Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.
October 28, 2025ሱዳን ኤልፋሽር ከተማ «ከ2,000 በላይ ያልታጠቁ ሰዎች» ተገደሉየሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ሚሊሻዎች (RSF) በምዕራባዊ የአገሪቱ ክፍል የምትገኘው የኤልፋሸር ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን ዐሳውቀዋል ። የዜና ምንጮች እንደሚሉት፦ ጎሳ ላይ ያነጣጠር ጥቃት ዛሬ በከተማዪቱ ዐይሏል ። በጥይት ተደብድበው ከተገደሉ ከ2,000» በላይ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ሕጻናት እና ሴቶች እንደሆኑም ተዘግቧል ።...more0minPlay
October 27, 2025የ2018 ምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስጋትየእናት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ጌትነት ወርቁ፤ ነገር ግን መንግሥት በሐገሪቱ ሰላም ካስከበረ፤ ጦርነቶች ቆመው፣ የታሰሩት ተፈትተው፣ ያኮረፉት ኃይሎች ጋር የውይይትና የድርድር ሁኔታዎች ከተካሄዱ ምርጫው ሊካሄድ እንደሚችል ተስፋቸውን ይገልጻሉ።...more0minPlay
October 27, 2025ማሕደረ ዜና፣ የASEAN ጉባኤ፣ የትራምፕ ጉብኝትና የሲኖ-አሜሪካ ድርድርየማሌዢያዉ ጠቅላይ ሚንስትር መልዕክት ካንጀት ይሁን ካንገት በርግጥ ማረጋገጪያ የለም።ያሉትን ያሉት ግን ከትብብር ይልቅ ተናጠልነትን፣ ከድርድር በፊት ቅጣትን የሚመርጡ ወይም ሚያራምዱትን፣ የ«አሜሪካ ትቅደም» መርሕን የሚያቀነቅኑት ዶናልድ ትራምፕን ከየትኛዉም እግዳ በላይ ለማስተናገድ ኢብራሒም ጠብ እርግፍ በሚሉበት መሐል ነዉ።...more0minPlay
October 27, 2025የጥቅምት 17 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል ። አርሰናል በአንዲት ብቸኛ ግብ መሪነቱን ከማስጠበቅም በላይ ከተከታዬ በአምስት ነጥብ መራቅ ችሏል ። ለተወሰኑ ጊዜያት የደረጃ ሰንጠረዡን ሲመራ የቆየው ሊቨርሉል የቁልቁለት ሽምጡን ተያይዞታል ።...more14minPlay
October 27, 2025የትራምፕ የእስያ ሀገራት ጉብኝት እና የአለም አቀፍ የኢኮኖሚ ውጥረትን የማርገብ ጥረትየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከትናንት ጀምሮ በእስያ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።ትራምፕ በማሌዢያ የጀመሩትን የእስያ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ጃፓን በማቅናት ነገ ማክሰኞ የሀገሪቱን የመጀመሪያዋን ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ታካይቺን ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።ለመሆኑየብኝቱ ዓላማው ምንድነው?በዚህ ወቅት እስያ ለምን?...more7minPlay
October 27, 2025የካሜሩን ፖለቲካዊ ቀውስየካሜሩን ሕገመንግሥታዊ ምክር ቤት አዛውንቱ ፓል ቢያ በሀገሪቱ በተካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን ዛሬ ይፋ አድርጓል።...more5minPlay
October 26, 2025እንወያይ፤ መንግሥት ለሕዝብ ጥያቄዎች ከምርጫ በፊት መልስ ያገኝላቸዉ ይሆን?የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራ ሊጠናቀቅ የቀረዉ ሦስት ወራት ገደማ ነዉ። ኮሚሽኑ ከህዝብ ያሰባሰባቸዉን ጥያቄዎችና አጀንዳዎች ለመንግሥት ያቀርባል።በሌላ በኩል በያዝነዉ 2018 ዓመት ብሔራዊ ምርጫ መካሄድ ይኖርበታል። ይሁንና መንግሥት ከህዝብ ለተሰበሰቡት አጀንዳዎች ከምርጫ መፊት መልስ ለመስጠት ጊዜና አቅም ይኖረዉ ይሆን?...more0minPlay
October 26, 2025የጅቡቲ ምክር ቤት ፕሬዝደንታዊ ዕጩዎች ላይ የተጣለ የዕድሜ ገደብ እንዲነሳ በድምጽ ደገፈየጅቡቲ ምክር ቤት በሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት ለፕሬዝደንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ላይ የተጣለው የዕድሜ ገደብ እንዲነሳ የቀረበ የውሳኔ-ሐሳብ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ። ውሳኔው ፕሬዝደንት ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ በሚያዝያ 2018 በሚካሔደው ምርጫ ለስድስተኛ የሥልጣን ዘመን በድጋሚ እንዲወዳደሩ መንገድ ከፍቷል።...more0minPlay
October 25, 2025ከ18 ዓመት በታች ስደተኞች የሊቢያና የባሕር ላይ መከራስደተኞችን ከመስጠም አደጋ የሚታደጉ የባሕር ላይ ነፍስ አድን ድርጅቶች የማንቂያ ደውሉን እያሰሙ ነው ። በርካታ ሕጻናት እና ወጣቶች በዓለም ላይ ካሉ አደገኛ የስደት መስመሮች አንዱ የሆነውን የሜዲትራኒያንን ባሕር አቋርጠው እየፈለሱ ነው ። በባሕር ከመስጠም ከተረፉት መካከል አንድ አምስተኛው የሚሆኑት ከ18 ዓመት በታች ናቸው ።...more0minPlay
October 25, 2025የኮትዲቫር ምርጫ እና የዴሞክራሲ ጥያቄ30 ሚሊዮን ነዋሪ ያላት ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ኮትዲቫር ቅዳሜ፤ ጥቅምት 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አካሂዳለች ። ለአራተኛ ጊዜ የተወዳደሩት ፕሬዚደንት አላሳን ዋታራ ያሸንፋሉ የሚል ቅድመ ግምት ተሰጥቷል ። የ83 ዓመቱ አዛውንት የአገሪቱ ፕሬዚደንት አላሳን ዋታራን ጨምሮ አምስት ተፎካካሪዎች ለፕሬዚደንትነት ተፎካክረዋል...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.