Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,899 episodes available.
November 11, 2025አብዛኛዎቹ ጀርመናውያን ጽንፈኝነትን ይቃወማሉለጥናቱ ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች አብዛኛዎቹ ዴሞክራሲንና ብዝሀነትን በበጎ ነው የሚመለከቱት። የዳሰሳ ጥናቱ ካካተታቸው 70 በመቶው ምንም እንኳን በግለሰቦች ደረጃ ድርቅ ያለ የጽንፈኝነት አመለካከት ያላቸው ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ቢሆንም በጀርመን ቀኝ ጽንፈኝነት እያደገ መሄዱ እንደ አደጋ ነው የሚያዩት።...more0minPlay
November 11, 2025የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ሥራ መዘጋትና መፍትሔዉዉዝግቡ የተነሳዉ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር ያረቀቀዉን በጀት የተቃዋሚዉ የዴሞክራቲክ ፓርቲ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴዎች (ሴናተሮች) አንቀበልም በማለታቸዉ ነበር...more0minPlay
November 11, 2025ወጣት አፍሪቃውያን ከዘንድሮው የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ምን ይጠብቃሉ?በብራዚል ትናንት የተጀመረው 30ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 30)እስከ ህዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም ይዘልቃል። በዚህ የጉባኤ ተሳታፊ የሆኑ አፍሪቃውያን ወጣቶች፤ ለአየር ንብረት ለውጥ ዝቅተኛ ድርሻ ያላት ነገር ግን ዋነኛ የችግሩ ተጠቂ ለሆነችው አፍሪቃ፤ መፍትሄ የሚያመጡ ውሳኔዎችን ይጠብቃሉ።...more0minPlay
November 11, 2025ብሪታኒያ ቤልጅየም ዉስጥ የጸረ ድሮን መሳሪዎችና ባለሙያዎች አሠፈረችወታደራዊው እርዳታ የተሰጠው ባለፈው ሐሙስ ምንጫቸው ከየት እንደሆነ ያልታወቁ ድሮኖች የቤልጅየምን ያየር ትራስንስፖርት ካወኩና በጦር ሰፈሮች ላይም ማንዣበባችው ከተረጋገጠ በኋላ፤ የቤልጅየም መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት መሆኑ ታውቋል።ቀደም ብሎ ጀርመንም እንደዚሁ ወታደራዊ ባለሙያዎችን መሳሪያዎችን ወደ ቤልጅየም መላኳ ተገልጿል።...more0minPlay
November 11, 2025ዓመታዊው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ተከታታይ ጉባኤ በብራዚልበየዓመቱ በተመድ አማካኝነት የአየር ንብረት ለውጥን የሚከታተለው ጉባኤ COP ትናንት ተጀምሯል። የዘንድሮው ጉባኤ COP 30 ሲሆን አስተናጋጇ ተረኛ ሀገር ብራዚል ናት። ጉባኤው የሚካሄደው የሚሊዮኖች መኖሪያ በሆነችው የብራዚሏ ቤለም ከተማ ነው።...more0minPlay
November 11, 2025የጦርነት ድባቡ በነዋሪዎች ላይ የፈጠረው ሥጋትያነጋገርናቸው የክልሉ ነዋሪዎች እንደነገሩን ጦርነት ዳግም ያገረሻል በሚል ስጋት የሸቀጦች ዋጋ አለቅጥ ንሯል፣ ወጣቶች በሕገወጥ መንገድ እየተሰደዱ ነው፣ ወደ መሐል አገር የሚጓዘውም አለቅጥ በዝቷል። ከምንም በላይ ደግሞ ሕዝቡ ተረጋግቶ መኖር እንዳልቻለ ነው የነገሩን።...more0minPlay
November 11, 2025የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአቶ ዳውድ ኢብሳ የጻፈው ደብዳቤ እና አንድምታውየኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ለኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በጻፈው ደብዳቤ ባለፉት ሰኔ 30 እና ሐምሌ 1 ቀን የተደረጉ የብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባዎችን እንደገና እንዲያካሂድ ጠየቀ።...more0minPlay
November 10, 2025ታዋቂው የታሪክ ምሑር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌዴሌቦ ሲታወሱታዋቂውን የታሪክ ምሑር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ ህብረ ብሄራዊ አንድነት እንዲጎለብት የሚያግዙ በርካታ የምርምር ስራዎችን የሰሩ ደፋር ሙህር ሲሉ የሚያውቋቸው ያስታውሷቸዋል።ለሀገራቸው ጥልቅ ፍቅር እንዳላቸው የሚነገርላቸው ፕሮፌሰር ላጲሶ ፤የኢትዮጵያን ታሪክ ከመደብ ትግል አውጥተው በአግባቡ እንዲሰነድ ማድረጋቸውም ተገልጿል።...more0minPlay
November 10, 2025የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዚ ከእስር ተፈቱየአምስት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው ባለፈው መስከረም ላ ሶንት የተባለ እስር ቤት ከወረዱ 20 ቀን የሆናቸው ሳርኮዚ ተለቀው ዛሬ ቤታቸው ገብተዋል። የ70 ዓመቱ ሳርኮዚ በመስከረም የተበየነባቸውን የ5 ዓመት እስር ከጀመሩ ከሳምንታት በኋላ ዛሬ ጠዋት ነበር ከእስር እንዲለቀቁ ለፍርድ ቤቱ ይግባኝ ያሉት። ሳርኮዚ ዛሬ ከእስር የተለቀቁት በገደብ ነው።...more0minPlay
November 10, 2025ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ-ኤርትራ ምድር ሌላ ጦርነት እየተደገሰለት ይሆን?ጦርነቱ የቆመበት 3ኛ ዓመት ሙታን የሚዘከበሩበት፣የሥምምነቱ ገበራዊነቱ የሚገመገምበት፣ለሰላም ፅናት ቃል የሚገባበት በሆነ ነበር።አልሆነም።የዛሬ ሶስት ዓመት አንድ የነበሩት ኃይላት ሁለትም፣ ሶስትም ሆነዉ--- ለመከረኛዉ ሕዝብ የዳግም ግጭት፣ጦርነት ሥጋት፣ ዉንጀላ ዛቻና አፀፋ ዛቻ ሲግቱት ሳምንቱ በሳምንት ተተካ።ከእንግዲሕስ?...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,899 episodes available.