Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.
October 13, 2025ኢሰመኮ የመዘዋወር ነጻነት አደጋ ላይ ወድቋል ሲል ላወጣው መግለጫ የመንግሥት ምላሽኢሰመኮ በአራት ክልሎች ባደረገው ምርመራ «በመንገዶች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች፣ እገታዎች፣ የንብረት ዘረፋዎች እና ውድመቶች የሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት መብት አደጋ ላይ መውደቁን» የጠቀሰበት መግለጫ «ሚዛናዊነት የጎደለው ነው» ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ።...more0minPlay
October 13, 2025በአፋር ክልል የተደጋገመው የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው ጉዳትበራህሌ ወረዳ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በቡሬ እና ዓስጉቢ ቀበሌዎች በርካታ ቤቶች ፈርሰዋል። በአደጋው ዕድሜው 12 ዓመት የሆነ ልጅ ሕይወት ያለፈ ሲሆን ሌሎች ስድስት ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል። በመሬት መንቀጥቀጡ ከ43 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸው ሙሉ በሙሉ ፈርሶባቸዋል።...more0minPlay
October 13, 2025የደሞዝና ሌሎች ጥያቄዎችን ያነሱ የትግራይ ሐይሎች የተቃውሞ ትዕይንት በመቀለየደሞዝ እና ሌሎች ጥያቄዎችን ያነሱ የትግራይ ሐይሎች አባላት ዛሬ በመቐለ የተቃውሞ ትዕይንት እያደረጉ ይገኛሉ። ዛሬ ረፋድ ጀምሮ ከከማው መሀል ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የሚወስደውን መንገድ ጨምሮ በርካታ የመቐለ ከተማ ጎዳናዎች በእነዚህ ተቃውሞ እያሰሙ ባሉ የሠራዊት አባላት ተዘግተዋል።...more0minPlay
October 13, 2025በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ዜጎች ላይ ለሚደርስ ጥቃት ኃላፊነቱን ማን ይውሰድ?ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ሐሙስ ማምሻውን በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሶዶ ዳጪ ወረዳ አከባቢ የሚንቀሳቀሱ የተባሉ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ውስጥ በደፈጣ በመግባት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሕይወት እና የንብረት ጉዳት አድርሰዋል።...more0minPlay
October 12, 2025አሳሳቢው መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት በኢትዮጵያበኢትዮጵያ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት እና በሰዎች የመነገድ ወንጄል ሰፊ እና ውስብስብ ችግር መሆኑን በዘርፉ የሚሰሩ ዓለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ተቋማት ይገልፃሉ።ይህ ችግርም በተለይም ወጣቶችን ሰለባ እያደረገ ሲሆን ፤አንድ ገለልተኛ ዘገባ እንዳመከተው በጅቡቲ በኩል በአማካይ 12,000 ኢትዮጵያውያን በየወሩ ወደ ሳውዲ አረቢያ ይጓዛሉ።...more48minPlay
October 11, 2025የካሜሩን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለ43 ዓመታት ሀገሪቱን የመሩትን የፓል ቢያን ሥልጣን ያራዝም ይሆን ?ፎኩም «በምርጫው ቀን ለመምረጥ መውጣት መቻላችንን መጠየቅ ጀምሬያለሁ፣ሁሉ ነገር ከተዘጋጋ ድምጽ ለመስጠት ወደምርጫ ጣቢያ እንዴት እንሄዳለን» ይላሉ።«የመራጮች ቁጥር በፀጥታ እጦት ካነሰ ምርጫው የተሀድሶ መንገድ ሳይሆን “የይስሙላ” ነው የሚለውን ግንዛቤ ያጠናክራል ፤መራጮች እንቅፋቶችን ከተቃወሙ ግን ያልተጠበቀ ለውጥ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።»...more0minPlay
October 11, 2025ኢትዮጵያ ውስጥ የተጠለሉ ስደተኞች የረሃብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለበኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ለጋሾች የሚሰጡት ገንዘብ በመቀነሱ የረሐብ አደጋ እንደተጋረጠባቸው በተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ መርሐ-ግብር አስጠንቅቋል። ድርጅቱ በበተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚገኙ 27 መጠለያዎች ለሚገኙ 780,000 ስደተኞች የሚሰጠውን የምግብ ርዳታ ከ60 በመቶ ወደ 40 በመቶ ቀንሷል።...more0minPlay
October 11, 2025የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት እና ከኤርትራ ሲወዛገብ እውነተኛ ንግግር እንዲደረግ ከትግራይ ጥሪ ቀረበየትግራይ ሲቪል ድርጅቶች “የፖለቲካ ችግሮች ወደ ከፋ ሁኔታ ሳይሸጋገሩ በውይይት እንዲፈቱ” ጠይቀዋል። ድርጅቶቹ “እውነተኛ ንግግር” እንዲደረግ ጥሪ ያቀረቡት የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓትና ከኤርትራ በኃይል ሲወዛገብ ነው።የሳልሳይ ወያነ ፓርቲ ሊቀ-መንበር የሚመለከታቸው ኃይሎች “ፍላጎታቸውን በኃይል ሳይሆን በንግግር” እንዲያስፈጽሙ ጥሪ አቅርበዋል...more0minPlay
October 11, 2025የዓለም አቀፉ ቀይመስቀል የመድኃኒት ድጋፍበአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከተደረገ ውጊያ በኋላ የከፋ ጉዳት የደረሰባቸውን 16 ቁስለኞች ወደ ሆስፒታሎች ማዘዋወሩን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ገለጸ። በውጊያው “በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ወይም መቁሰላቸውን” አስታውቋል። የድርጅቱ ሠራተኞች ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች መድኃኒት ያደረሱ ሲሆን በእስር ላይ የሚጎኙትን ጎብኝተዋል።...more0minPlay
October 11, 2025ፍልስጤማውያን ወደ ፈራረሱ መኖሪያ ቤቶቻቸው መመለስ ጀመሩበሺሕዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በጦርነት ወደወደሙ መኖሪያ ቤቶቻቸው መመለስ ሲጀምሩ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦቱን ለማሳደግ እየተዘጋጀ ነው። በተኩስ አቁሙ መሠረት ሐማስ 20 እስራኤላውያን ታጋቾች ይለቃል። እስራኤል ባለፉት ሁለት ዓመታት ከጋዛ የተያዙ 1,700 ሰዎች እና 250 የተፈረደባቸው ፍልስጤማውያን ትለቃለች።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.