Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.
October 15, 2025የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስር የውጪ ምንዛሪ ጨረታዎች ምን አሳኩ?የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ከተደረገ ወዲህ ባካሔዳቸው ጨረታዎች ከ690 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለባንኮች አከፋፍሏል። ጨረታዎቹ በትይዩ ገበያ ላይ እርምጃ ሲወሰድ የውጪ ምንዛሪ ገበያውን ማረጋጋት ቢችሉም ዋንኛ ዓላማቸውን ያሳኩ አይመስልም። በመደበኛ እና ትይዩ ገበያዎች የምንዛሪ ተመን ሲጨምር ልዩነታቸው አልጠበበም።...more11minPlay
October 14, 2025የቀጠለው የትግራይ ክልል ኃይሎች ተቃውሞዛሬ ከመቐለ ዓዲግራት የሚወስደውን ጎዳና የዘጉ የትግራይ ኃይሎች ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ጎዳናው እንደዘጉ ነበሩ። ትላንት የግዚያዊ አስተዳደሩፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ የህወሓት ሊ/መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የሠራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች ከተቃዋሚዎቹ የሠራዊት አባላት ጋር ስላካሄዱት ዝግ ስብሰባየተባለ ነገር የለም።...more0minPlay
October 14, 2025የጀርመን ፈጣን የዜግነት ሕግ ለምን ተሰረዘ?የቀደመው የጀርመን መንግሥት በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የውጭ የሰው ኃይልን ለመሳብ አልሞ ነበር ፈጣኑን የዜግነት አሰጣጥ ሕግ ከአንድ ዓመት በፊት ያወጣው። ሕጉ ከወግ አጥባቂዎቹ ቡድን ጠንካራ ተቃውሞ ከተነሳበት በኋላ ሲሰረዝ የውጭ ዜጎች የጀርመን ዜግነት ለማግኘት ጀርመን መኖር ያለባቸው አነስተኛው ጊዜ ወደ አምስት ዓመት ከፍ ብሏል።...more0minPlay
October 14, 2025በደሴ ከተማ በተማሪ ሊዛ ደሳለ ላይ የተፈጸመው ግድያ ያስነሳው ቁጣበወሎ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ክፍል መምህር እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ፣መምህር ሀሊፈት አሊ፣ የሴቶችን ጥቃት በተመለከተ እንደ ሀገር ለብቻው የተዘጋጀ ሕግ ባይኖርም በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ በሚገባ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን ለሴቶች ጥቃት ትኩረት አለመስጠት እና የሴት ልጅን ጥቃት በቸልተኝነት መመልከት እየተለመደ ነው ይላሉ፡፡...more4minPlay
October 14, 2025የኃይል መቋረጥ የፈተናቸው የኮሬ ዞን ነዋሪዎችበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ኬሌ ፣ ጂጆላ ፣ ኬሬዳ እና ዳኖ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች «የኃይል መጥፋት ከአቅማችን በላይ ሆኗል»ሲሉ ለዶቼ ቨለ ተናግረዋል ፡፡ የኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ በአካባቢው የታጠቁ ቡድኖች እንቅስቃሴ በፈጠረው የፀጥታ ሥጋት የኤሌክትሪክ መስመሮችን ለመጠገን አዳጋች ማድረጉን ተናግረዋል ፡፡...more4minPlay
October 14, 2025ግብጽ እና ኢትዮጵያ በዚህ ሰሞን ያደረጉት የቃላት ምልልስየውኃ ምህንድስና መምህሩ እንደሚሉት "እስካሁን ባለው ሁላችንም እንደምናውቀው በውኃ ምክንያት ጦር የተማዘዘ የለም። በዲፕሎማሲ ጠንካራ የሆኑ ሀሳቦች ለመሸናነፍ፣ ድርድሮች፣ ክርክሮች ይኖራሉ። ከዚያም አንዱ በተረዳው መጠን ውጤታማ ይሆናሉ። ስለዚህ የውኃ ሀብቶች፣ የልማት፣ የትብብር፣ አብሮ የማደግ መንፈስ እንጂ የግጭት መንፈስ የላቸውም።...more0minPlay
October 14, 2025የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ብሪታኒያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ያካሄደው ውይይትበምክከሩ የፖለቲካ ፖርቲዎችና ተፉላሚ ኃይሎች ተካፍለዋል ወይ እነሱ ያልተካፈሉበት አገራዊ ምከክር ምን መፍትሄ ያመጣል የሚል ጥያቄም ተነስቷል። በእለቱ ከመወያያው አዳራሽ በር ላይ አያሌ የአማራ ፉኖ ኃይል ደጋፊዎች ጦርነት እየተካሄደ ንፁሀን ዜጎች እየተገደሉ ባለበት ወቅት ውይይቱ ተገቢ እይደለም ሲሉ ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ነበር።...more4minPlay
October 14, 2025በጥቅምት ወር ስለጡት ካንሰር እንነጋገርየጡት ካንሰር በመላው ዓለም በርካታ ሴቶች ላይ የሚከኝ የካንሰር ዓይነት መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት ያመለክታል። ኢትዮጵያ ውስጥ ከዓመት ወደ ዓመት የጡት ካንሰር ታማሚዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የዘርፉ የህክምና ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ለምን ይሆን?...more12minPlay
October 13, 2025የጥቅምት 3 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባለዓለም ዋንጫ እግር ኳስ ጨዋታ ማለፋቸውን ካረጋገጡ የአፍሪቃ አገራት መካከል ጋና አምስተኛ ሁናለች ። ጋና፦ በቀጣዩ የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ አልጀሪያ፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ እና ቱኒዝያን ተቀላቅላለች ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሁነዋል ። የዚህንና የሌሎችን ዝርዝር ከዘገባው ያግኙ ።...more0minPlay
October 13, 2025ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት የቃላት ጦርነት ንሯል።ይዋጉ ይሆን?ሶስቱም ኃይላት የጦር ኃይላቸዉን እያጠናከሩ፣ አዳዲስ ተዋጊ እየመለመሉ መሆናቸዉ እየተዘገበ ነዉ።ሰሞኑን ከአሥመራ የሚናፈሱ መረጃዎች ደግሞ «ለሚፈጠረዉ ቀዉስ ነዳጅ ለመቆጠብ» በሚል የአስመራ የሕዝብ ማመላሻ ተሽከርካሪዎች ሥራ እንዲያቆሙ ታዘዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.