Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
June 30, 2025አትሌት አበባ አረጋዊ ከ13 ዓመታት በኋላ ሜዳሊያ፤ የዓለም ክለቦች ዋንጫ ፍልሚያዎችኢትዮጵያ እንደ ሀገር እና አትሌት አበባ አረጋዊ ከ13 ዓመታት ቆይታ በኋላ የለንደን ኦሎምፒክ በ1500 ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነዋል። በአሜሪካ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የፊፋ የዓለም ክለቦች እግር ኳስ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ተፋላሚ ክለቦችን መለየት ጀምሯል።...more11minPlay
June 30, 2025በደቡብ ወሎ ዞን የወባ በሽታ ስርጭት መጨመሩየደቡብ ወሎ ዞን ለወባ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ጤና ለመታደግ ከ600 ሺ በላይ የአልጋ አጎበር እና ለርጭት የሚያገለግሉ መከላከያ ኬሚካሎች ቢያስፈልጉትም ክልሉም ሆነ የፌዴራል መንግስቱም ባለፉት 3 ዓመታት ምንም አይነት ድጋፍ አላደረገልንም ሲሉ በደቡብ ወሎ ዞን ጤና መመሪያ የወባ መከላከል ፕሮግራም አስተባባሪ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።...more4minPlay
June 30, 2025ሥጋት የፈጠረው የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ማሻሻያረቂቁ፣ ጅርጅቶቹ ከውጭ ወይም በሀገር ውስጥ ካለ የውጭ አካል የገንዘብ ድጋፍ ሲያገኙ በ15 ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቁም ግዴታ ይጥላል። ማሻሻያው በቀረበበት ሁኔታ የሚፀድቅ ከሆነ "ችግር ውስጥ ያለውን የሲቪክ ምህዳር የበለጠ የመዘጋት" ዕጣ ያስከትልበታል፣ በዘርፉ ላይም ተጨባጭ "አደጋ ያንዣብባል" የሚሉ ሥጋቶች ከወዲሁ እየተነሱ ይገኛል።...more4minPlay
June 29, 2025እንወያይ፤ «የሕዝብ ለሕዝብ» የተባለለት ግንኙነት ወዴት ያመራል?በሕዝብ ለሕዝብ ስም እንዲህ አይነት ግንኙነቶች መጀመሩን ብዙዎች እየተቹት ይገኛሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ግንኙነቱ መጀመሩን ያለፈ ቁስልን በማሻር ወደፊት የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር በር ከፋች እንደሆነ የሚገልጹም አሉ።...more46minPlay
June 28, 2025ትኩረት በአፍሪቃ፤ ኤኮዋስ ለሕልዉናዉ እየታገለ ነዉ፤ የኬንያ ተቃዉሞ ሠልፈኞች ፅናትኤኮዋስ እንደ ምዕራባዉያን መንግሥታት ሁሉ «አሸባሪ» የሚላቸዉ በየአባል ሐገራት የሸመቁ ታጣቂዎች የሚያደርሱት ጥቃትም የማሕበሩ ከፍተኛ ፈተና ነዉ።የኤኮዋስ አባል መንግስታት የየአመፀኞቹን ጥያቄ ለማድመጥ፣ሠላማዊ መፍትሔ ለመፈለግ ይሁን ሌላ የብልሆች ሥልት ለመቀየስ ከመሞከር ይልቅ አመፅን በኃይል ለመደፍለቅ ያደረጉት ጥረትም አልተሳካለትም...more0minPlay
June 28, 2025የመብት ጥሰትን የመከላከል ጥረት በደቡባዊ ኢትዮጵያ ክልሎችየኢትዮጵያ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም በዜጎች ላይ የሚከሰቱ የመብት ጥሰቶችን የመከላከልና የማረም ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ ፡፡ተቋሙ ከመልካም አስተዳደር እጦት ጋር ተያይዘው ለሚነሱ አቤቱታዎች በቅንጅት ምላሽ ለመስጠት ያስችለኛል ያለውን የመግባቢያ ሥምምነት ከሦስት ክልላዊ መንግሥታት ጋር በሀዋሳ ተፈራርሟል ፡፡...more4minPlay
June 28, 2025በምያንማር የቀሪ ታጋች ኢትዮጵያዉያን ዕጣ ፈንታ አልታወቀምበምያንማር ከአጋቾች አምልጠው በካምፕ ውስጥ ከነበሩ 751 ኢትዮጵያውያን መካከል የሆኑት የመጨረሻዎቹ 49 ታጋቾች ከትናንትባለፈው ረቡዕ ወደ አገር መግባታቸውን የወላጆች ኮሚቴ አስተባባሪዎች ለዶይቼ ቬለ ገለጹ፡፡...more4minPlay
June 28, 2025ኢራን በእስራኤል ግጭት ለተገደሉ ወታደራዊ መኮንኖች ብሔራዊ ሥርዓተ ቀብር አካሔደችየኑክሌር ሳይንቲስቶች እና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችን ጨምሮ ኢራን ከእስራኤል ባደረገችው ውጊያ የተገደሉ 60 ሰዎች ብሔራዊ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ። በሥርዓተ-ቀብሩ የተሳተፉ ኢራናውያን የሟቾችን ፎቶግራፎች ይዘው፣ መፈክር እያሰሙ የኢራንን ሰንደቅ ዓላማ ሲያውለበልቡ ታይተዋል።...more0minPlay
June 28, 2025ኢትዮጵያን ጨምሮ ግጭት እና አለመረጋጋት በበረታባቸው 39 ሀገሮች ከፍተኛ ድሕነት በፍጥነት እያደገ መሆኑን ዓለም ባንክ አስጠነቀቀዓለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ39 ኢኮኖሚዎች ግጭት እና አለመረጋጋት ከየትኛውም የዓለም ክፍል በባሰ ሁኔታ ድሕነት እና አስከፊ ረሐብ ማባባሱን ይፋ አድርጓል። “ደካማ እና በግጭት የተጎዱ” የተባሉት 39 ኢኮኖሚዎች ከጎርጎሮሳዊው 2020 ወዲህ በዋና ዋና የዕድገት ጠቋሚዎች ወደ ኋላ መቅረታቸውን የባንኩ ትንታኔ አመልክቷል።...more0minPlay
June 27, 2025የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትሩፋትና ተግዳሮቱበኢትዮጵያ በሙሉ አቅጣጫ ስራ ላይ ከዋለ አንድ ዓመት ሊሞላዉ ጥቂት ጊዜ የቀሩት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ውጤት ፈተና ማስከተሉን የምጣኔ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡ የውጪ ምንዛሪን ለገበያው መተውን ጨምሮ በርካታ የማክሮ ኢኮኖሚው ለውጦችን ገቢራዊ ያደረገው ማሻሻያው በተለይም የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን በተፈለገው ፍጥነት ለመቆጣጠር የቀናው አይመስልም።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.