Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.
October 10, 2025በሰሜን ሸዋ ዞን፤ ወራጃርሶ ወረዳ ታጣቂዎች ያደረሱት ጥቃትበኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወራጃርሶ ወረዳ ጊርሚጎባ ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ድንገተኛ ጥቃት የንጹሃን ሕይወት ማለፉ ተመለከተ፡፡ በአከባቢው ታጣቂዎች አዘናግተው አደረሱ በተባለው ጥቃት በርካታ የገበሬ ማኅበሩ ቤቶች መቃጠላቸውና ሰዎች መታገታቸዉና የተዘረፉ ንብረቶችም መኖራቸውን ተጎጂዎች እና የአከባቢው ባለስልጣናት ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል፡፡...more0minPlay
October 10, 2025የልጅነት ልምሻ ክትባት በአማራ ክልልበአማራ ክልል ሁለት ዞኖች የታየውን የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ክስተት ተከትሎ ክልሉ ከ3 ሚሊዮን 500ሺህ በላይ ለሚሆኑ ህፃናት የፖሊዮ ክትባት መሰጠት መጀመሩን የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም አስታወቀ፡፡ ተቋሙ ባለፈው ዓመት ከ4 ሚሊዮን በላይ ህፃናት የፖሊዮ ክትባት መስጠቱን አመልክቷል፡፡...more0minPlay
October 10, 2025ጋና ከአሜሪካ ጋር ያደረገችው ስምምነትና ተቃውሞው«እርምጃው ለኔ ትርጉም አይሰጠኝም። በሁለተኛ ደረጃ ከመልሶች ይልቅ ጥያቄዎችን ያስነሳል። ይህን ዜና ስመለከት ለኔ ቀድሞ የተsሰማኝ ስሜት ዩናይትድ ስቴትስ ችግሮቿን እንደጋና ወደመሳሰሉ ሐገራት እያስተላለፈች ነው የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ። »...more0minPlay
October 10, 2025የአንድ ለአንድ እንግዳችን አቶ ስለሺ ግርማበኢትዮጵያ የቱሪዝም አገልግሎት መስክ ከአፍላ ወጣትነታቸው ጀምሮ ጉልህ ሚና የነበራቸው ናቸው። ከሀገር አስጎብኚነት እስከ የሚንስትር ዴታነትም ደርሰዋል። ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው የአንድ ለአንድ ቆይታ ከአፍላ የወጣትነት ጊዜያቸው ጀምሮ በቱሪዝም ኢትዮጵያ ውስጥ የነበራቸውን ቆይታ በጥቂቱም ቢሆን አካፍለውናል።...more0minPlay
October 10, 2025ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም ለተማሪዎች ጠቃሚ ወይስ ጎጂ?በቅርቡ የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ከፍተው የሚጠቀሙ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያው በመሳብ የትምህርታቸው ትኩረት ያጣሉ በሚል ተማሪዎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ (አካውንት) እንዳይኖራቸው የሚል ሃሳብ አቅርባል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች አቅራቢ ሱመያ ሳሙኤል ከሁለት ታዳጊዎችን አከራክራለች።...more11minPlay
October 09, 2025የግዕዝ ቋንቋ እና ፋይዳዉየሴማዊ ቋንቋዎች አባል የሆነዉ የግዕዝ ቋንቋ፤ የጥንት የሰዉ ልጅ ታሪክን የያዙ መሆናቸዉ ይነገራል። ጀርመንን ጨምሮ በርካታ የአዉሮጳ ሃገራት በግዕዝ ቋንቋ የተፃፉ ጥንታዊ መጻሕፍትን በማገላበጥ ማጥናት ከጀመሩ ዘመናትን አስቆጥረዋል። ጀርመን የግዕዝ ቋንቋን መጠናት የጀመረች የመጀመርያዋ አዉሮጳዊ ሃገር ናት።...more16minPlay
October 09, 2025የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት፣ የኢትዮጵያ ክስ፣ የኤርትራና የሕወሓት መልስ፣ የጎፋ ቅሌትየኢትዮጵያ መንግሥት፣ ኤርትራና ህወሓት ኢትዮጵያን ለመዉጋት እየተዘጋጁ ነዉ ማለቱ እስከ ሳምንቱ ከነበሩት ርዕሶች ሁሉ ከፍተኛ ትኩረት ያገኘ መስሏል።በሁለቱ የወሎ ዞኖች የሚደረገዉ ዉጊያ ማየል እንቅስቃሴ ማጎሉ ተዘግቧል፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ደግሞ በክልሉ በሚደረገዉ ዉጊያ ምክንያት የሰዎች እገታ፣ ዘረፋና ግድያ ማየሉን ጠቅሷል...more9minPlay
October 09, 2025“የአፍሪቃ ቲንከታንክ” ጉባኤየአፍሪቃ አገራት መሰብሰብ ከሚገባቸው ግብር እጅግ ዝቅተኛውን የግብር መጠን ብቻ እንደሚሰበስቡ ተገለጠ ፡፡ ይህም የተነገረው «የአፍሪቃ ቲንክ ታንክ» በሚል ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ መካሄድ በጀመረው 11ኛ ጉባኤ ላይ አህጉሪቱ ውስጥ ለሚታየው አነስተኛ መሰረተልማት አንዱ ምክንያት የግብር አሰባሰብ ድክመት መሆኑ ተገልጧል ።...more4minPlay
October 09, 2025የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተመድ ለየፃፈው ደብዳቤ ህወሓት ምላሽ ሰጠየኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተባበሩት መንግስት ድርጅት የጻፈው ደብዳቤ ከዕውነት የራቀ ነው ሲል ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራት (ህወሓት) ምላሽ ሰጠበት ። ሕወሓት ዝርዝር ምላሹን ያካተተበትን ደብዳቤ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ እና ሌሎች አካላት መላኩም ተዘግቧል ።...more3minPlay
October 09, 2025የኢትዮጵያ ምንዛሪ በአፍሪቃ ደካማ ከሆኑት 21 ገንዘቦች መካከል አንዱ ነው ተባለበጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር በ2025 ከዓለማችን እጅግ ደካማ ገንዘብ ካላቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ 26ኛ ላይ እንደምትገኝ ተዘገበ ። ኢራን ሊባኖስን እና ዚምባብዌን አስከትላ በቀዳሚነት ላይ ትገኛለች ተብሏል ።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.