Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
July 07, 2025የአማራ ልማት ማሕበር (አልማ) እና የልማት እንቅስቃሴውየአማራ ልማት ማህበር ባለፉት 5 ዓመታት በክልሉ ከ2ሺህ 950 በላይ የመማሪያ ክፍሎች መገንባቱን አስታውቋል። ማህበሩ ባለፉት 32 ዓመታት ከ10 ቢሊዮን 800 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ያሰባሰበ ሲሆን፣ አልማ 4 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ መደበኛ አባላት እንዳሉትም ታውቋል፡፡...more4minPlay
July 07, 2025ማሕደረ ዜና፣ የጋዛ ተኩስ አቁም ተስፋ፣ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ዕዉነታመካከለኛዉ ምሥራቅ ዉስጥ ባሉት በ19 የጦር ሠፈሮች 40 ሺሕ የአሜሪካ ወታደሮች ሠፍረዋል።ዩናይትድ ስቴትስና ተባባሪዎችዋ ከ2003 ጀምሮ ኢራቅንና ሊቢያን በቀጥታ ወርረዉ፣ ሶሪያን በተዘዋዋሪ አዉድመዉ፣ ፍልስጤምን አዳክመዉ፣ ጋዛን አጥፍተዉ፣ሊባኖስን፣ የመንን፣ ኢራንን፣ ደብድበዉ መካከለኛዉ ምሥራቅን አመሰቃቅለዉታል።...more13minPlay
July 07, 2025ዌስት ባንክ ውስጥ በ DW ሰራተኞች ላይ ለደረሰዉ ጥቃት ትችት ቀረበበሁለት የዶይቸ ቬለ (DW) ጋዜጠኞች ላይ በምዕራብ ዮርዳኖስ ዳርቻ ላይ የሰፈሩ እስራኤላዉያን ጥቃት ካደረሱ በኋላ የጀርመን ጋዜጠኞች ማህበር በጉዳዩ ላይ ማብራርያ ጠየቀ። ከዚህ ቀደም ሲል በእስራኤል የሚገኙት የጀርመን አምባሳደር ድርጊቱን ተችተዉታል። የ DW ማሰራጫ ጣብያ ዋና ዳይሬክተር ፒተር ሊምቡርግ በበኩላቸዉ ድግርጊቱን አዉግዘዉታል።...more0minPlay
July 06, 2025ዉይይት፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ የነዳጅ ዘይት ዋጋ መናር፣እጥረትና እስከፊ ጫናዉነዳጅ ዘይት ከመወደዱ በተጨማሪ በየነዳጅ ማደያዉ አለመገኘቱ ወይም እጥረቱ ለብዙዎች ፈተና ሆኗል።የኢትዮጵያ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ እንዳሉት ከዉጪ የሚገባዉ የነዳጅ መጠን አልቀነሰም።ባለሥልጣናቱ ለእጥረቱ «ስግብግብ» እና «ኮንትሮባንድ» ነጋዴዎች ያሏቸዉን ወገኖች ተጠያቂ ያደርጋሉ...more47minPlay
July 06, 2025ሪዮ ዲ ጄኒሮ፤ የብሪክስ አባል ሃገራት የመሪዎች ጉባኤ ሪዮ ዲ ጄኒሮ ብራዚል ውስጥ ዛሬ ተጀመረጉባኤው ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠንካራ የኤኮኖሚ ፖሊሲ ምላሽ መስጠትን ጨምሮ በዋና ዋና የጥምረቱ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።...more0minPlay
July 05, 2025“በትግራይ በኩል ምንም ዓይነት የጦርነት ፍላጎትም ሆነ ዝግጅት የለም” – ህወሓትህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ “በትግራይ በኩል ምንም ዓይነት የጦርነት ፍላጎትም ሆነ ዝግጅት” እንደሌለ አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላቀረቡት ማብራሪያ በሰጠው ምላሽ ህወሓት በኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት ላይ ብርቱ ውንጀላ አቅርቧል። ዐቢይ በምክር ቤቱ ውጊያ “ከተጀመረ ነገር ይበላሻል” ብለው ነበር።...more0minPlay
July 05, 2025ትኩረት በአፍሪቃ፤ የናይጄሪያ የምርጫ ዝግጅት፤ የሩዋንዳና የኮንጎ ስምምነትይህ በታጣቂዎች ላይ ቅሬታን ፈጥሯል ያሉት የፖለቲካ ተንታኙ ይህም የስምምነቱን ተፈጻሚነት አደጋ ላይ እንደሚጥለው ተናግሯል። የኮንጎ መንግሥት በበኩሉ እነዚህ የ ኤም አይ 23 ሚሊሺያዎች ድርጊት በማውገዝ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው አጥብቆ አሳስቧል።...more12minPlay
July 05, 2025የ"ብሩህ ትውልድ" የልዩ ክህሎት ሥልጠና በኢትዮጵያበሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በ28 ማዕከላት ከ800 በላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የክረምት ልዩ የክህሎት ስልጠና ለመስጠት መዘጋጀቱን ብሩህ ትውልድ ድርጅት አስታወቀ። የብሩህ ትውልድ በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች ለሃገራቸው መሰረታዊ ችግሮች መፍትሄ የሚያፈላልጉና ዐዲስ ነገር መፍጠር የሚችሉ ዜጎችን ማፍራት ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል።...more4minPlay
July 05, 2025ብዙዎችን ያስጨነቀው የሙቀት ማዕበልየሰሜኑ ንፍቀ ክበብ የበጋ ወራት በይፋ ከጀመረ አንስቶ በርካታ ሃገራት ለቀናት የዘለቀ ኃይለኛ ሙቀት እያስተናገዱ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ፤ በአሁኑ ጊዜ ምድር በሁሉም ቦታ እጅግ ሞቃትና ለሁሉም በጣም አደገኛ እየሆነች ነው በማለት ሁኔታውን ገልጸዋል።...more4minPlay
July 05, 2025የአውሮፓ ኅብረት የተመ ሰብአዊ መብቶች ምክር ቤትን ተጠቅሞ ጥቃት እንደሚፈጽምባት ኤርትራ ከሰሰችየኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል የአውሮፓ ኅብረት ሀገራቸውን ለመቅጣት የተ.መ. የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤትን እንደ መሣሪያ እንደሚጠቀም ከሰሱ። የማነ ኅብረቱን የወነጀሉት መንግሥታቸው በኤርትራ ተፈጽመዋል የሚባሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ለመመርመር የሚሾሙ ባለሙያ ሥልጣን እንዲያበቃ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ከተደረገ በኋላ ነው።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.