025የቀጠለው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት እና አዲሱ የሰላም ሐሳብየበራስልሱ ስብሰባ ዩክሬን ጠንካራ ተደራዳሪ ልትሆን በምትችልበት የወታደራዊና የፋይናንስ እርዳታ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ በበርሊኑ ስብሰባ ለመጀመሪያ ግዜ አሚሪካ ፣ ዩክሬንና አውሮፓ በጋራ የሰላም ዕቅድ ላይ እንደተስማሙ ተገልጿል።...more0minPlay
December 16, 2025ከኦፌኮ አመራር አባልነት ወደ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መስመር - ደስታ ዲንቃበኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ (ኦፌኮ) በከፍተኛ አመራርነት ለዓመታት ያገለገሉ ፖለቲከኛ ደስታ ድንቃ ከፓርቲው መውጣታቸውን አረጋገጡ፡፡ ፖለቲከኛው ከሌሎች የትግል አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በሌላ የፖለቲካ ድርጅት ለመምጣት መንገድ ስለመጀመራቸውም ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡...more0minPlay
December 16, 2025ሒውማን ራይትስ ዎች፦ «ዶይቸ ቬለ ላይ የደረሰው ጥቃት ገለልተኛው ፕሬስ ላይ የተደቀነ መጠነ ሰፊ ሥጋት ነው» አለሒውማን ራይትስ ዎች፦ የዶይቸ ቬለ ሁለት ወኪሎች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለ ሥልጣን ለዘለቄታው መታገዳቸውን አወገዘ ። ለ«ኢትዮጵያ መንግሥት» ጥሪ ያስተላለፈው ሒውማን ራይትስ ዎች፦ «በዶይቸ ቬለ ጋዜጠኞች ላይ የጣለውን እገዳ በአስቸኳይ እንዲያነሳ፤ በመገናኛ ብዙኃን ላይ የሚያደርሰውን ተጨማሪ ጥቃት እንዲያቆም» ሲልም ጥሪ አስተላልፏል ።...more0minPlay
December 15, 2025የታኅሣሥ 6 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባበስፔን ላሊጋ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ አሎንሶ ላይ ጫናው በርትቷል ።ዩናይትድ ስቴትስ በቅርቡ በሚከናወነው የዓለም አገር አቋራጭ ፉክክር ለመወዳደር ያመለከተው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን ቪዛ መከልከሉ ተሰምቷል ። ኢትዮጵያዊት እና ኤርትራዊት ብስክሌተኞች ጀርመን በሚገኝ ቡድን ውስጥ በቀጣዩ የጎርጎሪዮሱ ዓመት ለመሰለፍ ፈርመዋል ።...more12minPlay
December 15, 2025በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ክህናቱ እንዴት ተገደሉ?በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ አቅራቢያ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት በሚመለሱበት ወቅት በታጠቁ አካላት ተይዘው ከተወሰዱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን አገልጋዮች መካከል ሁለት ካህናት ተገደሉ፡፡ በእገታው ወቅት ስንጓዝበት የነበርነው የአገረስብከቱ ተሽከርካሪ ላይ ወደ 20 የሚሆኑ የቤተክስቲያን አገልጋዮች ነበሩ።...more4minPlay
December 15, 2025ውጥረት ያልተለየው የአፍሪቃ ቀንድ ወቅታዊ ኹኔታየአፍሪቃ ቀንድ ቁልፍ አልያም ስልታዊ አቀማመጥ ላይ የሚገኝ ነው። ያም ሆኖ ግን ሥር በሰደደ አለመረጋጋት ይታወቃል።ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር ያለው ሆኖ ሳለም የሥራ አጥነትት ምጣኔው ሽቅብ የወጣበት መሆኑ የሚካድ አልሆነም። ቀጣናው መለያው ከዚህም ይሻገራል።...more15minPlay
December 15, 2025በዳሰነች ወረዳ የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዳሰነች ወረዳ መስተዳድር ለሁለተኛ ጊዜ የህዝብ እንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን አስታወቀ። መስተዳድሩ ገደቡን የጣለው በማርበርግ ቫይረስ የአንድ ሰው ህይወት ማለፍን ተከትሎ ነው። ከወረዳው የሚወጡና የሚገቡ የህዝብ መጓጓዣ አገልግሎት ተቋርጧል፤ መጠጥ ቤቶች፣ መዝናኛን ጨምሮ ህዝብ የሚሰበሰብባቸው ሥፍራዎች ተዘግተዋል።...more0minPlay
December 15, 2025የትራምፕ አስተዳደር ከአሜሪካ እንዲወጡ የሚፈልጋቸዉ ኢትዮጵያዉያን ሁኔታየትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ፣ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በጊዜያዊ ጥበቃ ስር ያሉትን ፈቃድ ማገዱን አስታዉቋል።የሃገር ውስጥ ደህንነት ዋና ጸሐፊ እንዳሉት፤ የሃገራቱን ሁኔታ ከገመገምን በኋላና አግባብነት ካላቸው የአሜሪካ መንግስት ተቋሞች ምክክር ካደረግን በኋላ፤ ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ለጊዜያዊ ጥበቃ ሁኔታ ቅድመ ሁኔታዎችን አታሟላም።...more5minPlay
December 15, 202582,000 የቀድሞ ተዋጊዎች በአራት ክልሎች ወደ መደበኛ ኑሮ መቀላቀላቸው ተገለፀ82,000 የቀድሞ ተዋጊዎች በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋርና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ወደ መደበኛ ኑሮ መቀላቀላቸውና ወደ ሕብረተሰቡ እንዲዋሃዱ መደረጉ ተገለፀ። የተመ የልማት መርሐ ግብር እንዳለው የፕሪቴሪያው ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት አካል የሆነው የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ማሕበረሰባቸው የማዋሃዱ ተግባር አሁንም የቀጠለ ነው።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.