Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.
November 19, 2025የአሜሪካ ህግ አውጭዎች የጄፌሪ ኤፕስታይን የወሲብ ቅሌት ሰነድ ይፋ እንዲሆን ዉሳኔ አሳለፉአነጋጋሪው የጄፌሪ ኤፕስታይን የወሲብ ቅሌት ሰነድ ይፋ እንዲደረግ የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች እና ሴኔት በአብላጫ ድምፅ ወሰኑ ። የሕግ አውጭዎቹ ባለሥልጣናትን ጨምሮ የታዋቂ ሰዎችን የወሲብ ቅሌት ይዟል የተባለው ሰነድ ይፋ እንዲሆን ድጋፍ ከማግኘቱ በፊት ለዓመታት የዘለቀ ተቋማዊ ክህደት ተፈጽሞበት እንደነበር የጥቃቱ ሰላባዎች ተናግረዋል።...more0minPlay
November 18, 2025ናማታይ ክዌክዌዛ የዘንድሮው የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት አሸናፊናማታኒ ክዌክዌዛ በ18 ዓመቷ ነበር WELEAD TRUST የተባለ ወጣት መሪዎችን የሚያሰለጥንና በፖለቲካ ውሳኔዎች ሂደቶች እንዲሳተፉ የሚሠራ ድርጅት የመሠረተችው።በተባባሰው የዚምባብዌ ጨቋኝ ድባብ ክዌክዌዛ ለሕግ የበላይነትn ለፖለቲካዊ ተሳትፎ ትታገላለች፤ታስራለች፤ቁም ስቅልና የማስፈራሪት ሙከራዎች ደርሰውባታል። ስኬት ዋጋ ያስከፍላል ትላለች።...more0minPlay
November 18, 2025በኮሪያ ጦርነት የተዋጉ ኢትዮጵያዉያን መታሰቢያ በዋሽግተንየዝግጅቱ አስተባባሪ የሆኑት የታሪክ መምህርና የማኀበራዊ ጉዳይ ባለሙያ አቶ ተፈራ ኃይሉ፣የሰሞኑበክብረ በዓል፣እንደ ሻምበል ከተማ ጆባ ሁሉ በኮሪያ ዘመቻ ለተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ምስጋና ለማቅረብ የተዘጋጀ እንደነበር ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።...more0minPlay
November 18, 2025የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ መንግስትና የኤም 23 የሰላም ውልየኮንጎ ዴሞክራቲክ መንግስትና ኤም23 ባለፈው ሀምሌም ከሰላም ምምነት ደርሰው የነበር ቢሆንም ሁለቱም ስምምነቱን ሳያከብሩ ነበር የቆዩት። ያሁኑ ስምምነት በቀጣይ ሊሚደረጉ ድርድሮች መነሻ በመሆን እንድሚያገልግል የታመነ ሲሆን፤ ከበፊቱ ስምምነት የየለየ እንደሆነና ለተግብራዊነቱ የሚሰሩ---...more0minPlay
November 18, 2025የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ጸሐፊ “ምግብ ራሱ የጦር መሣሪያ ሆኗል” ሲሉ ተናገሩበዓለም ዙሪያ በሚካሔዱ ግጭቶች ምግብ እንደ የጦር መሣሪያ ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ጸሀፊ ተናገሩ። በዓለም 673 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች እንደራባቸው ወደ መኝታቸው ይሔዳሉ። ከእነዚህ ውስጥ 307 ሚሊዮን አፍሪካውያን ናቸው። አሚና መሐመድ ዓለም ረሐብን ከማቆም ይልቅ ለወታደራዊ ወጪዎች ትኩረት እንደሰጠ ተችተዋል።...more0minPlay
November 18, 2025የማርበርግ ተሐዋሲ ምንነትና ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄኢትዮጵያ ውስጥ ማርበርግ የተሰኘው ተሐዋሲ መከሰቱን የጤና ሚኒስቴር አረጋግጧል። በዚህ ምክንያትም የሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል። ማርበርግ ተሐዋሲ የኤቦላ ተሐዋሲ ቤተሰብ ከሚባሉት አደገኛና ለሞት ከሚያደርሱ ተሐዋሲያን አንዱ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።...more0minPlay
November 17, 2025ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ ተቃራኒ የአፍሪቃ መርሕለመሆኑ በቅርብ ዓመታት የዘር ማጥፋት ወይም የጦር ወንጀል የተፈፀመዉ ናይጄሪያ ይሆን? ብቻ ዶናልድ ትራምፕ 8 ጦርነት አስቁሜያለሁ ይላሉ፣ትራምፕ እንደ ጠቅላይ አዛዥ የሚያዘምቱት ጦር ሶማሊያን፣ የመንን፣ ኢራንን፣ የቬኑዙዌላ ጠረፍን ይደበድባል አሁን ደጎሞ ናጄሪያ ላይ እየዛቱ ነዉ...more0minPlay
November 17, 2025በደቡብ አፍሪቃ ቢያንስ አምስት ኢትዮጵያዊያን በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ተገደሉቢያንስ 5 ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪቃ ባለፈው ሳምንት በታጣቂዎች ተገድለዋል። በደቡብ አፍሪቃ የተባበሩት የኢትዮጵያውን ማኅበረሰብ ማኅበርና አንድ የማኅበረሰብ አንቂ በጆሀንስበርግ እና አካባቢው እንዲሁም በደርባን ኢትዮጵያውያኑን የገደሉት ወንጀለኞች መሆናቸውን ለዶቼቬለ ተናግረዋል፤ ሌሎች ግድያዎችም ደርሰው ሊሆን ይችላልም ብለዋል።...more0minPlay
November 17, 2025የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የገጠሙት ተግዳሮቶች “አብዛኞቹ ፖለቲካዊ” መሆናቸው ተገለጸየኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሒደት ወደ “የመጨረሻ ምዕራፍ” ቢቃረብም ኦነግ፣ ኦፌኮ፣ መኢአድ፣ ኢሕአፓ እና እናት ፓርቲዎች እየተሳተፉ አይደለም። የትግራይ ሕዝብ እስካሁን በሒደቱ ውክልና እንደሌለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ገልጸዋል። ሒደቱ የገጠሙት ተግዳሮቶች “አብዛኞቹ ፖለቲካዊ” መሆናቸውን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ተናግረዋል።...more0minPlay
November 17, 2025የጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን መታሰቢያ መርሐ ግብርዶቼ ቬለን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ያገለገለው፣የአንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ዜናነህ መኮንን አንደኛ ሙት ዓመት ልዩ መታሰቢያ መርሐግብር አዲስ አበባ ውስጥ ተካሄደ። ''ታላላቆቻችን እናክብር፣ ከቀደሙት ምን እንማር?''፣ በሚል መርህ በተካሄደው የዜናነህ መታሰቢያ መርሐ ግብር ላይ፣ የቀድሞ የሙያ አጋሮቹ እና አድናቂዎቹ ተገኝተዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.