Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.
October 30, 2025በታንዛኒያ አወዛጋቢ ምርጫ ከተደረገ በኋላ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ተስፋፋበታንዛኒያ በተቀሰቀሰ ድኅረ ምርጫ ኹከት እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች እና የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ ምንጮች ተናግረዋል። ትላንት ረቡዕ በታንዛኒያ እና በከፊል ራስ ገዝ በሆነችው ዛንዚባር በተካሔደው ፕሬዝዳንታዊ እና የምክር ቤት አባላት ምርጫ ዋና ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች አልተሳተፉም።...more0minPlay
October 30, 2025ኢዜማ፤ የብልፅግና ፓርቲ ያደርጋል ያለውን የግዳጅ የአባላት ምልመላን አወገዘየብልፅግና ፓርቲ የግዳጅ የፓርቲ አባላት ምልመላ ነፃ እና ፍትሃዊ የፖለቲካ ውድድርን የሚያጠብ እና ዜጎችን ስጋት ላይ የሚጥል ነው ፤ ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፤ኢዜማ ገለፀ። ችግሩን በዳሰሳ ጥናት እና በአንዳንድ አቤቱታዎች ማረጋገጡን ፓርቲው ገልጾ፤ይህ የገዢውፓርቲ ርምጃ የዜጎችን በነፃ የመደራጀት መብት የሚገፍ ነው ብሏል።...more0minPlay
October 30, 2025በዐማራ ክልል ይፈጸማል የተባለ ጥቃትና ኢሰብአዊ ድርጊት በገለተኛ አካል እንዲጣራ ተጠየቀበዐማራ ክልል በንጹሐን ዜጎች ላይ ይፈጸማል ያለውን ጥቃትና ኢሰብአዊ ድርጊት ለማጣራት፣ገለልተኛ አካል እንዲቋቋም፣የዓለም ዓቀፍ የዐማራ ዲያስፖራ ዲፕሎማሲ ግብረ ኃይል ጥሪ አቀረበ። ግብረ ኃይሉ ሰሞኑን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፦ በጉዳዩ ላይ ዓለም አቀፍ ተጠያቂነት ለማምጣት እንዲሠራም ጥሪ አስተላልፏል።...more0minPlay
October 29, 2025በሰውሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ ሀሰተኛ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን እንዴት እንለይ?በሰውሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የሚፈጠሩ ሀሰተኛ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ባለንበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ትልቁ ፈተና ነው።በተለይ ዲፕፌክ የሚባለው ዘዴ ሰዎች ያልተናገሩትን አስመስለው የሚናገሩ፣ያላደረጉትን ድርጊት የሚፈጽሙ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይውላል። ለመሆኑ እነዚህ ይዘቶች ከእውነተኛዎቹ እንዴት መለየት ይቻላል?...more0minPlay
October 29, 2025የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዳሉት “ከ23 ቢሊዮን ዶላር አይበልጥም”?ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ከ23 ቢሊዮን ዶላር እንደማይበልጥ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል። የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የዕዳ ዘላቂነት ትንተና በአንጻሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የተበደሩትን ጨምሮ እስከ ሰኔ 2016 የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ 31.7 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ያሳያል።...more0minPlay
October 29, 2025ጀርመን ውስጥ በርካታ ሴቶች ከቤት ውጪ ደሕንነት አይሰማቸውምከሰሞኑ ጀርመን ውስጥ ይፋ የሆነ ጥናት ጀርመን ውስጥ በርካታ ሴቶች ከቤት ውጪ ደኅንነት እንደማይሰማቸው ያመለክታል። በተለይ እንደ ባቡር ጣቢያ ባሉ የሕዝብ ማመላለሻ ሥፍራዎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ይበልጥ ደኅንነት እንደማይሰማቸው ነው ጥናቱ የገለጸው ።...more0minPlay
October 29, 2025በሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃቶችና ትንኮሳ በመፈጸም የተበየነበት ሀዱሽ ገብረ ሥላሴ ቅባቱ ከብሪታንያ ወደ ኢትዮጵያ ተባረረየብሪታንያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ በስህተት ከታሰረበት ከተለቀቀ፣48 ሰዓታት ከሚጠጋ ጊዜ በኋላ እሁድ ዳግም የታሰረው ተገን ጠያቂው ሀዱሽ ገብረ ሥላሴ ከብሪታንያ ወደ ኢትዮጵያ መባረሩን ዛሬ አስታውቋል። በሌላ በኩል ብሪታንያ በሆቴሎች ውስጥ የምታኖራቸውን ተገን ጠያቂዎች ወደ ቀድሞ ወታደራዊ ጦር ሰፈሮች ለማዛወር ማቀዷን አስታውቃለች።...more0minPlay
October 29, 2025ተቃዋሚዎች ምን አሉ?«አገሪቱን እየፈተነ ያለውንና ምርጫውን ለማካሄድም እንቅፋት ይሆናል ተብሎ የሚሰጋውን የጸጥታ ሁኔታው ወደ ተራ ሽፍትነት አውርደው መግለጻቸው ስህተት ነው፣»...more0minPlay
October 28, 2025“ውጊያው ከተነሳ ውጤቱ ግልጽ ነው። ከዚያ በኋላ እዬዬ አይሠራም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኤርትራ መንግሥት ላይ ደጋግመው ብርቱ ክስ አቅርበዋል። መንግሥታቸው ከማንም ጋር ወደ ግጭት የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ቢናገሩም ውጊያ ቢቀሰቀስ ግን “ማንም አያቆመንም” ብለዋል። በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን ያጣጣሉት ዐቢይ ለህወሓት “ብትዋጉም አታሸንፉም” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።...more0minPlay
October 28, 2025ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ተሸለሙሻለቃ ዳዊት፣በዓለሙ ማኀበረሰብ ዘንድም ዕውቅና የተሰጣቸው ዲፕሎማት እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ከሃገር ከተሰደዱ በኋላ፣በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ስር ያሉ የተለያዩ ተቋማትን በመምራትና በማማከር አገልግሎት ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.