Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.
November 25, 2025የጀርመን መራኄ መንግሥት፦ ስለዩክሬን፣ ፕሬዚደንት ትራምፕ ዕቅድ እና አፍሪቃ ምን አሉ?በደቡብ አፍሪቃ ጁሐንስበርግ ከተማ በተካሄደው የቡድን 20 ጉባኤ ማጠቃለያ ላሽ የጀርመን መራኄ-መንግስት ፍሬድሪሽ ሜርትስ ዩናይትድ ስቴትስ ባለ 28 ነጥብ ዕቅድ በሚል ዩክሬንን በሚመለከት ስላቀረበችው የስምምነት ሐሳብ፤ ስለ አውሮጳውያን ምላሽ እና ሌሎች ጉዳዮችም ማብራሪያ ሰጥተዋል ።...more9minPlay
November 25, 20257ኛው የአውሮፓ ህብረትና የአፍሪካ መሪዎች የጋራ ጉባኤ በሉዋንዳ - አንጎላ7ኛው የአውሮፓና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ለሁለት ቀናት በአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ ሲካሄድ ቆይቶ፤ ማምሻውን ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍና የጋራ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። ጉባኤዉ 55 የአፍሪካና 27 የአውሮፓ አገሮች የተሳተፉበት 49 የአገር መሪዎች ተገኝተውበታል።...more4minPlay
November 25, 2025የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ገዢውን የብልጽግና ፓርቲ ለመዋሃድ ወሰነበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው ተቃዋሚው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ቦዴፓ ከገዢው የብልጽግና ፓርቲ ጋር መዋሃድ የሚያስችለውን ውሳኔ አሳለፈ። ፓርቲውን ወክለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር መብራቱ አለሙ ውህደቱ የግለሰቦችን ጥቅም ለማስጠበቅ የተፈጸመ በማለት በይፋ ተቃውመዋል።...more5minPlay
November 24, 2025የኅዳር 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባየሊቨርፑል እና ማንቸስተር ሲቲ ነጥብ መጣል ዕድሉን ያሰፋለት አርሰናል ቶትንሀምን በሰፋ የግብ ልዩነት ድል አድርጓል ። ባዬርን ሙይንሽን ፍራይቡርግን 6 ለ2 አንኮታኩቷል ። እነ ብራድ ፒት፣ ቢዮንሴ እና ጄዚን የመሰሉ የዓለማችን ታዋቂ አርቲስቶች በታደሙበት የላስቬጋሱ አንድ የመኪና ሽቅድምድም የሬድ ቡል አሽከርካሪ ማክስ ፈርሽታፐን አሸንፏል ።...more0minPlay
November 24, 2025በአዉሮጳ ኅብረት ተቃዉሞ የገጠመዉ የአሜሪካ የ 28 ነጥብ የሰላም እቅድዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ሩስያ በዩክሬን የምታካሂደዉን ጦርነት ለማስቆም ያወጣችዉን ባለ 28 ነጥብ የሰላም እቅድ የአዉሮጳ ኅብረት ተቃወመዉ። ኅብረቱ የራሱ ያለዉን የሰላም አማራጮች ይፋ አድርጓል። ዩናይትድ ስቴትስ ከዩክሬይን ይልቅ ከሞስኮ ጋር የበለጠ ወዳጅነት እንዳላትም ይነገራሉ።...more0minPlay
November 24, 2025«ሙስሊሙን ኀብረተሰብ ከትምህርት እና ሀገራዊ ተሳትፎ በማራቅ ዘላቂ ልማት አይኖርም» የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤትሙስሊሙ ኀብረተሰብ ከሃይማኖቱና ከትምህርቱ አንዱን እንዲመርጥ እየተገደደ እንደሆነ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገለፀ። «የኢትዮጵያ ሙስሊም ኀብረተሰብን ከሃይማኖቱ እና ከትምህርቱ አንዱን እንዲመርጥ በማስገደድ ከትምህርት እና ሀገራዊ ተሳትፎ በማራቅ የሚመጣ ዘላቂ ልማት አይኖርም» ሲል መግለጫ አውጥቷል።...more0minPlay
November 24, 2025የደቡብ አፍሪካ እና አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ ያየለበት የቡድን 20 ጉባኤየቡድን 20 ጉባኤ ሲጠናቀቅ በሱዳን፣ ኮንጎ፣ በእስራኤል በጉልበት በተያዙት የፍልስጤም ግዛቶችና በዩክሬን “ፍትኃዊ፣ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ሰላም” እንዲወርድ እንደሚሠሩ መሪዎቹ ቃል ገብተዋል። በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሔደው ጉባኤ የደቡብ አፍሪካ እና የአሜሪካ ውዝግብ ተጭኖታል። የፕሬዝደንትነት ርክክቡ እንደታቀደው አልተካሔደም።...more0minPlay
November 24, 2025የቡለኑ ጥቃት እና የስጋት ዳመና ያጠላበት የመተከል የጸጥታ ኹኔታበቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ ማለዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ተናገሩ።...more0minPlay
November 23, 2025ውይይት፦ ምን ያስተሳስረው ይሆን? ግጭት ኢትዮጵያ እና ጎረቤት አገራትውይይት፦ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከሰተው ግጭት ሱዳን ውስጥ፥ የሱዳኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ነጸብራቁ በጉልኅ ይታያል ። ከፍ ሲል ግብጽ ከወደታች ደግሞ ሶማሊያም በግጭት ውጥረቱ ስማቸው በተደጋጋሚ ይነሳል ። የኢትዮጵያ መንግሥትን ደግፎ በትግራይ ክልል ጦር ያዘመተው የኤርትራ መንግሥት ያኔ ከደገፈው ጋር አሁን ዐይን እና ናጫ ከመሆንም አልፈው ተፋጥጠዋል ።...more0minPlay
November 23, 2025የዩክሬን ጦርነትን ለማቆም የተዘጋጀው አወዛጋቢ ምክረ ሐሳብ ምን ይዟል?በዩክሬን በመካሔድ ላይ የሚገኘውን ጦርነት ለማቆም በቀረበ ምክረ ሐሳብ ላይ ለመወያየት የአሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ብሪታኒያ ባለሥልጣናት ዛሬ እሁድ በጄኔቫ ተገናኝተዋል። ምክረ ሐሳቡ ወደ ሩሲያ ያደላ ነው ቢባልም ለፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መንግሥት ፈታኝ ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉ ጉዳዮችንም ያካተተ ነው።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.