Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.
December 01, 2025የሩስያ ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም የተነደፈው የአሜሪካን የሰላም እቅድ ሂደት ፣ ተስፋውና የአውሮጳውያን ሚናዩክሬን ከሩስያ ጋር የምታካሂደውን ጦርነት እንድታሸንፍ የሚፈልጉት አውሮጳውያን ባለፈው ሰሞን ጄኔቫ ውስጥ ተሰብስበው ለሰላም እቅዱ የበኩላቸውን ማሻሻያ ከማቅረብ ውጭ የትናንቱን የፍሎሪዳው ንግግር ጨምሮ በአሜሪካን የሰላም እቅዱ ሂደት አልተሳተፉም። ንግግሩ የቀጠለው አውሮጳውያኖች በሌሉበት ነው።...more7minPlay
December 01, 2025የኅዳር 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባቸልሲ በለንደን ደርቢ አርሰናልን ትናንት ነጥብ አስጥሎ ግስጋሴውን ገትቷል ። ሊቨርፑል፣ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በተጋጣሚ ሜዳ ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ በኤቲሐድ ስታዲየሙ ድል ቀንቷቸዋል ። በቡንደስሊጋው ላይፕትሲሽ እና ዶርትሙንድ አንገት ለአንገት ተናንቀዋል ።...more13minPlay
December 01, 2025በዓለም ላይ የሚገኝ የጦር መሳርያ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ የጦር መሳርያ ንግድ ማካሄዱ ተነገረበዓለም ዙርያ የሚገኘዉ የጦር መሳሪያ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ የጦር መሳርያ ንግድን አስመዘገበ። የዓለማችን ትልልቅ የሚባሉት 100 የጦር መሳሪያ አምራቾች ከመሳርያዎች ሽያጭ በጎርጎረሳዉያኑ 2024 ከሚያገኙትን ገቢ በ 5.9 በመቶ መጨመሩን በስቶክሆልም የሚገኘዉ ዓለም አቀፉ የሰላም ምርምር ተቋም (SIPRI) ይፋ ባደረገዉ ዓመታዊ መግለጫ አስታወቀ።...more0minPlay
December 01, 2025የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14 ኛ የሊባኖስ ጉብኝትርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በቱርክ የሦስት ቀናት ጉብኝታቸው በኋላ እስራኤል አጎራባች ወደ በሆነችዉ በሊባኖስ ጉብኝታቸዉን ጀመሩ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትናንት እሁድ መዲና ቤይሩት እንደደረሱ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ዉስጥ የሚገኘዉን የሊባኖስን ህዝብ በጥንካሪ እንዲቆም አበረታተዋል...more0minPlay
December 01, 2025በባቲ እስከ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት የደረሰው ሽምግልና ግጭቱን «እንዳይመለስ» አድርጎ ሸኝቷልበአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ባቲ ወረዳ ከሁለት ዓመታት በላይ ለበቀል ይፈላለግ የነበረ ማህበረሰብ እስከ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት በቆየ የሽምግልና ስረዓት ዕርቅ አወረዱ ። በግጭቱ ምክንያት እርቅ ማውረዳቸውን ለዶቼ ቬለ የገለጹ የማህበረሰቡ ተወካዮች እንዳሉት በህግ ያልቻልነውን በቆየ የሽምግልና እሴታችን ሰላም አውርደናል ብለዋል።...more5minPlay
November 30, 2025ዉይይት፣ የኢትዮጵያ የምርጫ ዝግጅት፣ የተቃዋሚዎች ሥጋትና የሰላም ጥያቄብዙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ኢትዮጵያ ዉስጥ የቀጠሉት ግጭቶች፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የፖለቲካ አለመረጋጋትና ሥርዓተ አልበኝነት ሳይወገዱ ወይም ሳይቃላሉ ምርጫ ማድረግ ያስቸግራል እያሉ ነዉ...more46minPlay
November 29, 2025መፈንቅለ መንግሥት የደጋገማት ጊኒቢሳውባሳለፍነው ረቡዕ ዕለት ነበር ወታደሮች በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው ነው ጊኒቢሳው ውስጥ የመንግሥትን ሥልጣን መቆጣጠራቸውን ይፋ ያደረጉት። ለቀናት በወታደሮቹ ቁጥጥር ሥር የቆዩት የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ትናንት ወደ ጎረቤት ሀገር ሴኔጋል መግባታቸውን የዳካር መንግሥት አረጋግጧል።...more6minPlay
November 29, 2025የአፍሪቃ ሕብረትና የአውሮጳ ሕብረት ጉባኤሉዋንዳ አንጎላ ውስጥ የተካሄደው የአፍሪቃ ሕብረት እና የአውሮጳ ሕብረት ጉባኤ የንግድ ትስስርን ስለማጠናከር እና የስደተኞችን ፍሰት ስለመግታት ለሁለት ቀናት መክሯል።...more8minPlay
November 29, 2025የማርበርግ ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገው ጥረት አጥጋቢ አይደለም፤ ነዋሪዎችበደቡብ ኢትዮጵያ ጂንካ ከተማ የተቀሰቀሰውን የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት ለመግታት ተገቢው የመከላከል ጥረት ባለመኖሩ ስርጭቱ እንዳይስፋፋ ያሰጋናል ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ ። ከጂንካ ከተማ ወደ ደቡብ ዞሞ ዞን ከተሞች ይደረጉ የነበሩ የህዝብ ማጓጓዣ አገልግሎቶች መቋረጣቸውንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።...more7minPlay
November 29, 2025ሩሲያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱን ሂውማን ራይትስ ዎችን አገደችሩሲያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ ትናንት ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለውን የመብት ተሟጋች ድርጅት ሩሲያ “የማይፈለጉ ድርጅቶች”ብላ ከሰየመቻቸው ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ አካቷል።ርምጃው ፤ በሩሲያ ውስጥ የድርጅቱን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ወዲያውኑ የሚያግድ ሲሆን፤ በሩሲያ ውስጥ ካሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር አብሮ መስራትንም ሕገ-ወጥ ያደርጋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.