Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
June 27, 2025አንድ ለአንድ፤ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ገነት አየለ ግሩንበርግተወልዳ ያደገችው በምሥራቅ ኢትዮጵያ ሀረር ከተማ ነው። ትምህርቷንም እዚያው ሀረር እና አዲስ አበባ ተማረች። ከዚያም ወደ ጋዜጠኝነቱ ዓለም ገባች። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለዓመታት ሠርታለች። ደራሲም ናት።...more20minPlay
June 27, 2025በዓመት 11ሺህ ያክል ሠዎች “በሕገ ወጥ መልኩ ከሀገር ይወጣሉ” ተባለበየዓመቱ 11ሺህ ህፃናትና ወጣቶች በምዕራብ ጎንደር መተማ በኩል በህገወጥ መንገድ ከሀገር እንደሚወጡ የዞኑ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ። ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት የትግራይና የደቡብ ክልል ወጣቶች እንደሆኑም መምሪያው ገልጧል። አንድ የፖልቲካል ሳይንስና ዓለማቀፍ ግንኙነት ምሁር “ለስደት ገፊና ሳቢ ምክንያቶች አሉ” ይላሉ፡፡...more4minPlay
June 27, 2025ለሦስት ወር የሚሸፍን የእቃዎች መግዣ የውጭ ምንዛሪ ክምችት መኖሩ ተገለፀብሔራዊ ባንክ ለ3 ወር የተጠጋ የሸቀጦች እና የአገልግሎት ገቢ ክፍያ የሚሸፍን የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዳለው ተገለፀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ለ3 ወር የተጠጋ የሸቀጦች እና የአገልግሎት ገቢ ክፍያ ለመሸፍን የሚያስችል ደረጃ ላይ መድረሱን የባንኩ ገዢ ማሞ ምህረቱ ገለፁ።...more4minPlay
June 27, 2025የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር እንደሚወያዩ ገለፁበፕሪቶርያ ስምምነት ጉዳይ፣ በተፈናቃዮች ጉዳይ እና በሌሎች አጀንዳዎች ዙርያ ከጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ጋር እንደሚወያዩ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለፁ። ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ መልሶ ሊያጤን እንደሚገባም ጀነራል ታደሰ ገልፀዋል።...more4minPlay
June 27, 2025« በአንዱ እጄ ውኃ በብብቴ ደግሞ ጫት ይዤ እዞር ነበር»በዓለም ላይ አደንዛዥ እፅ የሚወስዱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት መሠረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሁሉም አደንዛዥ እፆች በተለይ የኮኬይን ተጠቃሚዎች ቁጥር በፍጥነት እያደገ ነው።...more10minPlay
June 26, 2025በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን መመሪያ እየፈቀደልን ለመኖሪያ ቤት ቦታ ካሳ ክፍያ ተከለከልን አሉከ2009 ዓ.ም የካቲት 17 ጀምሮ በአማራ ክልል ያሉ መምህራን ተደራጅተው የቤት መስሪያ ቦታ ሲያገኙ የክልሉ መንግስት ከ21 በላይ ለሚሆኑ መምህራን የቦታ ካሳ ክፍያ ፈጽመው ከ3ኛ ወገን ነጻ የሆነን ቦታ አስረክቧል።ሆኖም ደሴ ባህር ዳር ጎንደር ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደርና ምእራብ ጎጃም ያሉ መምህራን የመሬት ካሳ ክፍያ አልተሰጠንም ያላሉ፡፡...more4minPlay
June 26, 2025ኢትዮጵያዉያኑ ለአዲሱ የደቡብ ኮርያ ፕሬዚዳንት የደስታ መግለጫ አስተላለፉ -መልዕክትም አላቸዉበደቡብ ኮርያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለአዲሱ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከደቡብ ኮሪያ ነፃ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታን የሰለጠነ ህዝባዊ ተሳትፎ ነፃና ገለልተኛ ተቋማትን የሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅን እንዲሁ ሙሉ ዜጎች ላይ ያተኮረ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዝርጋታ ላይ በሰፊ ልምድ እንድትቀስም እኛ ዜጎቿ እንፈልጋለን።...more15minPlay
June 26, 2025ኢትዮጵያና ኤርትራ በአዋሳኝ ድንበር አካባቢዎች፥ የነዳጅ እጥረትየኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት አስቸጋሪ በመሰለበት በአሁኑ ወቅት፥ በኤርትራ እና በትግራይ ክልል አዋሳኝ ድንበር አካባቢ ነዋሪዎች ከሰሞኑ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማድረጋቸው ተነግሯል ። በኢትዮጵያ የነዳጅ እጥረቱ ነዋሪዎችን እያማረረ መሆኑ እየተነገረ ነው ። የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ላይ የተሰጡ አስተያየቶች ስብስብ፤ ሙሉውን ማድመጥ ይቻላል ።...more9minPlay
June 26, 2025«የትራንስፖርት ዘርፍ ውስብስብ ችግር ያለበት ነው» የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትርመንግሥት ይህንን መሠረታዊ ችግር ለመቅረፍ ጥረት ማድረጉን የገለፁት የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ በዚህም ያልተገባ ኬላ ወይም የፍተሻ ጣቢያ እንዲቀር ቢደረግም በየጥቂት ኪሎ ሜትር ርቀት አሽከርካሪን ሁለት ሁለት ሺህ ብር የሚጠይቁ ቀማኞች መኖራቸውንና ችግሩ መልኩን ቀይሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።...more4minPlay
June 26, 2025ጀርመን ውስጥ በሞያቸው የሚፈለጉ አፍሪቃውያን ለምን ቪዛ አያገኙም?ወደ ጀርመን ፍልሰት ከቆመ ከዛሬ 15 ዓመት በኋላ የሠራተኛ ኃይል ቁጥር እጅግ እያሽቆለቆለ ይሄዳል። ይህም በሀገሪቱ የኤኮኖሚ እድገትና ተፎካካሪነት ላይ አሉታዊ መዘዞችን ማስከተሉ አይቀርም። የፌደራል የሠራተኞች ቅጥር መስሪያ ቤት በቅርቡ እንዳለው በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በህክምና በቴክኒክና በትምሕርት ዘርፍ 646 ሺህ ክፍት የስራ ቦታዎች አሉ ።...more5minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.