Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.
September 21, 2025ብሪታንያ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በዛሬው ዕለት ለፍልስጤም መንግስትነት በይፋ እውቅና ሰጡብሪታንያ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በዛሬው ዕለት ለፍልስጤም መንግስትነት በይፋ እውቅና ሰጡ። ርምጃውን የፍልስጤም መብት ደጋፊዎች መደበኛ እውቅና ለማግኘት የመጀመሪያው ጥረት ነው ሲሉ፤ በእስራኤል እና በዩናይትድ ስቴትስ ዘንድ ውግዘት አስከትሏል።...more0minPlay
September 21, 2025የኬንያ አትሌቶች በበርሊን ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች አሸነፉበወንዶች የ29 አመቱ ስባስቲያን ሳዌ ያሸነፈ ሲሆን፤ ይህ ውጤት በለንደን ማራቶን ካሸነፈ ከአምስት ወራት በኋላ የተመዘገበ መሆኑ ነው።በሴቶችም ሌኛዋ የሀገሩ ልጅ ሮዝሜሪ ዋንጂሩ ፉክክሩን በአንደኛነት ጨርሳለች።ባለፈው አመት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን በወንዶች ሚልኬሳ መንገሻ፤ በሴቶች ትግስት ከተማ ለኢትዮጵያ ድርብ ድል አስገኝተው ነበር።...more0minPlay
September 20, 2025በጃፓን ያልተሳካው የኢትዮጵያ አትሌቶች ተልዕኮኢትዮጵያ ስትካፈልበት ከሰነበተችው 20ኛው የቶኪዮ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ ሳታገኝ የመጨረሻውን ቀን እየጠበቀች ነው። ዛሬ ኢትዮጵያዉያ ሜዳሊያ ልታገኝ ትችላለች ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የሴቶች የ5000 ሜትር ውድድር ያለ ሜዳሊያ ተጠናቋል።...more5minPlay
September 20, 2025የኢትዮጵያ መንግሥት አራት ጄኔራልነትን ጨምሮ ለ66 ከፍተኛ ወታደራዊ የጦር መኮንኖች ማዕረጎች ሰጠየኢትዮጵያ መንግሥት አራት ጄኔራልነትን ጨምሮ ለ66 ከፍተኛ ወታደራዊ የጦር መኮንኖች ማዕረጎች ሰጠ። ሉቴናንት ጄኔራል አለምሸት ደግፌ፣ ሉቴናንት ጄኔራል ደስታ አብቼ፣ ሉቴናንት ጄኔራል ይመር መኮንን እና ሉቴናንት ጀኔራል ድሪባ መኮንን ሙሉ ጄኔራል ሆነዋል።...more0minPlay
September 20, 2025የሳህል ግዛቶች ህብረት፤ አንድነት ወይስ እኩል ያልሆነ አጋርነት?የማሊ፣ ኒጀር እና የቡርኪናፋሶ መንግሥታ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተገረሱ በኋላ ከሁለት ዓመታት በፊት የተመሰረተዉ የሳህል ግዛቶች ህብረት (AES) በያዘዉ ያልተሟሉ ግቦች እና የኢኮኖሚ ተስፋዎች ብሎም ሚዛናዊ ያልሆኑ ጥቅሞች በማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ ትችቶች ገጥሞታል። ህብረቱ ዛሬ እስከ ምን ድርሶ ይሆን?...more6minPlay
September 20, 2025ስለደካማዉ የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ምን ያዉቃሉ?ደቡብ ሱዳን አዲስ የእርስ በርስ ግጭት አፋፍ ላይ ያለች ይመስላል። ከጎርጎረሳዉያኑ 2018 ጀምሮ በሃገሪቱ የነበረዉን ከፍተኛ የእርስ በእርስ ጦርነት ያስቆመዉ የሰላም ስምምነት በተለይ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር በአገር ክህደት እና በሌሎች ወንጀሎች ከተከሰሱ እና እስር ላይ ከዋሉ በኋላ የሰላም ስምምነቱ ዳመና ያጠላበት ይመስላል።...more7minPlay
September 20, 2025"ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት" የተባለ የአምስት የፖለቲካ ድርጅቶች ቅንጅት በይፋ ተመሠረተለሦስት ዓመት ተኩል በትብብር ሲሠሩ የቆዩ አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ዛሬ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ቅንጅት መሠረቱ። "ኢትዮጵያ የህልውና አደጋ ውስጥ ናት" የሚለው ድምዳሜ የቅንጅቱ መመሥረት ዐቢይ መነሻ ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል።...more3minPlay
September 20, 2025በደቡብ ኢትዮጵያ አሪ ዞን የተከሰተው ጸረ ሰብል ተምች ያስከተለው ስጋትደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ዎባ ኣሪ ወረዳ ለጊዜው “ ምንነቱ ያልታወቀ “ ባሉት ተባይ የአርሻ ማሳቸው መወረሩን አርሶ አደሮች ተናገሩ ፡፡ ተባዩ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘው የሰብሎችን ፈሳሽ በመምጠጥና በማድረቅ መሆኑን የተናገሩት አርሶአደሮቹ ተባዩ ከሳምንት በፊት በአካባቢው ከታየ በኋላ ቀስ በቀስ ወደ መንጋነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል ፡፡...more0minPlay
September 20, 2025በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ በኢትዮጵያ ምን አሉ?ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድን ቀጠና “ሰላም ለማጠናከር ባላት ቁርጠኝነት” እንደተበረታቱ በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቡሎስ ተናገሩ። ቡሎስ ይኸን ያሉት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር በኩል ወደብ ሊኖራት ይገባል በሚል የሚያራምደው አቋም ውጥረት በፈጠረበት ወቅት ነው።...more0minPlay
September 20, 2025የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት ሪየክ ማቻር ጠባቂ እስር ቤት መሞቱን ፓርቲያቸው ገለጸየደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት የነበሩት ሪየክ ማቻር ጠባቂ በእስር ቤት መሞቱን ፓርቲያቸው አረጋገጠ። ሟቹ ወታደር በደቡብ ሱዳን መንግሥት ከታሠሩ 82 የማቻር ጠባቂዎች አንዱ ነበር። ግድያ፣ በመንግሥት ላይ ማሴር እና ሽብርተኝነት የሚሉትን ጨምሮ ስድስት ክሶች የተመሠረተባቸው ማቻር ሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.