Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.
November 17, 2025የምሥራቅ እና የመካከለኛው አፍሪቃ እና የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጫወታዎችበኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በቀጠለው የምስራቅ እና የመካከለኛው አፍሪቃ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ሻምፒዮና ዋሊያዎቹ የመጀመሪያ የምድብ ጫወታቸውን በድል ጀምረዋል። ኢትዮጵያዊቷ ልቅና አምባው የስፔይን ሶሪአ ከተማ የስምንት ሺ ሜትር የሀገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር አሸንፋለች።...more0minPlay
November 16, 2025ያንዣበበው የጦርነት ስጋት እንዲገታ ...የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፕሪቶሪያ-ደቡብ አፍሪቃ ላይ ግጭትን የማቆም ስምምነት ከተፈራረሙ ባለፈዉ ጥቅምት 23 ሶስኛ ዓመቱን አስቆጥሯል። ሶስቱ ዓመታቱ ብዙዎች እንደሚሉት ሁለቱ ኃይላት በስምምነታቸው መሰረት ግዴታቸውን ያልተወጡበት ወይም ሊወጡ ያልፈለጉበት ሰላምም ግጭት ያልነበረበት ሆኖ ነው ያለፈው።...more0minPlay
November 16, 2025ብሪታኒያ የስደተኞች ቁጥርን ለመቀነስ የጥገኝነት ፖሊሲ ማሻሻያ ማድረጓን አስታወቀችብሪታኒያ የስደተኞች ቁጥርን ለመቀነስ የጥገኝነት ፖሊሲ ማሻሻያ ማድረጓን አስታወቀች...more0minPlay
November 16, 2025በወላጅ እናቱ መሪነት መክሊቱን ያገኘው ወጣት ሙዚቀኛትውልድ እና ዕድገቱ ጅማ ከተማ ነው ። በቅርቡ ኤን ቢ ሲ በተሰኘ የቴሌቬዥን ጣቢያ በሚያሰናዳው የሙዚቃ የተሰጥዖ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ላይ አሸናፊ መሆን ችሏል። የቤት መኪናም ተሸልሟል። ሱራፌል አስቴር ። «እናቴ እንደ እናትም እንደ አባትም ሆና ስላሳደገችኝ በርሷ መጠራትን መረጥኩ» አሸናፊ መሆንም ልዩ ልዩ ስሜት አለው ይላል።...more0minPlay
November 16, 2025የምሥራቅ ኢትዮጵያ የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ዘመቻየምሥራቅ ኢትዮጵያ የጸጥታ ግብረ ኃይል በድሬደዋ፣ በሶማሌ ክልል እና በምሥራቅ ሐረርጌ ሲንቀሳቀሱ ነበር ያላቸውን የኦነግ ሸኔ ያላቸው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው ቡድን 43 አባላት መግደሉን አስታውቋል።...more0minPlay
November 16, 2025በካርቱም ከተማ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት እና የተናፈቀው የተኩስ አቁምየሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም፣ አትባራ እና ኦምዱርማን ላይ ዛሬ አርብ በድሮኖች ጥቃት መፈጸሙን የዐይን እማኞች እና ወታደራዊ መኮንኖች አስታውቀዋል። ጥቃቶቹ የተፈጸሙት አሜሪካን ጨምሮ አራት ሀገራት ብሔራዊ ጦር እና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ለሰብአዊነት ተኩስ እንዲያቆሙ ግፊት እያደረጉ በሚገኝበት ወቅት ነው።...more0minPlay
November 16, 2025የአቢዬ ግዛት ዕጣ ፈንታን ያራዘመው የሁለቱ ሱዳኖች የጸጥታ ኹኔታ አሳስቧልሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በገጠማቸው የውስጥ ቀውስ በይገባኛል በሚወዛገቡባት በነዳጅ ዘይት በበለጸገችው የአቢዬ ግዛት ዕጣ ፈንታ ቁርጡ እንዳይታወቅ ተግዳሮት መፍጠሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመለከተ። የግዛቲቱን ዕጣ ፈንታ ለመመልከት ባለፈው ረቡዕ የተሰባሰበው የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የተከፋፈለ አቋም መያዙ ተሰምቷል።...more0minPlay
November 16, 2025ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል የተባለው የሱዳን ጦርነትበ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደለውና ሚሊዮኖችን ያፈናቀለው የሱዳኑ ጦርነት ሰብዓዊውን ቀውስ እንዳይባባስ አስግቷል። በአሁኑ ጊዜ የተመድ ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ ሲያቀርብ ኳታር ለጦርነቱ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈለግ ጠይቃለች።ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ የተኩስ የተኩስ አቁም ሀሳብ አቅርባለች።...more0minPlay
November 15, 2025የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤልፋሺር ይፈጽማል የሚባለው ግፍበጀርመኑ ዓለም አቀፋዊና እና አካባቢያዊ ጥናቶች ተቋም የሱዳን ጉዳዮች አዋቂ ሀገር አሊ እንደተናገሩት አሁን በአልፋሺር በሚካሄደው ጭፍጨፋ የጭካኔው መጠን በጣም አስደንጋጭ ወደሆነ አዲስ ደረጃ ላይ ደርሷል ። በበቂ ሁኔታ በጋለ ስሜት የማይደግፋቸው፣ ከእነሱ ጋር መቀላቀል የማይፈልግ ወይም ማንኛውንም ተዋጊ የሚያደናቅፍ ሰው አደጋ ላይ ይወድቃል።...more0minPlay
November 15, 2025በኒዠር ዴልታ የነዳጅ ዘይት እጣ ፈንታ«ይህ የኦጎኒ ዘይት በእጁ ብዙ ደም አለው። እርስዎ እኔን ተረድተውኝ ከሆነ አላውቅም ። ይህ የኦጎኒ ዘይት ብዙ ደም አለው። ሕዝባችን ሞቷል፣ ብዙ ሰዎች፣ የኦጎኒዎች ሕይወት ብቻ አይደለም የጠፋው። በተቃውሞው ወቅት ከ4,000 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ታውቃላችሁ፣ ስለዚህ በዚህ ጊዜ የፌዴራል መንግሥት በመጀመሪያ የራሱን ድርሻ መወጣት አለበት። »...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,893 episodes available.