Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.
September 29, 2025ማሕደረ ዜና፣ የዓለም መሪዎች እየተግባቡ ይሆን ወይስ ግራ እያጋቡበልማዱ፣ ረጅም ጊዜ ባስቆጠረዉ ሥምምነትና አሠራርም የዓለም አቀፉ ድርጅት ዋና መቀመጫ ዩናይትድ ስቴትስ ለጉባኤተኞች ቪዛ መከልክል አልነበረባትም። የትራምፕ አስተዳደር ነባሩን ዉል ጥሷል የሚሉ መንግሥታት የዘንድሮዉ የጉባኤ ሥፍራ ከኒዮርክ ወደ ዤኔቭ እንዲዛወር እስከመጠየቅ ደርሰዉም ነበር።የሰማ እንጂ የተቀበላቸዉ የለም።...more0minPlay
September 29, 2025የመስከረም 19 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባበአውሮጳ ሻምፒዮስን ሊግ ነገ የቱርኩ ጋላታሳራይን የሚገጥመው ሊቨርፑል በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ቀዳሚ ሽንፈቱን አስተናግዷል። በባከነ ሰአት ድል ለተቀዳጀው ተከታዩ አርሰናል የማታ ሲሳይ ሁኖለታል። የአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊው ቦሩስያ ሞይንሽንግላድባህ በአይንትራኅት ፍራንክፉርት ብርቱ ሽንፈት አስተናግዶ የመጨረሻ 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።...more0minPlay
September 29, 2025በሆሮ ጉዱሩ የኦነሰ ታጣቂዎችበኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች ወደ ሰላም መመለሳቸውን ሲል ዞኑ አስታወቀ፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አዛዥ አማካሪ የሆኑት አቶ ጅሬኛ ጉደታ በዚሁ የትጥቅ ትግል አቋርጠው ወደ ሰላም እየተመለሱ ነው ስለተባለው ጉዳይ በዶይቼ ቬለ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡...more0minPlay
September 29, 2025በአማራ ክልል በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተሸለሙየአማራ ክልል መንግሥት በ2017 ዓም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ከ 500 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅናና የገንዘብ ሽልማት ሰጠ፣ በክልሉ ያለው የፀጥታ ችግር የተፈታኝ ተማሪዎችን ቁጥር ከዓመት ወደ ዓመት እንዲቀንስ ማድረጉን ደግሞ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡...more5minPlay
September 28, 2025ከወደቀ ውጤት ባሻገር የቀጣዩ ትውልድ ተስፋ ምን ይሁን ?የትምህርት ሚኒስቴር የዚህ ዓመት የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ዉጤት ይፋ አድርጓል። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በመላው ሀገሪቱ ባለፈው ዓመት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች መካከል 8.4 በመቶው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ውጤት ማግኘታቸውን ይፋ አድርጓል።...more41minPlay
September 28, 2025በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች «ግጭቱ ተባብሷል» ነዋሪዎችዶይቸ ቬለ ያነጋገራቸው የመካነ ሰላም ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ ከትናንት በስትያ አንስቶ የነበረው ውጥረት ዛሬ መቀዛቀዝ ቢያሳይም በዙሪያው ባሉ የገጠር ከተሞች ቀጥሎ እንዳለ ተናግረዋል።...more0minPlay
September 27, 2025የመስቀል በዓል አከባበር በትግራይየመስቀል በዓል ከሀይማኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ይከበራል። በዓሉ በትግራይ ክልል በተለይ በአዲግራት እና በክልሉ ምስራቃዊ ዞን የሚገኙ የኢሮብ ማሕበረሰብ አባላት የመስቀል በዓል በተለየ ሁኔታ የሚያከብሩ ሲሆን፥ ግዕዝም እና ጥሕሎ የመሳሰሉ ልዩ የበዓል ምግቦች በዋነኝነት ለበዓሉይቀርባሉ።...more0minPlay
September 27, 2025የመስቀል በዓል አከባበር እና ትርጓሜው በኦሮሚያ ክልልበክርስትና ሃማኖት በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ትርጉም የሚከበረው የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች እጅግ በሚወደድ ባህላዊ መልኩም በድምቀት ይከበራል፡፡...more0minPlay
September 27, 2025ትኩረት በአፍሪካ፤ የማቻር ፍርድ ቤት መቅረብ፤ ኡጋንዳ 40 ዓመታት በዩዌሪ ሙሰቬኒ ሥርየማቻር ፍርድ ቤት መቅረብ ተጨምሮበት ደቡብ ሱዳንን እንደገና ወደ ግጭት ሊመልሳት ይችላል እየተባለ ነው። ለዛም ነው የሪክ ማቻር የፍርድ ሂደት የእሳቸውና እና የተባባሪዎቻቸው ብቻ ሳይሆን የደቡብ ሱዳን የወደፊት እጣ ፈንታን የሚወስን ነው የሚባለው።...more0minPlay
September 27, 2025በአማራ ክልል የመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰበአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በክረምቱ ወቅት ያስከተለው ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አርሶ አደሮች ተናገሩ። በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ብቻ በበረዶ፣ በጎርፍና በመሬት መንሽራተት 6ሺህ ሄክታር ማሳ መውደሙንና ከ45ሺህ በላይ ቤተሰቦች ለችግር መጋለጣቸውን የወረዳው ግብርና ፅ/ቤት ገልጿል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.