Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.
December 06, 2025አሜሪካ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ “ግጭት እንዳይቀሰቀስ መከላከል” ላይ እንድታተኩር የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የብሔራዊ ደሕንነት የፖሊሲ ሰነድ አሳየዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ መካከል “አዲስ ግጭት እንዳይቀሰቀስ መከላከል” ላይ ማተኮር እንዳለባት የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ይፋ ያደረገው የብሔራዊ ደሕንነት ፖሊሲ ሰነድ አሳየ።...more0minPlay
December 06, 2025ኢትዮጵያ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የማርበርግ ቫይረስ የሙከራ ክትባት መስጠት ልትጀምር ነውየአሜሪካው ሳቢን የክትባት ኢንስቲትዩት ከ640 በላይ በሙከራ ላይ የሚገኘውን ሲኤዲስሪ የማርበርግ ክትባት (cAd3-Marburg Vaccine) ወደ ኢትዮጵያ እንደላከ አስታውቋል። ወጪውን የሚሸፍነው በአሜሪካ ጤና ሚኒስቴር ሥር የሚገኘው የባዮ ሜዲካል የላቀ ምርምር እና ልማት ባለሥልጣን (BARDA) ነው።...more0minPlay
December 05, 2025ኢህአፓ ገዢው ፓርቲ እያሳደረ ባለው ጫና ምክንያት በቀጣዩ ምርጫ ላይ የሚኖረውን ተሳትፎ እንደሚገመግም አስታወቀኢህአፓ ገዢው ፓርቲ እያሳደረ ባለው ጫና ምክንያት በቀጣዩ ምርጫ ላይ የሚኖረውን ተሳትፎ እንደሚገመግም አስታወቀ። የፓርቲው ዋና ጸሐፊ ወይዘሪት ሚስጥረስላሴ ታምራት ዛሬ ለዶቼ ቬለ በሰጡት አጭር ቃለምልልስ ፓርቲው ሊያካሂድ አቅዶ የነበረው ህዝባዊ ስብሰባ የገዢው ፓርቲ ባሳደረው ጫና ምክንያት ተስተጓጉሏል።...more0minPlay
December 05, 2025ኮርዶፋን ሌላዋ ኤል ፋሺር የመሆን ሥጋት እንደተጋረጠባት የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ፎልከር ቱርክ አስጠነቀቁየተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ፎልከር ቱርክ በሱዳን ኮርዶፋን በተባባሰው ግጭት ምክንያት የሚፈጸመው ግፍ መበርታቱትን አስጠንቅቀዋል። ኃላፊው “በተፋላሚ ኃይሎች ላይ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉ ሁሉም ሀገራት ውጊያውን ለማቆም እና ግጭቱን የሚያባብሰውን የጦር መሣሪያ አቅርቦት ለመግታት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ” አቅርበዋል።...more0minPlay
December 05, 2025የአማራ ክልላዊ መንግሥት እና የአፋሕድ ሥምምነት ከማስረሻ ሰጤ ያለፈ ነው?በአማራ ክልላዊ መንግሥት እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን በመወከል ማስረሻ ሰጤ የተፈራረሙት “ዘላቂ የሰላም ሥምምነት” ጥያቄ በርትቶበታል። ማስረሻ ሥምምነቱን የፈረሙት አፋሕድ ከአመራርነት እንዳገዳቸው ባሳወቀ በቀናት ልዩነት ነው። የፋኖን እንቅስቃሴ እና የአማራ ክልልን ፖለቲካ የሚከታተሉ አጥኚዎች ሥምምነቱ ከግለሰብ ያለፈ እንዳልሆነ ይተቻሉ።...more0minPlay
December 05, 2025በተራዘመ ግጭት ካለፈው ይልቅ መጭው ጊዜ ያሳስበናል፤ የአማራ ክልል ነዋሪዎችበአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት መራዘሙ ህይወት አስከፊ እንዳ,ደረገባቸው ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ተናገሩ ። በክልሉ የተለያዩ ዞኖች ነዋሪዎች እንደሚሉት ግጭት አስቸኳይ መፍትሔ ካልተበጀለት መጪው ጊዜ አሳሳቢ ነው።...more0minPlay
December 05, 2025"በ11 ዓመቴ ሙዚቃ በደንብ እጫወት ነበር" የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችና አቀናባሪ አሰፋ ዳኜአሰፋ ዳኜ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች ፣ አቀናባሪ እና መምህር ነው። የተለያዩ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ከልጅነቱ አንስቶ መጫወት የሚችል ሲሆን ከኢትዮጵያ ታዋቂ አርቲስቶች ጋርም ሰርቷል። ስራዎቹን ውጭ ሀገር ድረስ የማሳየት እድልም ነበረው።...more0minPlay
December 04, 2025በቀለ መኮንን በሥነ ጥበቡ ዘርፍ ለኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነዉን የፕሮፌሰር ማዕረግን ተቀበሉለአንድ ሥነ-ጥበበኛ በአ.አ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መሰጠት እንደሚችል ማሳያው ማመላከቻው ዳገቱ ምልክቱ ነው በቀለ መኮንን። ያሉትና የመጪዎቹ የሥነ-ጥበብ ልሂቃን ተስፋና ብርታትም ነው።ይህ ለሥነ-ጥበቡ ብቻም ሳይሆን ለሙዚቃውም ፣ ለትያትሩም ነው። ለመሆኑ ግን በሙዚቃ ወይም በትያትርስ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተሰጥቶ ያውቅ ይሆን?...more0minPlay
December 04, 2025የአሜሪካን የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ሚኒሶታ የሚኖሩ ሶማሊያውያንን ማሰር መጀመራቸው ስጋት አሳድሯልበሚኒሶታ ግዛት የስደተኞች ጉዳይ ጠበቃ የሕግ ባለሙያው አቶ ሙሉአለም ጌታቸው፣ እንደሚሉት፣ከ80 እሰከ 100 ሺህ የሚገመቱ ሶማሊያውያን ስደተኞች በሚኖሩባት ሚኒሶታ ግዛት፣ በአሁኑ ሠዓት ሶማሊያውያን ስደተኞች በቁጥጥር ስር መዋል መጀመራቸውን ገልጸዋል። እርምጃው ለኢትዮጵያውን ስደተኞች ጭምር ከባድ ስጋት መሆኑንም አመልክተዋል።...more0minPlay
December 04, 2025መቀሌ ውስጥ የተፈጠረው ምንድነው ?በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ጎልተው መታየታቸውን ተከትሎ ውጥረት ነግሶ መዋሉን የዓይን ምስክሮች ለዶቼ ቬለ ተናገሩ። ጠዋት የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በመክበብ የተጀመረው የክልሉ ታጣቂ ቡድን እንቅስቃሴ በኋላ ላይ ድምጸ ወያኔን ጨምሮ ዋና ዋና የክልሉ ተቋማትን ወደ መቆጣጠር ተሸጋግሯል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.