Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.
July 19, 2025አሁን ያለው የኑሮ ውድነት በምን ኹኔታ የሚገለጽ ነው?"ትናንት መርካቶ ሄጄ ዕቃ ገዝቼ ነገ ደግሞ ስሄድ ጨምሮ ነው የሚገኘው። መሠረታዊ ፍላጎቶች እንዳለ ጨምረዋል [ዋጋቸው]። ከሰላሙ አንጻር ነው እንጂ አዲስ አበባ ላይ ኑሮ ውድነቱ ምንም ደስ አይልም"።...more4minPlay
July 19, 2025የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ከኤም 23 አማጺ ቡድን ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራረመበዚህ አመት ተጠናክሮ ብቅ ያለው የኤም 23 አማጺ ቡድን በማዕድን በበለጸገው ምስራቃዊ ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት የጎማ ከተማን ጨምሮ የአካባቢውን በርካታ ከተሞች በቁጥጥሩ ስር ማዋሉን ተከትሎ በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ እና በርዋንዳ መንግስታት መካከል ከፍተኛ ውጥረት እንዲገቡ አድርጓቸዋል።...more0minPlay
July 18, 2025አንድ - ለ - አንድ፤ ከአቶ በቀለ ገርባ ጋርአቶ በቀለ ገርባ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ በኋላ ተፈጥሮ የነበረዉን ረብሻ ተከትሎ በቁጥጥር ስር ዉለዉ ለ 18 ወራቶች እስር ላይ ቆይተዋል። ከእስር እንደወጡ፤ ከእስር እንዲፈቱ ሲጠይቅ በረዉን ማኅበረሰብ ለማመስገን ወደ ዉጭ ወጥተዉ አልተመለሱም። አሜሪካ ሲኖሩ ሦስት ዓመት ሆናቸዉ።«ኦቦ በቀለ የጠፉ? ኢትዮጵያ አልናፈቀቾትም?»ብለናቸዋል።...more16minPlay
July 18, 2025መንግሥት የሠራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለልን ተግባራዊ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሲየሽን ጠየቀየኢትዮጵያ መንግሥት የሠራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እርከንን በሕግ ተግባራዊ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሲየሽን ጠየቀ። ይህ ባለመሆኑ ሠራተኞች ሕይወታቸውን ለመምራት የማያግዝ ዝቅተኛ ደሞዝ እንዲከፈላቸው ከማደረጉም በላይ፣ ለሥራ ማጣት ሥጋትም እንዳጋለጡ ማድረጉ ተገልጿል።...more4minPlay
July 18, 2025በምዕራብ ሸዋ ዞን ጨሊያ ወረዳ የበረታው “የሽፍቶች” ጥቃትበኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ጨሊያ ወረዳ ሶኮሩ ቀበሌ ታጥቀው በአከባቢው ዝርፊያን የሚፈጽሙ “ሽፍቶች” እየገደሉ መሆኑንም የአከባቢው ማህበረሰቦች እና የጭነት አሽከርካሪዎች አማረሩ፡፡ የአከባቢው ነዋሪዎችም ሆነ በዚያ ለሚያልፉ ሁሉ ፈታኝ ነው የተባለው ይህ አከባቢ ላይ የሚፈጸመዉ ወንጀል እልባት ሊበጅለት ይገባል ብለዋል።...more4minPlay
July 18, 2025በባሕር ዳር ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ በከፊል መነሳትከፀጥታ ጋር በተያያዘ በባሕር ዳር ከተማ የሰዓት ገደብ ተጥሎባቸው የነበሩ አንዳንድ የእንቅስቃሴና የንግድ ሥራዎች እገዳው እንደተነሳላቸው የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። አስተያየት ሰጪዎች። እንቅስቃሴዎቹ ቀድሞውንም ቢሆን የቆሙት በነበረው የእንቅስቃሴ ገደቡ ብቻ ሳይሆን ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት መሆኑን ይገልፃሉ።...more5minPlay
July 18, 2025ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: “ ጀማ “ ጠቃሚ ወይስ ጎጂ?ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታዳጊ ወጣቶች “ እገሌ የእኛ ጀማ ናት “ እገሌ የእኛ ጀማ ነው ሲሉ ይደመጣሉ ፡፡ ጀማ በርከት ያሉ ወጣቶች የሚመሠርቱት የህብረት ጓደኝነት ሲሆን ወንዶችም ሴቶችም ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ ተቀጣጥረው ሊገባበዙ ወይንም አብረው የተለያዩ መዝናኛ ሥፍራዎች ሊሄዱ ይችላሉ። “ ጀማ “ ጠቀሜታው ወይስ ጉዳቱ ያመዝናል?...more10minPlay
July 17, 2025በመቀሌ የተካሄደው ዝግ ውይይት፤ አነስተኛ ደሞዝ ያላቸው ሠራተኞች ችግር፣ ትራምፕ ስለ ህዳሴ ግድብ የሰጡት አነጋሪ አስተያየትየኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣናት እና ህወሓት እንዲሁም ከኅብረተሰቡ ተወካዮች ጋር ያካሄዱት ዝግ ውይይት አካሂደዋል፤ አነስተኛ ደሞዝ የሚያገኙ የመንግስት ሠራተኞች በኑሮ ውድነት የሚበሉት እስከማጣት መድረሳቸው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተነግሯል።...more9minPlay
July 17, 2025ምክር ቤት ያጸደቃቸው ሁለት ረቂቅ ሕጎችኢትዮጵያ ውስጥ ጎሳን ወይም የብሔር ማነትን መነሻ አድርጎ የፖለቲካ ፓርቲን መመሥረት እንዲቀር የተጠየቀበት የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ጥያቄው ተቀባይነት ሳያገኝ ፀደቀ።...more4minPlay
July 17, 2025አዲሱ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ፖሊሲ በሩሲያ - ዩክሬን ጦርነት ላይየአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ላይ ያላቸው አቅም የተለወጠ መስሏል። ሰላም ስለማስፈን በአደባባይ ሲናገሩ የከረሙት ትራምፕ ለዩክሬን የጦር መሣሪያ በገፍ ለመላክ፤ በሩሲያ ላይ ደግሞ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ዳርዳር እያሉ ነው። እርምጃቸው የአውሮጳን ድጋፍ አግኝቷል።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.