Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.
November 29, 2025"እዚህ የአበሻ ቀጠሮ የለም" ኢትዮጵያ ውስጥ ያደገችው ኖርዌያዊት ሀኔምናልባት ማህበራዊ ሚዲያ የሚከታተሉ ወጣቶች ሀኔን በምትሰራቸው ቪዲዮዎች ያውቋት ይሆናል። የሮርዌይ ዜጋ ስትሆን አማርኛ ትናገራለች። ከእጇ ላይም የቡና ስኒ አይጠፋም።...more0minPlay
November 28, 2025እንዳይንቀሳቀስ ማዕቀብ የተጣለበትን የሩሲያ ገንዘብ አውሮፓ ከትራምፕ ማስቆም ትችል ይሆን?የሩሲያ እና ዩክሬይንን ጦርነት ለማስቆም በፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር የተዘጋጀው ባለ 28 ነጥብ የሰላም ዕቅድ ለአሜሪካ መንግሥት እና የሀገሪቱን ኩባንያዎች እንዲጠቅም ተደርጎ የተዘጋጀ ነው የሚል ስጋት ጭሯል።...more0minPlay
November 28, 2025ትራምፕ «ከሦስተኛ ዓለም ለሚመጡ ዜጎች ጥገኝነት ተቋርጧል» አሉዩናይትድ ስቴትስ ከሦስተኛ ዓለም ሀገራት ስደተኞችን መቀበል ማቆምዋን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ። ይህ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተያየት የተሰማዉ አንድ አፍጋናዊ ሁለት የአሜሪካ ብሔራዊ ዘቦች ላይ ተኩስ ከፍቶ ካቆሰላቸዉ በኋላ ነዉ። ከኤርትራ፣ ከሶማልያ፣ ሊቢያና የመንን ጨምሮ ከ 19 ሃገራት ስደተኞች የመኖርያ ፈቃዳቸዉ ይመረመራል ተብሏል።...more0minPlay
November 28, 2025የሐንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የሩሲያ ጉብኝትና የዩክሬን ጦርነትን ለማቆም የሚደረገው ጥረትበዩክሬን በመካሔድ ላይ የሚገኘውን ጦርነት ለማቆም የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በተጧጧፈበት በዚህ ወቅት የሐንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የሩሲያ እና የአሜሪካ መሪዎች የሚገናኙበት ስብሰባ በቡዳፔስት እንዲካሔድ ጋብዘዋል። ትራምፕ ያቀረቡት ምክረ ሐሳብ በአሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ዩክሬን እና የአውሮፓ ዲፕሎማቶች ንግግር እየተደረገበት ይገኛል።...more0minPlay
November 28, 2025በመቀሌ ከተማ የተፈጸመው የቦምብ ጥቃት እና የነዋሪው ስጋትጥቃቱ ስማቸው ባልተጠቀሰ የሰላም ጸጥታ የስራ ኃላፊ ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን እንዳልቀረ ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ገልጸዋል። የከተማዋ የሰላም እና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ረዳኸኝ ፍሰሃ በአዲ ሃቂ ክፍል ከተማ «የሽብር ተልዕኮ በተሰጣቸው » ሰዎች የተወረወረው ቦምቡ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም ብለዋል።...more0minPlay
November 28, 2025የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች እና የአሜሪካ የሰላም ሃሳብየሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች በአሜሪካ የቀረበውን የተኩስ አቁም ስምምነት ውድቅ አድርገዋል።ሚሊዮኖችን አደጋ ላይ የጣለው የሱዳንን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማቆም እና የሰብዓዊ ዕርዳታ ተደራሽነትን ለመጨመር ዓለም አቀፋዊ ጫና ቀጥሏል።ተንታኞች ጫናው ተፋላሚ ሀይሎችን በሚረዱ እንደ አረብ ኢመሬቶች ያሉ የውጭ ሀይሎች ላይ ጭምር መሆን እንዳለበት ያሳስባሉ።...more0minPlay
November 27, 2025የጊኒ ቢሳው ወታደራዊ ኽንታ ጀነራል ሆርታ ንታምን በጊዜያዊ ፕሬዝዳንትነት ሰየመበገለልተኛ ወገን አልተረጋገጠም እንጂ ፌርናንዶ ድያስ ትናንት ከመሸ ምርጫውን ማሸነፋቸውን ተናግረው የትናንቱ መፈንቅለ መንግሥት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሽንፈታቸውን ላለመቀበል የፈጠሩት መላ ነው ሲሉ ከሰዋል። መፈንቅለ መንግሥቱንም የተፈበረከ ብለውታል።...more0minPlay
November 27, 2025አፍጋኒስታን ውስጥ ከአሜሪካ ወታደሮች ጋር ተሰልፎ የነበረ አፍጋናዊ ዋሽንግተን ውስጥ ወታደሮች ላይ ጥቃት አደረሰዩናይትድስ ስቴትስ ዋሽንግተን ከተማ ውስጥ በነጩ ቤተ-መንግሥት አቅራቢያ አንድ አፍጋናዊ ተጠርጣሪ ሁለት የብሔራዊ ዘብ አባላት ላይ ተኩሶ ማቁሰሉ ተነግሯል ። ጥቃቱን አደረሰ የተባለው ራማኑላህ ላካናዋል በመባል የሚታወቅ የ29 ዓመት አፍጋናዊው መሆኑ ተገልጧል ። ቃለ መጠይቅ፥...more0minPlay
November 27, 2025የኢትዮጵያንና የጀርመንን የረጅም ጊዜ ወዳጅነት የሚያሳይ ቅርስ ለኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ተበረከተበ 1920 ዎቹ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደርና ልዩ መልዕክተኛ በነበሩት፤ በፍሪዝ ቫይስ እጅ የነበሩ 12 የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች ባለፈዉ ሳምንት ለኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ተቋም ተበርክቷል። ለተቋሙ ከተሰጡት ውድ ቅርሶች ውስጥ ዘውዶች፣ ጋሻዎች፣ ጎራዴ ዝናር ስዕሎች እንዲሁም ከራስ ተፈሪ መኮንን የተበረከቱ ስጦታዎች እንደሚገኙት ተገልጿል።...more0minPlay
November 27, 2025የኢትዮ-ቴሌኮ ገቢ ሲጨምር ትርፉ በውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ምክንያት አሽቆልቁሏልየኢትዮ-ቴሌኮም ገቢ ባለፈው ዓመት 148 ቢሊዮን ብር ቢደርስም መንግሥት ተግባራዊ ያደረገው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ግን ትርፉ በከፍተኛ መጠን እንዲቀንስ አድርጎታል። በሒሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን የተዘጋጀው የፋይናንስ መግለጫ እንደሚለው የኢትዮ-ቴሌኮም “የውጭ ምንዛሪ ኪሳራ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ1825% ጨምሯል።”...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.