Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.
September 09, 2025የነሐሴ በዓላት ማጠናቀቂያ በአማራ ክልልበአማራና አጎራባች ክልሎች በነሀሴ ወር የሚከበሩ ባህላዊ ዝግጅቶች ሳይበረዙና ይዘታቸውን ጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገሩ የፌደራል መንግሥት እንደሚሰራ ስፖርትና ባህል ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በአብዛኛው በአማራ ክልል በልጃገረዶች ዘንድ የሚከበሩ ባህላዊ ጨዋታዎች የማጠቃለያ ዝግጅት ትናንት በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡...more4minPlay
September 09, 2025የኦሮሚያው ግጭት ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሻገርዓመታትን ያስቆጠረው የትጥቅ ትግል አሁንም ድረስ መቋጫ አላገኘም ። አንዴ ውጥረት እያነገሰ ሌላ ጊዜ ረገብ እያለ የቀጠለው የታጣቂዎች እና የመንግስት የጸጥታ አካላት ግጭት ለማህበረሰቡ ሌላ ስጋት ካስከተለ ሰነበተ ። ዕገታ ፤ የዘፈቀደ ግድያ እና ዘረፋ ደግሞ ዋነኞቹ ናቸው ።...more15minPlay
September 09, 2025ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቀቀ ዓላማውን ማሳካት ይቀራልከ233 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በ14 ዓመት ገደማ የተጠናቀቀውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኢንጂነር አሥራት ብርሀኑ “የኢትዮጵያን ክብር የመለሰ፣ አይን ገላጭ” ይሉታል። የውኃ ፖለቲካን የሚያጠኑት ወንድወሰን ሚቻጎ ግድቡ ኢትዮጵያ “የበይ ተመልካች” ሆና የቆየችበትን የዐባይ ወንዝ የውኃ አጠቃቀም ታሪክ የቀየረ ነው የሚል እምነት አላቸው።...more0minPlay
September 08, 2025“የሚታይ የጦርነት ደመና አለ” የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንትየትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ሉቴናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ “የሚታይ የጦርነት ደመና” መኖሩን ተናገሩ። ፕሬዝደንቱ ሥጋታቸውን የገለጹት ለሁለት ቀናት በተካሔደ የትግራይ ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ነው። የስብሰባው ተሳታፊዎች “የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግራይ በኩል ለሚቀርቡ ሕገ-መንግሥታዊ ጥያቄዎች ምላሹ ማስፈራራት ሆኗል” ሲሉ ከሰዋል...more3minPlay
September 08, 2025የኢትዮጵያ የባህር ኃይል ዋና መስሪያ ቤትን የማስመረቅ አንድምታ?ከ33 ዓመታት በኋላ መከላከያ ሠራዊት ያስመረቀውን የባህር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ዋና መሥሪያ ቤት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም አስጠባቂ” ብለውታል፡፡ የመከላከያ ሰራዊት ይፋዊ ማህበራዊ ገጽ “ዳግም ወደ ነበረበት ቀይ ባህር እንደሚመለስ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዋና መስሪያ ቤት ተመረቀ” ሲል ዘግቦታል።...more4minPlay
September 08, 2025ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ዛሬ ጳጉሜን 3 ቀን በአዲስ አበባ ተጀመረዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መፍትሔዎችን ማፋጠንና ለአፍሪካ አረንጓዴ ልማት የፋይናንስ ድጋፍ ማድረግ ላይ ባተኮረው ጉባኤ አሳሳቢነቱ የጨመረው የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ይመክራል። ጀርመንን ወክሎ በጉባኤው የተገኘው ልዑክ የናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል የወንዙን ውኃ ለመጠቀም መግባባት አለባቸው ብለን ስለምናምን ለማዕቀፉ ድጋፍ እናደርጋለን ብሏል።...more4minPlay
September 08, 2025የጳጉሜ 3 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በግብጽ ቡድን 2 ለ0 የተሸነፈው ቡድኑ ላይ በግብፅ ደጋፊዎች የስነስርዓት ጥሰት ተፈጽሟል በሚል ለፊፋ ክስ አቅርቧል ።ል ርቆት በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በመጥፎ ውጤት የጀመረው የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የሰሜን አየርላንድ ቡድንን በማሸነፍ ወደ ድል ተመልሷል ።...more11minPlay
September 07, 2025የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ የተጣለበት ተስፋ እና የተገተረው ድርድርኢትዮጵያውያን በመዋጮ ከደገፉት ታላቁ የህዳሴ ግድብ የተሻለ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይጠብቃሉ። በሀገሪቱ ጥልቅ ፖለቲካዊ ልዩነት ቢበረታም የግድቡ ግንባታ እና ዓላማው ብዙዎችን ያስማማ ነው። ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው፤ ኢንጂነር አሥራት ብርሀኑ እና ወንድወሰን ሚቻጎን ጋብዘን ስለ ታሪካዊው ምዕራፍ፣ ስለ ድርድሩ እና ቀጣዩ የቤት ሥራ አወያይተናል።...more46minPlay
September 06, 2025ሱዳን፦ ከመከራ ወደ ሌላ መከራሱዳን ውስጥ ከሰሞኑ በደረሰ ብርቱ የመሬት መንሸራተት ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል ። እስከ ሐሙስ ድረስ በነበረው ቆጠራ ምዕራብ ሱዳን የዳርፉርል ግዛት ውስጥ በምትገኘው ታራሲን መንደር ከሟቾች መካከል አክሬናቸው የተገኘው የ370 ሰዎች ነው ።...more4minPlay
September 06, 2025ደቡብ አፍሪቃ በግድ «ጥበቃ እንድርግላችሁ ክፈሉን» ባይ ቡድኖች መበራከትያለፍላጎት «ጥበቃ እንድርግላችሁ» የሚሉ አስገዳጅ የገንዘብ ጥያቄዎች በደቡብ አፍሪቃ ካፕሽታድት ከተማ በርካታ የንግድ ተቋማትን ማስጨነቅ ቀጥሏል ። ሁኔታው ላለፉት ዓመታት በመላው ደቡብ አፍሪቃ እየተባባሰ መጥቷል ። እናስ ጸረ-ማስገደድ ጉባኤ ችግሩን ይቀለብስ ይሆን?...more7minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,900 episodes available.