Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.
November 27, 2025ህወሓት ከመጭው ምርጫ በፊት ሕጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት ገለፀበኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲነት የተሰረዘው ሕወሓት ከመጭው ሀገራዊ ምርጫ በፊት ሕጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት አመልክቷል። የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ተግባራዊ እንዲደረግ አደራዳሪ አካላት ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። ፓርቲው ከኤርትራ መንግስት ጋር ይገገናኛል መባሉንም አሉባልታ ሲል አጣጥሎታል።...more0minPlay
November 27, 2025የሱዳንን ጦርነት ያባባሰው የአረብ ኤሜሬት ጦር መሣሪያሱዳን የተባበሩት አረብ ኤሜሬት ለፈጥኖ ደረሽ ኃይሉ የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታቆም ጠየቀች። የአውሮጳ ሕብረት ምክር ቤት አባላትም ይህን ለማስቆም ያለመ ውይይት እያደረጉ መሆኑም ተገልጿል።...more0minPlay
November 26, 2025ለዩክሬን ሩስያ ሰላም ፣አሜሪካን ያረቀቀችውና በኋላም የተሻሻለው እቅድና የአውሮጳ ኅብረት አቋምሩስያ የምትወጋት ዩክሬንና ደጋፊዋ የአውሮጳ ኅብረት፣ ያልተሳተፉበትን ይህን እቅድ ሩስያን የሚሸልም ሲሉ ተቃውመዋል። ኅብረቱ ባቀረበው አማራጭ ካካተታቸው ማሻሻያዎች መካከል የዩክሬን ወታደሮች ቁጥር በእቅዱ ከቀረበው ከፍ እንዲል፣ የዩክሬን የወደፊት የኔቶ አባልነት ጉዳይ ክፍት ሆኖ እንዲቆይ የሚጠይቁት ይገኙበታል።...more0minPlay
November 26, 2025የኢትዮጵያ እና የጀርመን ቢዝነስ ፎረም በበርሊን ተካሔደየኢትዮጵያ እና የጀርመን ኩባንያዎችን ከመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከልማት ድርጅቶች የሚያገናኘው የቢዝነስ ፎረም በበርሊን ተካሒዷል። መርሐ-ግብሩ በታዳሽ ኃይል፣ በግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያ እና በዲጂታላይዜሽን ዘርፎች የተሰማሩ ኩባንያዎች የተጋበዙበት ነው።...more10minPlay
November 26, 2025አዉሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉን፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ «ይፈፀማል» ያሉትን ግድያ በሠልፍ አወገዙበኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በጠራዉ ሰልፍ ላይ የታደሙት ሠልፈኞች እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ አካባባቢዎች «በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ» የሚፈፀመዉን ግድያና ግፍ እስካሁን ማስቆም አልቻለም...more5minPlay
November 26, 2025የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለምን አሳሳቢ ሆነ?የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ፎልከር ቱርክ ሰሞኑን ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።ኮሚሽነሩ እንዳሉት በተለይም ጀነሬቲቭ ኤአይ ቁጥጥር ካልተደረገበት «ራንከንስታይን ሞንስተር» እየተባለ የሚጠራውን እኩይ ወይም በተለምዶ «ጭራቅ» የምንለው አይነት ገፀባህሪ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።...more11minPlay
November 26, 2025"ከሐይሊ ጉቢ የወጣው «አሽ» ውፍረት ያለውና በጣም ብዙ ቦታ እንደሸፈነ ነው"በአፋር ክልል ሐይሊ ጉቢ ያለው የእሳተ ገሞራ እንቅስቃሴ ጋብ ማለቱ ቢገለፅም በአፍዴራ የሚገኙ መንደሮች በአመድ መሸፈናቸውን፤ አመዱም በነዋሪዎች ላይ ሳል ማስከተሉ፤ እንዲሁም እንስሳት የሚበሉት እና የሚጠጡት ነገር እንደሌላቸው ተገልጿል።...more3minPlay
November 25, 2025የተመድ፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቁሙ - ዘመቻበተባበሩት መንግስታት ሴት ድርጅቶች፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የሚቃወም ዘመቻ ጀመሩ። ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን 2024 ዓመት ብቻ ወደ 50,000 የሚሆኑ ሴቶች እና ታዳጊ ሴት ልጆች በወዳጆቻቸዉ አልያም በቤተሰብ አባላት ተገድለዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ መረጃ አዉጥቷል።...more0minPlay
November 25, 2025በኢትዮጵያ ከ12,000 ዓመታት በኋላ የፈነዳው ሐይሊ ጉብ እሳተ ገሞራ በረራ አስተጓጎለበአፋር ክልል ሐይሊ ጉብ እሳተ ገሞራ ከመጨረሻው የበረዶ ዘመን በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲፈነዳ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ድንጋጤ ፈጥሯል። ፍንዳታው ወደ ሰማይ ያጓነው አመድ የኢትዮጵያን ድንበር እና ቀይ ባሕርን ተሻግሮ በሕንድ በረራ አስተጓጉሏል። አመዱ ወደ ሰማይ እስከ 14 ኪሎ ሜትር የሚትጎለጎል ነበር።...more7minPlay
November 25, 2025በሥራቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ባለሙያዎች ተሸለሙበኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ ዲያስፖራ ማኅበረሰብ ውስጥ ውጤታማ አገልግሎት አበርክተዋል የተባሉ ባለሙያዎች፣የዕውቅና ሽልማት አገኙ።በመላው ዓለም ከሚንቀሳቀሰው ''ፒፕል ቱ ፒፕል'' ዕውቅና ያገኙት እነዚህ ባለሙያዎች፣በሥራ አመራር፣በምርምርና በትምህርት የላቁ እንዲሁም አርኣያነት ያላቸው ናቸው ብሏል...more5minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.