Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
June 26, 2025የስሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ጉባኤ ፍፃሜና ውጤቱየስሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ዋና ጸሃፊ ማርክ ሩተ የኔቶ መሪዎች በሄግ የመከላከያ እቅድ ላይ መስማማታቸውን አስታውቀዋል። በዚህ ዕቅድ መሰረት አገሮች ከጠቅላላ ገቢያቸው 5 ከመቶውን ለመክለካያ ወጭና ኢንቭስትሜንት ያውላሉ። 3.5 ከመቶ ለጦር መሳሪያዎች ወጭ፤ 1.5 ከመቶ ለመከላክያ መሠረተ ልማት ይመድባሉ።...more4minPlay
June 25, 2025«አከራካሪ» የተባሉ አካባቢዎች ችግር በሰላም እንዲፈታ ስለመጠየቁየወልቃይት ነባር ነዋሪዎች በመላው ዓለም በስደት ላይ እንደሚገኙ የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎች፣ እኚህም ወደ ቀደመ ቀያቸው የሚመለሱበት ሁኔታ እንዲመቻች የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እገዛ እንዲያደርጉ ተወያዮቹ መጠየቃቸውን አስተያየት ሰጪው ተናግረዋል፡፡...more4minPlay
June 25, 2025የነዳጅ እጥረት በትግራይ ክልልወደ ትግራይ የሚገባ ነዳጅ በከፍተኛ መጠን መቀነሱን ተከትሎ በክልሉ የእርዳታ ስርጭት ሥራ እየተስተጓጐለ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ። በነዳጅ እጦት ምክንያት ከ150 በላይ እርዳታ እና የሕክምና ግብአት የጫኑ መኪኖች ለቀናት መቆማቸውን የትግራይ ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ ገልጿል።...more5minPlay
June 25, 2025በኢትዮጵያ ፈታኝ ሆኖ የቀጠለው የነዳጅ አቅርቦትና መዘዙኢትዮጵያ ውስጥ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ጨምሮ አሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት በብርቱ መፈተናቸውን እየገለጹ ነው። ማደያዎች ነዳጅን በሕገወጥ እያወጡ ዋጋን ጨምረው መሸጥና ወር እየተገባደደ በመጣ ቁጥር ጭማሪ ይደረጋል በሚል ምርቱን መደበቅ መዘዝ እያስከተለ ነው ተብሏል።...more4minPlay
June 25, 2025በሀገሪቱ የምሥራቅ አካባቢዎች ጉዳት ሊያስከትል የሚችል የዝናብ ሁኔታ ማስጠንቀቂያበሀገሪቱ የምሥራቅ አካባቢዎች በተያዘው የክረምት ወቅት ቀጣይ ወራት የከፋ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል የዝናብ ሁኔታ እንደሚጠበቅ የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት አስታወቀ።...more4minPlay
June 25, 2025የጀርመን ቤተ ክርስቲያን ት/ቤት ለተማሪዎቹ ምገባ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱአቅም ያነሳቸውን ሰዎች ልጆች በነፃ የሚያስተምረው የጀርመን ቤተ ክርስቲያን ት/ቤት ለተማሪዎቹ የተሟላ ምግባ የሚያደርግበትን የገንዘብ ድጋፍ አገኘ። አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ አካባቢ የሚገኘውና ከተመሠረተ 53 ዓመታት ያለፉት ይህ ትምህርት ቤት በአሁኑ ወቅት ብቻ ከመጀመርያ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የደረሱ 690 ተማሪዎችን ያስተምራል።...more4minPlay
June 25, 2025የብር ምንዛሪ ተመን እየላሸቀ ሲሔድ የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ድጎማ አስቀረ-ከዚያስ?የኢትዮጵያ መንግሥት ለነዳጅ ግብይት ያደርግ የነበረውን “ጥቅል ድጎማ” ከግንቦት ወር መጨረሻ ጀምሮ አቁሟል። እርምጃው ኢትዮጵያውያን ቤንዚን እና ናፍጣን የመሳሰሉ የነዳጅ ውጤቶች ሲገዙ የዓለም ገበያ ዋጋን እንዲከፍሉ የሚያደርግ ነው። የድጎማ መቅረት ለመንግሥት ወጪ ፋታ የሚሰጥ ቢሆንም በገበያው ወደ ሸማቾች የሚተላለፍ ጫና ሊያስከትል ይችላል።...more11minPlay
June 24, 2025ትራምፕ፤ በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተኩስ አቁም ተግባራዊ ሆንዋልየዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያወጁት የተኩስ አቁም ስምምነት በመካከለኛዉ ምስራቅ ተደቅኖ የነበረዉን ዉጥረት ወደ መረጋጋት ያመራ ነዉ ሲሉ በርካታ የአረብ ሀገራት ስምምነቱን በደስታ ተቀበሉት።...more0minPlay
June 24, 2025የኔቶ አባል ሐገራት የሁለት ቀናት ጉባኤ ኔዘርላንድ ዉስጥ ተጀመረየሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት የ(ኔቶ) መሪዎች ዛሬ ኔዘርላንድስ ላይ ታሪካዊ የተባለዉን የሁለት ቀናት ጉባኤ ጀመሩ። 32 የዓለም ሃገራት አባላት የሆኑበት የዓለም ትልቁ የደህንነት ድርጅት ለደህንነት ተጨማሪ ወጭ ለማዉጣት ይስማማሉ አልያም ያለስምምነት ይበተናሉ ተብሎ ይጠበቃል።...more0minPlay
June 24, 2025የነዳጅ እጥረት በደቡባዊ ኢትዮጵያ የሸቀጦች ዝዉዉርን እያጎለ ነዉየናፍጣ እና የቢንዚን ምርት እጦት ሥራቸውን አንዳስተጓጎለባቸው ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል ፡፡ ናፍጣ አለማግኘታችን ከፍተኛ ጫና ፈጥሮብናል ያሉት አቶ ያሲን “ የወጪ እና የገቢ ምርቶችን የጫኑ ተሸከርካሪዎች ተገተዋል ፡፡ በወቅቱ ከአገር መውጣትም ሆነ ወደ ማሀል አገር መንቀሳቀስ አልቻሉም...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.