Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
July 16, 2025ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የትራምፕ አስተያየትና ኢትዮጵያትራምፕ ከሳምንታት በፊት በማህበራዊ መገናኛ አውታር ባጋሩት ጽሑፍ አሜሪካ [የቀድሞው አስተዳደር] ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ በሞኝነት ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰው ነበር። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ግድቡ "እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ካለው ቀንሶ በከፍተኛ ርብርብ የተሠራ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው" ብለው ነበር።...more4minPlay
July 16, 2025ኢትዮጵያ ተስፋ የጣለችበት የካፒታል ገበያ ፍሬ መቼ ይታያል?የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በደረሰበት ምዕራፍ መንግሥት ከፍ ያለ ተስፋ ሰንቋል። ገበያው የግምጃ ቤት ሰነዶች፣ የወጋገን እና የገዳ ባንኮችን አክሲዮኖች መዝግቦ ለሁለተኛ ገበያ አቅርቧል። ባለሙያዎች “ፈጣን ግብይት” እስኪፈጠር መታገስ እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ። ነገር ግን “ቀስ በቀስ እያደገ ካልመጣ ሊሞት ይችላል” የሚል ሥጋትም አለ።...more13minPlay
July 15, 2025«ከታጣቂዎች የሚደረግ ትንኮሳን ከፌዴራል መንግስቱ እንደተደረገ እንቆጥራለን»ጄነራል ታደሰ ወረደበአፋር ካሉ የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች ታጣቂዎች ጋር ያለው ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርግ ጄነራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ። ይሁንና የውክልና ግጭት ለመፍጠር ከተሞከረ ግን ጉዳዮ ከፌደራል መንግስት ጋር ነው የሚሆነው ብለዋል። ህወሓትም በበኩሉ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አውጥቶት በነበረ መግለጫ የፌደራሉ መንግስቱን ከሷል።...more3minPlay
July 15, 2025ስደተኞችን በሜዴትራንያን ባህር ከመስጠም ለሚታደጉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ እንዲቆም መወሰኑ ያስነሳው ተቃውሞየጀርመን ጥምር መንግስት ስደተኞችን ከሜዴትራንያን ባህር ለሚታደጉ ድርጅቶች የሚሰጠውን የፋይናንስ ድጋፍ ሊያቋርጥ መሆኑ ጀርመን ውስጥ ተቃውሞ ገጥሞታል። በዚህ ስራ የተሰማሩ ልዩ ልዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ከ2 ዓመት በፊት የ 2ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ዘንድሮም ወደ 900 ሺህ ዩሮ ድጋፍ አግኝተዋል። ከአሁን በኋ ግን ድጋፍ የመስጠቱ ይቆማል።...more9minPlay
July 15, 2025“አዲሱ የደመወዝ ገቢ ግብር ረቂቅ የኑሮ ጫናን ያገናዝብ” የሰራተኞች ኮንፌዴሬሽንበምክር ቤቱ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አዘጋጅነት የቀረበው ረቂቁ ግብር የሚቆረጥበት የደመወዝ መነሻ ከዚህ በፊት ከነበረው 600 ብር ወደ 2000 ብር ከፍ እንዲል ሃሳብ ያቀረበ ቢሆንም በበርካቶች እይታ ግን አመርቂ አለሆነም፡፡...more4minPlay
July 15, 2025በደቡብ ጎንደር ዞን በድርቅ ምክንያት ከ175ሺህ በላይ ሠዎች እርዳታ ይፈልጋሉበአማራ ክልል በደቡብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች በድርቅ ምክንያት ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ነዋሪዎቹ ተናገሩ። የደቡብ ጎንደር ዞን አደጋ መከላክልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት በዞኑ በሚገኙ 7 ወረዳዎች በሚገኙ 57 ቀበሌዎች 175ሺህ በላይ ወገኖች ለድርቅ መጋለጣቸውን አመልክቷል ።...more4minPlay
July 15, 2025ድምፅ አልባዎቹ ገዳይ በሽታዎችምልክት ሳያሳዩና ሳየሰሙ ለከፋ የጤና ጉዳት አልፎም እስከ ሕልፈተ ሕይወት የሚያደርሱ በሽታዎች በህክምናው ዘርፍ ዘ ሳይለንት ኪለርስ በመባል ይታወቃሉ። ይህን ለመከላከል የህክምና አገልግሎት ባለበት አካባቢ የሚኖሩ ወገኖች ቢቻል በዓመት ሁለት ጊዜ ካልሆነም አንዴ የጤና ምርመራ ቢያደርጉ ይመከራል።...more11minPlay
July 15, 2025MSF በትግራይ ክልል ስለተገደሉ ባልደረቦቹ አሟሟት ያወጣዉ ምርመራድንበር የለሽ ሐኪሞች ድርጅት የተባለዉ ግብረ ሠናይ ድርጅት የዛሬ አራት ዓመት ትግራይ ክልል ዉስጥ ሆነ ተብሎ ስለተገደሉ ሦስት ባልደረቦቹ አሟሟት ያደረገዉን የዉስጥ ምርመራ ዉጤት ዛሬ በይፋ አሰራጨ። ሰዎቹ ከቅርብ ርቀት በተተኮሰ ጥይት መገደላቸዉን መኪናቸዉም በጥይት መበሳሳቱን ባወጣዉ ምርመራ አስታዉቋል።...more0minPlay
July 15, 2025ሰሜን እና ደቡብ ወሎ አዲስ ያገረሸው ግጭት እና የአርሶአደሮች ስጋትበአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል እንደ አዲስ በክረምቱ መግቢያ ጊዜ ያገረሸዉ ጦርነት የእርሻ ስራችን ተረጋግተን እንዳንሰራ አድርጎናል ሲሉ አርሶደሮች ስጋታቸውን ገለጹ።አርሶደሮቹ ከዘር ወቅት እስከ አጨዳ ባለዉ ጊዜ ጦርነቱ እየፈጠረብን ባለዉ ተፅኖ ተገቢዉን ምርት ማግኘት አልቻልንም ብለዋል።...more4minPlay
July 15, 2025የሠራተኞች ማሕበራት በገቢ ግብር ማሻሻያ ዙሪያ ለመንግሥት ጠንካራ መከራከሪያ አቀረቡየኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ትናንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ በተደረገ ውይይት ላይ እንዳሉት "ሠራተኛው በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም"።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.