Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.
November 21, 2025ወጣቶች ብቃታቸውን እንዴት ማዘመን ይችላሉ?ሰሞኑን ኢትዮጵያው ውስጥ ሥራውን በይፋ አስፋፍቶ የጀመረው "የሙያ ወግ ኢኒሺየቲቭ" ፕሮጀክት በ10 ዓመታት ውስጥ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እና ምስራቅ አፍሪቃውያን ወጣቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሥራ ብቁ ማድረግ ይሻል ። ይኽ ፕሮጀክት ወጣቶችን የማብቃት፣ የማሰልጠን እና የማማከር የመሳሰሉ ድጋፎችን የሚሰጥ ይሆናል።...more11minPlay
November 20, 2025የአውሮጳ ኅብረትና ዩክሬን ያልመከሩበት የአሜሪካ ሩስያ የዩክሬን ጦርነት ማስቆሚያ የሰላም እቅድዩናይትድ ስቴትስ እና ሩስያ የዩክሬኑን ጦርነት ሊያስቆም ይችላል የተባለ የሰላም እቅድ ነድፈዋል።እቅዱ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ በትላልቅ ጉዳዮች ላይ በሰጥቶ መቀበል እንዲስማሙ ጥሪ ያቀርባል። የአውሮጳ ዲፕሎማቶች ግን እቅዱ የአውሮፓ ኅብረትና ዩክሬንን ባልተሳተፉበት የትም አይደርስም ሲሉ ቅሬታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።...more0minPlay
November 20, 2025ጀርመን ኔፈርቲቲን ለግብፅ መመለስ ይኖርባት ይሆን?በምዕራቡ ዓለም ኔፈረቲቲ ዘመናዊነትን በሚያሳዬ የማኅበረሰብ ዝግጅቶች ላይ መቃ አንገትዋን፤ የጫነችዉ ዘዉድን ምልክት እያደረጉ ያቀርቧታል። ኔፈረቲቲ የበርሊን ምልክት መሆንዋን የሚናገሩት ኢትዮጵያዊ የታሪክ ምሁር አንድ ቀን ወደ አገርዋ ወደ ግብፅ መግባትዋ እንደማይቀር ተናግረዋል። በጀርመን የሚገኙ ምሁራንም ይሄ ተስፋ እንዳላቸዉ ተናግረዋል።...more0minPlay
November 20, 2025በኢትዮጵያ ኬንያ እና ሶማሊያ ድርቅ ሊከሰት ይችላል ተባለበኢትዮጵያ ኬንያ እና ሶማሊያ ድርቅ ሊከሰት እንደሚችል የኢጋድ የአየር ትንበያ ማዕከል አስጠነቀቀ።እንደ ትንበያው ከጎርጎሪያኑ ጥር 2026 ድረስ ከመደበኛ በታች የሆነ የዝናብ መጠን የሚጠበቅ በመሆኑ፤ በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ፣ ምስራቃዊ ኬንያ እና ደቡባዊ ሶማሊያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን አደጋ ላይ የሚጥል የከፋ ድርቅ ሊያጋጥም ይችላል።...more0minPlay
November 20, 2025የጸጥታ እና የፖለቲካ ጥያቄዎች መልስ ካላገኙ ቀጣዩ ምርጫ ምርጫ ሊሆን አይችልም፤ ኦፌኮበኢትዮጵያ የፀጥታ እና የፖለቲካ ጥያቄዎች መልስ ካላገኙ ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ምርጫ ሊሆን አይችልም ሲሉ የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተናገሩ ። ፕሮፌሰር መረራ ለዶቼ ቬለ በተለይ እንዳሉት በተለይ በኦሮሚያ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ ከክልሉ መንግስት ጋር መነጋጋር የግድ አስፈላጊ ኾኖ ተገኝቷል።...more0minPlay
November 20, 2025እናት ፓርቲ ከቅንጅት ተሰረዝኩ ሲል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ወቀሰእናት ፓርቲ«ከቅንጅት ተሳትፎ በማግለል የእናት ፓርቲን እንቅስቃሴ መገደብ አይቻልም»ሲል መግለጫ አወጣ። ፓርቲዉ ትናንት ይህን መግለጫ ያወጣዉ፤ ምርጫ ቦርድ የ5 ፓርቲዎች ስብስብ ሆኖ ከተመሰረተዉ ከ«ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» ቅንጅት ዉስጥ ሰርዞኛል ሲል ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ለማነጋገር ያደረግነዉ ጥረት ለዛሬ አልተሳካም።...more0minPlay
November 19, 2025የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዕድል እና ፈተና በአፍሪቃሰውሰራሽ አስተውሎት በዓለም ላይ በፍጥነት እያደገ ያለ ቴክኖሎጂ ነው።ቴክኖሎጂው ትምህርትን ግላዊነት በማላበስ፣ በቂ አገልግሎት ለሌላቸው ተማሪዎች ተደራሽነትን በማሻሻል በአፍሪካ በትምህርት ላይ በጎ ተጽእኖ እያሳደረ ነው።ያም ሆኖ ቴክኖሎጂውፈተናዎችም አሉት።ባለሙያዎች ፈተናዎቹን ለመሻገር ቴክኖሎጂው የሚገዛበት ፖሊሲዎች ማውጣትን ይመክራሉ።...more12minPlay
November 19, 2025ከምርጫ በፊት ሰላም እንዲሰፍን ፣የታሰሩ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ተጠየቀየ5 ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው «ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» የተሰኘው ቅንጅት ከመጭው ምርጫ በፊት የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ሰላም እንዲያሰፍን ጠየቀ። ትብብሩ ያለፈው ሰኞ ባወጣው መግለጫ የታሰሩ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች እንዲፈቱም ጠይቋል። መንግስት ለዚህ ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥም ትብብሩ ቀነ ገደብ አስቀምጧል።...more5minPlay
November 19, 2025የዩናይትድ ስቴትስና የሳዑዲ አረቢያ ግንኙነት ወደ ልዩ ወዳጅነት አደገልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሠልማን ዩናይትድ ስቴትስን ሲጎበኙ ከ7 ዓመት ወዲሕ የመጀመሪያቸዉ ነዉ።ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በመካከለኛዉ ምሥራቅ «ምትክ የሌላቸዉ» መሪ ላሏቸዉ ልዑል ያደረጉት አቀባበልም ልዩ ነዉ።ልዑሉ ራት ተጋበዙ፣ ዋይት ሐዉስ፣ ቀይ ምንጣፍ ተዘረጋ፣ የክብር ዘቡ ተሰለፈ፣ ማርሹ ተንቆረቆረ----...more0minPlay
November 19, 2025የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አምስት ተጨማሪ ኩባንያዎች እያቋቋመ ነውየኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የመማሪያ መጻሕፍት አታሚ ድርጅት እና የወጣቶች የኢንቨስትመንት ባንክ ጨምሮ በዚህ ዓመት አምስት ኩባንያዎች እንደሚያቋቁም አሳውቋል። ከሁለት የሩሲያ ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሥምምነቶች የተፈራረመው ተቋም ከ2011 ጀምሮ የስኳር ፋብሪካዎች ለመሸጥ ሲደረግ የነበረው ጥረት አቋርጧል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.