Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.
October 07, 2025ወሎ ዉስጥ የሚደረገዉ ዉጊያ እንቅስቃሴን አጎለባለፉት 2 ዓመታትበአማራ ክልል በመንግስት እና በፋኖ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት በንግድ ሥራችን ላይ የጎላ ተፅዕኖ አሳድሯል የሚሉት ነጋዴዎች በቅርቡ እያየለ የመጣው ጦርነትሥራችንን ለመስራት አላስቻለንም ይላሉ፡፡...more4minPlay
October 07, 2025የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት መልዕክትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየትበወቅቱ ኦፌኮ "የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሕዝብን አመኔታ እንዲያገኝ በሁሉም ፓርቲዎች ሙሉ ስምምነት ላይ ተመስርቶ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር" ሲል በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ ይህንን እንደ አንድ ቅድመ ሁኔታ አድርጎ አቅርቧል፤ ምንም እንኳን ቦርዱ ይህንን ውድቅ ቢያደርገውም - በገለልተኝነት እየሠራ ያለ ተቋም መሆኑን በመግለጽ።...more4minPlay
October 07, 2025የመንግስት የትኩረት አቅጣጫና የህዝቡ ቀዳሚ ፍላጎትበዚህ ላይ ዶቼ ቬለ ከተለያዩ የአገሪቱ አከባቢዎች ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች የሰላምና ጸትታው ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠውና በተፋላሚ አካላት ሁሉ ለህዝብ ያደላ ውሳኔ የሚተላለፍበትና ስራዎች የሚሰሩበት ዓመት እንዲሆን ተማጽነዋል፡፡...more0minPlay
October 07, 2025ጤናና አካባቢ፤ የአካባቢ በካዮችን ወደ ፍርድ ማቅረብየአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለረዥም ዓመታት በየዕለቱ በሚያወጣቸው የእርድ ተረፈ ምርቶች የአካባቢ ብክለት እየፈጸመ እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎችና እግር ጥሏቸው በአካባቢው በተሽከርካሪም ሆነ በእግር የሚጓዙ የከተማዋ ነዋሪዎች ያማርራሉ።...more11minPlay
October 06, 2025ኢትዮጵያ "ቁልፍ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች" ርእሠ ብሔር ታዬ አጽቀ ሥላሴፕሬዝደንት ታዬ "በየቦታው የሚታዩ ግጭቶችን በኃይል ማስተካከል የሚቻል ቢሆንም" መንግሥት ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሆነ ያምናል ሲሉ ተናግረዋል። መንግሥት አንድነትና ሰላምን ለማጽናት ሕዝባዊ ተቋማትን መገንባት፣ ለሕዝብ የቀረበ እና የታመነ ያሉት አስተዳደርን መዘርጋ ላይ አተኩሮ ይሠራል ብለዋል...more4minPlay
October 06, 2025ማሕደረ ዜና፣ የእስራኤል መጠቃት፣ የጋዛ ጦርነትና ድርድር 2ኛ ዓመትበሚንስቴሩ መዘርዝር መሠረት የጋዛዉ ጦርነት እንደ ሐማስ መሪዎች ሁሉ ከጆናታን ሽታንይበርግ-እስከ ቶሞር ግሪንበርግ ያሉ 6 ኮሎኔሎችን፣ 11 ሌትናት ኮሎኔሎችን፣ ከ70 በላይ ሻለቆችን ጨምሮ እስካለፈዉ ሳምንት ድረስ 913 የእስራኤል ወታደሮችን ሕይወት አጥፍቷል...more15minPlay
October 06, 2025የመስከረም 26 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተደረጉ ፉክክሮች አሸናፊ ሁነዋል ። ባለፉት ሦስት ተከታታይ ግጥሚያዎች ነጥብ የጣለው ሊቨርፑል በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ በቸልሲ በደረሰበት ሽንፈት የደረጃ ሰንጠረዥ መሪነቱን ለአርሰናል አስረክቧል ። ባዬርን ሙይንሽንን እና ግብ አዳኙ አጥቂው ሔሪ ኬንን የሚያስቆማቸው አልተገኘም ።...more11minPlay
October 06, 2025በአማራ ክልል ዋግኸምራ ዞን በርካታ ተማሪዎች አሁንም በዳስ ትምህርት ቤቶች እንደሚማሩ ተገለጸበአማራ ክልል ዋግኸምራ ዞን ውስጥ በርካታ ተማሪዎች አሁንም በዳስ ትምህርት ቤቶች እንደሚማሩ የአካባቢው ባለሥልጣናት ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በዞኑ ዝቋላ ወረዳ አምስት፣ በሰኸላ ሰየምት ወረዳ ሰባት እንዲሁም በጻግብጂ ወረዳ አራት ትምህርት ቤቶች የዳስ ናቸው። የዞኑ ባለሥልጣናት የዳስ ትምህርት ቤቶችን ለመቀየር ርብርብ እናደርጋለን ብለዋል።...more4minPlay
October 06, 2025እንደ ኢሬቻ ያሉ ህዝባዊ በዓላት አገራዊ ፋይዳቸውበቢሾፍቱ በሚገኘው ሆራ አርሰዲ ዓመታዊው የኦሮሞ የምሥጋና በዓል ኢሬቻ ትላንት እሁድ በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል። በተለያዩ ቀለማት ያጌጡ ተሳታፊዎች ባህላዊ ኅብረ ዜማ እያሰሙ በጋራ እየጨፈሩ በዓሉን ሲያከብሩ ታይተዋል። ሥዩም ጌቱ ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች ኢሬቻ ላቅ ያለ ፋይዳ እንዳለው ያስረዳሉ።...more4minPlay
October 06, 2025የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ህወሓትን ለማጥፋት ይደረጋል ያሉትን ሙከራ አወገዙየትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ህወሓትን ለማጥፋት ይደረጋል ያሉትን ሙከራ አወገዙ። ጄኔራል ታደሰ ወረደ ህወሓት “ሊጠፋም ሆነ ሊድን የሚችለው በውስጡና በአባላቱ” እንደሆነ ተናግረዋል። በመቐለ የተካሔደ የትግራይ ሕዝብ ኮንፈረንስ ሲጠናቀቅ በፕሪቶሪያ ሥምምነት መሠረት የህወሓት ሕጋዊ ሰውነት እንዲመለስ ለኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ ቀርቧል...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.