Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.
October 22, 2025የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ይዞታ እና የኢትዮጵያና ኤርትራ የቃላት ውዝግብ ያሳደረው ስጋትትግራይ ለጋዜጠኞች አደገኛ መሆኗ ቀጥሏል ሲል ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት CPJ አስታውቋል።CPJ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ አለ ያለውን የፕሬስ ነጻነት ገደብም ሲያወግዝ ቆይቷል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወደ ሌላ ግጭት በመግባት ተጨማሪ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይደርሱ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።...more0minPlay
October 22, 2025ኒኮላ ሳርኮዚ ፤ በፈረንሳይ ታሪክ ዘብጥያ የወረዱ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንትበተፈረደባቸው የ5 ዓመት የእስር ቆይታ በሙሉ ሳርኮዚ ከታሰሩበት ክፍል አጠገብ ሆነው በቋሚነት ሁለት ፖሊሶች እንደሚጠብቋቸው የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ላውረን ኑኔስ ዛሬ ተናግረዋል። የሳርኮዚ የእስር ጊዜ እንዲያጥር ይግባኝ ያሉት ጠበቆቻቸው በአንድ ወር ውስጥ ሊፈቱ ይችላሉ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ።...more0minPlay
October 22, 2025የመንገድ ብልሽት በመተከል ዞንበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ወምበራ ወረዳ፣ ቡሌን እና ድባጢ የተባሉ ወረዳዎች እና ሌሎች አካባቢዎች ጋር የሚያገናኝ መንገድ በመበላሸቱ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሁለት ሳምንት ያህል መስተጓጉሉ ተገለጸ።...more0minPlay
October 22, 2025የዶቼ ቬለ ዲጅታል ጉዞ፤ ከሬዲዮ ሞገዶች ወደ ሳተላይት እና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችከ60 ዓመታት በላይ በአጭር ሞገድ ስርጭቱን ሲያስተላልፍ የቆየው ዶቼ ቤለ ከጥቅምት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የአጭር ሞገድ ሥርጭቱን ያቋርጣል።በምትኩ በሳተላይት እና እንደ ፌስቡክ ፣ዩቱዩብ እና ቴሌግራምን በመሳሰሉ ዲጅታል መድረኮች ስርጭቱን ይቀጥላል።ያም ሆኖ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ላልሆነው የኅብረተሰብ ክፍል ውሳኔው የሚጎዳ ነው ተብሏል።...more0minPlay
October 22, 2025የደወሌው የባቡር አደጋ ያስከተለው ጉዳትባሳለፍነው ሰኞ ሌሊት በድሬደዋ ደወሌ የባቡር መጓጓዣ ላይ በደረሰው አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 15 መሆኑን የድሬደዋ ደወሌ የምድር ባቡር ድርጅት አስታወቀ።...more0minPlay
October 21, 2025በምዕራብ ሸዋ ኖኖ ወረዳ የደረሰው የንጹሃን እልቂት«ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ እሁድ ጥቅምት 09 ቀን 2018 ዓ.ም. ማምሻውን አገር ሰላም ብለው እንደወትሮው ወደ ቤታቸው በገቡ ንጹሃን የኖኖ ወረዳ ሃሎዲንቂ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ነው» የአካባቢው ነዋሪ አስተያየት...more0minPlay
October 21, 2025የገዋኔ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍእንደወረዳው ነዋሪዎች ገለፃ የትናንቱ ተቃውሞ ከሰዓታት በኋላ የተቋረጠው መንገደኞች ሊደርስባቸው የሚችለውን እንግልት ለመቀነስ እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በተደረገ መግባባት ቢሆንም ጥያቄው ካልተፈታ ከቀናት በኋላ በድጋሚ አደባባይ እንወጣለን ይላሉ፡፡...more0minPlay
October 21, 2025ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ የውኃ አያያዝ ዓውደ ጥናትሲምፖዝየሙ ሲጠናቀቅ ፖሊሲ አውጪዎችን፣ ተመራማሪዎችን እና ዲጂታል አበልጻጊወችን በማገናኘት በዳታ የሚመሩ መሳሪያዎችን ተቀባይነት ከማፋጠኑም በላይ በውኃ አስተዳደር ውስጥ ለዲጂታል ለውጥ የሚረዳ አህጉራዊ ፍኖተ ካርታ ይቀርጻል ተብሎ ይጠበቃል ።...more0minPlay
October 21, 2025ተፈጥሮን ተከባካቢዋ የእጽዋት ወዳጅ በኮምቦልቻእያደር የተራቆተና የተበላሸው የአካባቢ ተፈጥሮ ግለሰቦች በሚያደርጉት የየግል አስተዋጽኦ ሊለወጥ ለመቻሉ ማሳያ ይሆናል የኮምቦልቻ ከተማው የአትክልት ስፍራ። በዚህ ስፍራ በየዓመቱ የተለያዩ ችግኞችን እያፈሉ ለኅብረተሰቡ ማቅረብም ሌላው የማይታጎል ሥራ ከሆነ አስር ዓመት አለፈው።...more0minPlay
October 20, 2025በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተባባሰው የትራፊክ አደጋበአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ንጉሴ ሞግስ በዞኑ በተለያዩ ምክንያቶች የትራፊክ አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡ ባለፉት 3 ወራት 33 አደጋዎች መድረሳቸውን የየገለፁት አዛዡ፣ በ82 ሠዎች ላይ ጉዳት ደርሶ 24ቱ ህይወታቸው ሲያልፍ በ34ቱ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.