Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
July 08, 2025ተጽእኖ ፈጣሪ ሶማሊያውያን ከጀርመን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚያሰራጩዋታቸው ጽንፈኛ መልዕክቶችእንደ ዶቼቬለ እና ARD የምርመራ ዘገባ አዩብ በቪድዮው «ጠመንጃችሁን አንስታችሁ ተዋጉ »የሚል ጥሪ አቅርቧል። ከልምዴ ብሎ ተዋጊዎች ጠላቶችን ከርቀት ለማየት እንዲችሉ ከፍ ያለ ህንጻ እንዲወጡ ይመክራል። «መንገድ ላይ ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሰ ማንንም ሰው ካያችሁ ተኩሱ ወደ ህንጻ ጣሪያ እንዳትወጡ የሚከለክሏቸው ሰዎችም ላይ ተኩሱ»ብሏል።...more10minPlay
July 08, 2025ስለመጭዉ የኢትዮጵያ 2018 ምርጫ ኦፌኮ የሰጠዉ ገለጻበኢትዮጵያ በ2018 ዓመት የሚያካሂደዉ 7ኛው ብሔራዊ ምርጫ በጠባብ የፖለቲካ ምህዳርና በሁለት የአገሪቱ ክልሎች በሚስተዋለዉ ግጭት ሊፈተን ይችላል ሲል የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አስታወቀ፡፡ ኦፌኮ ይህን ያለዉ በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የልዑካን ቡድንን አዲስ አበባ በሚገኘዉ ዋና ጽ/ ቤቱ ዉስጥ ባነጋገረበት ወቅት ነው፡፡...more4minPlay
July 08, 2025ደቡብ ወሎ ዞን 380 ሺህ ህዝብ የምግብ ድጋፍ ይፈልጋል ተባለየበልግ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመጣሉ ምክንያት በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን 380 ሺህ የህብረተሰብ ክፍል የምግብ ድጋፍ ይፈልጋል ተባለ። በዝናብ እጥረቱ ምክንያት በዞኑ የሚገኙ እንስሶች ላይ የመኖ እጥረት አጋጥሞል። ደሴ ዙሪያ፣ ኩታበር፣ ለጋምቦ፣ መቅደላ፣ ተንታ፣ አምባሰል፣ ደላንታ ወረዳዎች ናቸዉ የዝናብ እጥረት ያጋጠማቸዉ።...more4minPlay
July 08, 202517 ኛዉ የብሪክስ ጉባኤ - ትራምፕ የብሪክስ ጥምረትን ለምን ፈሩት?ሪዮ ዲ ጄኒሮ ብራዚል ለሁለት ቀናት ለጉባኤ የተቀመጠዉ የብሪክስ ስብስብ ለትራምፕ የኤኮኖሚ ፖሊሲ ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል። ጥምረቱ እንደ ቻይና ያሉ አገራትን ቢያካትትም እስካሁን እምብዛም ስኬት አላመጣም። በ17ኛዉ የብሪክስ ጉባኤ የቻይናና የሩሲያ መሪዎች በአካል አልተገኙም፤ የኢራንና ግብጽ መሪዎች ደሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው ተወክለዋል።...more5minPlay
July 08, 2025ህወሓትን 'ሕገወጥ እና ኃላቀር' ያለዉ አዲሱ 'ስምረት' ፓርቲበቅርቡ የተመሰረተው በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው 'ስምረት' ፓርቲ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በትግራይ ባለው 'ሕገወጥ ቡድን' ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ። ይህ ቡድን ከኤርትራ ጋር በመተባበር፥ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ለመክፈል ዝግጅቱ ጨርሶ ይገኛል ሲልም የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ፓርቲ ከሷል።...more4minPlay
July 08, 2025«መሰናክሎችን በማስወገድ ድልድዮችን መገንባት» የዓለም የመገናኛ ብዙኃን መድረክ ተጠናቀቀበዓለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የሄደውን የፖለቲካ አለመረጋጋት በተጨባጭ መረጃ በተደገፈ የሚዲያ ስራ ሚዛን መጠበቅ እንደሚገባ ተጠየቀ። ዶቼ ቬለ ያዘጋጀው እና ከበርካታ የዓለም ሃገራት የተጋበዙ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ለሁለት ቀናት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተጠናቋል።...more5minPlay
July 07, 2025የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጥሪበተሳሳተ ድምዳሜ ትግራይ ላይ ጦርነት እንዳይጀመር ጥንቃቄ ያስፈልጋል ሲሉ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ። አሁን ላይ አፋር ክልል ያሉ ከተባሉ የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች ታጣቂዎች ጋርም ልዩነቶች በሰላም ለመፍታት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር እንደሚሰራ ገልፀዋል።...more4minPlay
July 07, 2025ደቡብ አፍሪቃ፤ በፖሊስ በተተኮስ ጥይት ከ 10 በላይ ኢትዮጵያዉያን ጉዳት ደረሰባቸዉየህክምና ዋስትና የሌላቸዉ በደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለመዉለድ ሆስፒታል የሄዱ ነፍሰጡር እህቶቻችን፤ ዘመዶቻችን በመጤ ጠል ሆስፒታል እንዳይገቡ ተከለከሉ ሲሉ አማረሩ። በደርባን ከተማ ሆስፒታል በራፍ ላይ ለመግባት የሞከሩት ነፍሰጡሮች በመከልከላቸዉ የተቆጡ ከአስር የሚበልጡ ኢትዮጵያዉያን በፖሊስ በተተኮሰ የጎማ ጥይት ቆሰለዋል።...more5minPlay
July 07, 2025የምርጫ ቦርድ ተሿሚዎችን ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት የሚያግደው ረቂቅ ሕግየምርጫ ቦርድ ተሿሚዎች ሥራ በለቀቁ 5 ዓመት ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አባልም ሆነ አመራር እንዳይሆኑ የሚገድብ ሕግ ቀረበ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ አመራሮች ሥራ በለቀቁ በ አምስት ዓመታት ውስጥ በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ወይም አመራር እንዳይሆኑ የሚያደርግ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ለውይይት ቀረበ።...more4minPlay
July 07, 2025የሰኔ 30 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባየሊቨርፑል ኮከብ አጥቂ ዲዬጎ ጆታ ባለፈው ሳምንት በመኪና አደጋ ከወንድሙ ጋር ሕይወቱ ማለፉ በደጋፊዎቹ ዘንድ የፈጠረው ድንጋጤና ሐዘን እንደቀጠለ ነው ። በፊፋ የቡድኖች የዓለም ዋንጫ ፉክክር የጀርመን ቡድኖች ከሩብ ፍጻሜው ሲሰናበቱ፤ ጃማል ሙሳይላ ብርቱ ጉዳት ደርሶበታል ። ከተደረገለት ቀዶ ሕክምናው እስኪያገግም አንድ ወር ይፈጃል ተብሏል ።...more9minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.