Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
July 12, 2025በተቃዋሚዎች ላይ የአዕምሮ መታወክ ያስከተለው የኬንያ ተቃዉሞ እና የዛምቢያ የሳይበር ህግ ድጋፍ እና ተቃዉሞለተቃዉሞ አደባባይ የወጡ እና ለፖሊስ የጭካኔ ጥቃት የተጋለጡ ኬንያዉያን ተቃዋሚዎች ለከፋ የአዕምሮ መታወክ እየተጋለጡ ነው። ጠበቅ ያለ የሳይበር ደህንነት ህግን ተግባራዊ ያደረጉት የዛምብያው ፕሬዚዳንት በድጋፍ እና ተቃዉሞ መሃል ናቸው...more11minPlay
July 12, 2025በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ሥደተኞች ጋምቤላ ክልል ገቡበዚህ ሳምንት ማዕከላዊ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፈንድ Central Emergency Response Fund (CERF) 3 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለደቡብ ሱዳን ሰደተኞች፣ ለነፍስ አድንና ሰደተኞቹ ለሚኖሩባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ጭምር ለጤናና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት የሚውል ገንዛብ መመደቡን አመልክቷል፡፡...more4minPlay
July 11, 2025ኢትዮጵያና ሩሲያ የብርና የሩብል የቀጥታ የምንዛሪ ልዉዉጥ ማድረግ ጀመሩማዕከላዊ ባንኩ ዛሬ ሃምሌ 04 ቀን 2017 ዓ.ም. ማለዳውን ይፋ ባደረገው መረጃም ባንኩ የሩሲያ ሩብል ከብር አኳያ ያለውን ዋጋ ተምኖ አስቀምጧል፡፡ በዚህም ለ100 የኢትዮጵያ ብር 57.58 ሩብል ወይም ለ1 ብር 0.57 ሩብል የምንዛሬ ተመን አስቀምጧል።...more4minPlay
July 11, 2025አንድ-ለ-አንድ መጋቤ ብሉይ አብርሀም ሃይማኖት የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር ጋርኢሕአፓ ከሀገር ከወጣ በኋላ የተለያዩ አንጃዎች ተፈጥረዋል። ከመካከላቸው በውጭ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ የቀረበውን ጥሪ በመቀበል ወደ ሀገር ቤት የገባው የኢሕአፓ ቡድን ከዛሬ 6 ዓመት አንስቶ እየተንቀሳቀሰ ነው። መርኁም ሶሻል ዴሞክራሲ ነው። መጋቤ ብሊይ አብርሀም ሃይማኖት የፓርቲው ተቃዳሚ ምክትል ሊ/መንበር ናቸው።...more16minPlay
July 11, 2025የትግራይ ክልል የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ወደ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ልትልክ ነዉየሃይማኖት አባቶቹ ትላንት በሰጡት መግለጫ በተለይም ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው አለመመለሳቸው ተከትሎ በከፋ ሁኔታ ይገኛሉ ያሉ ሲሆን፥ ለዚህ መፍትሔ መሰጠት ሲገባው ከዚህ በተቃራኒ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር በቅርቡ በፖርላማ ቀርበው ትግራይን አስመልክተው የሰጡት ማብራሪያ ግን ስጋት የሚፈጥር ሲሉ በጋራ መግለጫቸው አስታውቀዋል።...more3minPlay
July 11, 2025"ተንከራታች ህልሞች" በናትናኤል መኩሪያናትናኤል መኩሪያ ከሀገር ከወጣ 16 ዓመት ሆኖታል። በተለይ አውሮፓ እስኪገባ በፈጀበት የሶስት ዓመት ጉዞው የገጠሙትን የስደት ህይወቶች በመፅሀፉ አስፍሯል። ይህንንም መፅሀፍ በሳምንቱ መጨረሻ እዚህ ጀርመን ሀገር ላይ አስመርቋል።...more10minPlay
July 10, 2025አዶዬ - የጅማ ፍቅር - ከጠይብ አባፎጊ ጋርአቶ ጠይብ አባፎጊ ይባላሉ፤ ከወራቶች በፊት በአፋን ኦሮሞ ለአንባቢያን ያቀረቡት እና «አዶዬ» በሚል የጅማ ማኅበረሰብ ባህል እና የአኗኗር ዘይቤን ያሳዩበት የልብ ወለድ መጽሐፋቸዉ ታዋቂነትን አስገኝቶላቸዋል። በጅማ ቡናን ለመጠጣት ብቻ ሳይሆን ለመድሃኒትነት ፤ በባህላዊ ሥነ-ስርአት እና ክንዉኖች ላይ ጥቅም ላይ እንደሚዉል ጠይብ ተናግረዋል።...more14minPlay
July 10, 2025የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና የአምስት የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤባንድ-ወይም በሁለቱም ምክንያቶች ባልተጠበቀዉ ጉባኤ የተካፈሉት የጋቦን፣ የጊኒ-ቢሳዉ፣ የላይቤሪያ፣ የሞሮታኒያና የሴኔጋል መሪዎች ናቸዉ።የትራምፕ መስተዳድር የብዙ የአፍሪቃ ሐገራት ዜጎች አሜሪካ እንዳይገቡ አግዷል።ዩናይትድ ስቴትስ በUSAID በኩል የምትሰጠዉ ርዳታ በመቋረጡም ሁሉም ሐገራት ተጎድተዋል...more6minPlay
July 10, 2025ያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ «ገጸ በረከትነቱ ቀርቶ ሸክም መሆኑ በቀረልን »ግንባታው ተጀምሮ ለአስራ አራት ዓመታት ገደማ ቆሞ የቀረው የያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ ሃገራዊ ፋይዳው ቀርቶ ከተተከለበት አካባቢ ማህበረሰብ ትከሻ በወረደ ይላሉ ነዋሪዎች እና የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ። በካሳ የእርሻ መሬታቸውን የለቀቁ አርሶ አደሮች አሁን በተመሰቃቀለ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ ነዋሪዎች እና የመስተዳድር አካላት አረጋግጠዋል።...more5minPlay
July 10, 2025የሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም፤ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝትበአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን 380,000 ወገኖች የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል መባሉን፤ ህወሐት ከፌደራል መንግስት ጋር የቀጠለው አታካሮን ተከትሎ በተሰጠ የሕዝብ አስተያየት እንዲሁም የኢዜማ መሬ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ «የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም ልዩነት አያግድም» ማለታቸውን ተንተርሰው የተንሸራረሩ ሐሳቦች እናቀርባለን...more9minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.