Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
July 10, 2025ሱዳን ድንበር (አል ፋሽጋ) የመንግሥት ምላሽየኢትዮጵያ ኃይሎች አል ፋሽጋን ከሱዳን ጦር መልሰው ስለመቆጣጠራቸው ማረጋገጫ የተጠየቀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር «በመንግሥት በኩል የተለየ እንቅስቃሴ የለም» ሲል ምላሽ ሰጠ ።...more4minPlay
July 10, 2025የኢትዮጵያ ቡና የውጪ ገቢ እመርታበ2017 ዓ.ም. የምርት ዘመን ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ምርት 2.65 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አሳወቀ። እንደ ባለሥልጣኑ ማብራሪያ አምና ከቡና የወጪ ንግድ ከተገኘው 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር አኳያ የዘንድሮ 2017 ዓ.ም. ገቢው በ1.2 ቢሊዮን ዶላር ያህል ብልጫ አለው።...more4minPlay
July 10, 2025የአውሮጳ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርዙላ ፎንደርላይን የመተማመኛ ድምፁ አገኙየአውሮጳ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርዙላ ፎንደርላይን በሀላፊነት ለመቆየት የሚያስችላቸውን ከፍተኛ የመተማመኛ ድምፅ አገኙ። በህብረቱ ምክር ቤት በሚገኝበት በሽትራዝ ቡርግ ላይ ዛሬ በተካሄደዉ የድምፅ አሰጣጥ 175 አባላት ክሱን ትክክል ሲሉ፤ 360 አባላት ክሱን ዉድቅ አድርገዉታል። 18 አባላት ደግሞ ምርጫዉን በድምፀ ታዕቅቦ አልፈዉታል።...more0minPlay
July 10, 2025አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን የምትሰጠውን ጊዜያዊ ቪዛ ለሦስት ወራት የሚቆይ እና የአንድ ጊዜ መግቢያ ብቻ እንዲሆን አደረገችበአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ስደተኛ ላልሆኑ እና ወደ ዩናይትድ ስቴት መጓዝ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ጊዜያዊ ቪዛ የሶስት ወራት ብቻ እንደሚሆን አስታወቀ። በዚህ የአጭር ጊዜ ቪዛ ኢትዮጵያውያን ወደ አሜሪካ መግባት የሚችሉት አንድ ጊዜ ብቻ እንደሚሆን ኤምባሲው ዛሬ ሐሙስ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።...more0minPlay
July 09, 2025ስለኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ውዝግብ የሕዝብ አስተያየት ከመቀሌዶቼቬለ ያነጋገርናቸው አንድ የመቐለ ከተማ ነዋሪ፥ "አሁን ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ሰው ስጋት ውስጥ አስገብቶታል። ማቀድ አትችልም፣ ስረህ መስራት አትችልም።ምክንያቱ ከዛሬ ነገር ምን ይሆናል የሚለው አታውቅም። ጦርነት ይነሳል የሚል ስጋት ውስጥ ነው ያለነው። ኑሮም ተወዷል" ብለዋል። ሌሎች በርካቶችም ተመሳሳይ ሐሳብ ይሰጣሉ።...more3minPlay
July 09, 2025ማይቻርጅ፤ ዲጅታል የፖወር ባንክ ኪራይ በአዲስ አበባበጉዞ ላይ ወይም በሌሎች የስራ አጋጣሚዎች መንገድ ላይ እያሉ የተንቀሳቃሽ ስልከዎ ባትሪ ጨርሶ በድንገት ዘግቶበዎት ያውቃል? በአደጉ ሀገራት ያለ ሰው እገዛ ዲጅታል በሆነ መንገድ የሚከናወን የፖወር ባንክ ኪራይ መፍትሄ ይሰጣል። ይህ ዲጅታል መፍትሄ በቅርቡ በኢትዮጵያም ተጀምሯል።...more14minPlay
July 09, 2025የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባኦነግ ባለፉት 50 ዓመታት ባከናወናቸው የፖለቲካ ትግሎች በርካታ ድሎች መገኘታቸውን ገልጾ ዛሬም ድረስ ግን ህዝቡ ሙሉ ነጻነት እንዳልተጎናጸፈ እንደሚያምን አስታውቋል። በፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት ምክንያት ዛሬም መታሰርና መሳደድ እንዳለ የገለጸው ኦንግ፤ ባለፉት7 ዓመታትም ችግሮችን በንግግር ወደመፍታት መሻገር አለመቻሉን ገምግሜያለሁ ብሏል፡፡...more4minPlay
July 09, 2025በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው የወባ በሽታበአሁኑ ጊዜ የበሽታው ሥርጭት ምጣኔ 61 በመቶ ላይ እንደሚገኝ ሃላፊው አሃዛዊ መረጃዎችን በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡ በሽታውን አስቀድሞ ለመከላከል ቀደምሲል ጀምሮ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን የጠቀሱት ሃላፊው እንደክልል በ870 ሺህ 390 ካሬ ሜትር ላይ የወባ ትንኝ ማራቢያ የሆነ ያቆረ ውሃን የማፋሰስ ስራ መከናወኑን አስረድተዋል ፡፡...more4minPlay
July 09, 2025የእርሻ ማሳዎች መራራቅ የሚያስከትለው የጊዜ ብክነትና የገንዘብ ወጪበውይይቱ እንደተገለጸው አንድ አርሶ አደር በኪሎሜትሮች የሚራራቁ በርካታ ማሳዎችን ይዞ ይገኛል፡፡ ማሳዎቹ በዚህ መልክ መያዛቸው የጊዜና የገንዘብ ወጪን እንደሚያስከትል፣ በቅድመ ድህረ ምርትና ድህረ ምርት ወቅት የምርት ብክነትን እንደሚያስከትል በግብርና ሚኒስቴር የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ክፍል የሕግ ባለሙያው አቶ አበባው አበበ ተናግረዋል፡፡...more4minPlay
July 09, 2025ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ከያዮ እና ድሬዳዋ በዳንጎቴ ኢንቨስትመንት ፊቷን ወደ ጎዴ አዞረችሜቴክ በያዮ የጀመረው የማዳበሪያ ፋብሪካ ኢትዮጵያን በቢሊዮን ብሮች አክስሮ ገበሬ አስለቅሶ ቆሟል። በሞሮኮ ኦሲፒ ኩባንያ በድሬዳዋ ሊገነባ የታቀደው ከወረቀት አልዘለለም። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በሶማሌ ክልል በምትገኘው ጎዴ ከተፈጥሮ ጋዝ ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ተስፋውን በናይጄሪያዊው ባለጠጋ አሊኮ ዳንጎቴ ላይ አሳርፏል።...more10minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.