Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
June 17, 2025የኦሞ ወንዝ ተፈናቃዮች የዘላቂ መፍትሄ ጥያቄበደቡብ ኢትዮጵያ ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በኦሞ ወንዝ ሙላትና በቱርካና ሐይቅ መጨመር የተፈናቀሉ ከ79 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መንግሥት ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠየቁ። ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ባለመበጀቱ ለ3ተኛ ጊዜ መፈናቀላቸውን ለዶቼ ቬለ የተናገሩት ነዋሪዎቹ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም አሁንም በውኃ ተውጠው እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።...more4minPlay
June 16, 2025የሰኔ 9 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባበአውሮጳ እግር ኳስ ግጥሚያ፦ የጀርመን ከ21 ዐመት በታች ተጨዋቾች ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ። ሊቨርፑል በከፍተኛ ክፍያ ጀርመናዊው አማካይ ፍሎሪያን ቪርትስን ሊያስመጣ ተስማምቷል ። ቅዳሜ የግብጹ አል አህሊ ከዩናይትድ ስቴትሱ ኢንተር ሚያሚ ጋ ያለምንም ግብ ተለያይቷል ። የ37 ዓመቱ አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ የፈየደው ነገር አልነበረም ።...more10minPlay
June 16, 2025የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እና የጦር የሠራዊቱ ሚናየታላቁ ህዳሴ ግድብ አሁን ያለበትን ደረጃ ለማድረስ ሰራዊቱ ከፍተኛ ገድል መፈጸሙን የኢፌዲሪ ጦር ሐይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተናገሩ፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ይሄንን የተናገሩት ትናንት የምዕራብ ዕዝ 404ኛ ህዳሴ ኮር 3ኛ ዓመት ምስረታ በዓሉን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ባከበረበት ወቅት ነው፡፡...more4minPlay
June 16, 2025በብድር አቅርቦት እጥረት የተፈተነው የቤት ልማት ዘርፍቤት ገንቢ ድርጅቶች ከግል ባንኮች በቂ ብድር እያገኙ አለመሆኑ መሠረታዊ ችግር እንደሆነበት የኢትዮጵያ የሪል እስቴት አልሚዎች ማሕበር አስታወቀ። በዚህ ወቅት በግል ዘርፉ ያለው የቤት ግንባታ እና ግብይት መቀዛቀዝ የታየበት ሲሆን የቤቶች ዋጋ መናር ለዚህ ምክንያት መሆኑን ማሕበሩ ገልጿል።...more4minPlay
June 16, 2025«በትግራይ ከመቶ 50 ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል» የትግራይ አስተዳደርበትግራይ 50 ከመቶ ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነው እንዳለ የክልሉ አስተዳደር ገለፀ። ድህነት፣ መፈናቀል እና ሌሎች ሁኔታዎች ለዚህ ምክንያቶች ናቸው ተብለዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ህፃናት በክልሉ እና ከክልሉ ውጭ በልመና ተሰማርተዋል፣ ለጉልበት ብዝበዛ እየተዳረጉ መሆኑንም ተገልጿል። ዛሬ የአፍሪካ ህፃናት ቀን እየተዘከረ ነው።...more3minPlay
June 16, 2025አሳሳቢው የእስራኤልና ኢራን ግጭት-ዉዝግብእስራኤል በኢራን ላይ ያደርሰችው ጥቃትና የኢራን ወታደራዊ የአጸፋ መልስ አካባቢውን ወደ ሌላ አስከፊ ጦርነት እንዳያስገባው እና የዓለም ሰላም እና ምጣኔ ሀብትም እንድይናጋ አስግቷል። መንግስታትና አለማቀፍ ድርጅቶችም ዋና አጀንዳቸው አድርገው እየተወያዩበት ነዉ። የሰባቱ ባለፀጋ አገር መሪዎች ጉባኤ ዋና ርዕስም ነዉ።...more4minPlay
June 16, 2025የእስራኤል ኢራን ግጭት እና የደቀነው ብርቱ ስጋትያ የተፈራው ፤ ያ እንዳይመጣ የተሰጋው ቀንና ሰዓት ደረሰ። ለአራት አስርት ዓመታት የዘለቀው የከፋ ጠላትነት ገነፈለ ፤ በመጨረሻም እስራኤል ክብሪቱን ለኮሰች ፤ የኢራን እስራኤል የአየር ላይ ጦርነት የእሳት ኳስ እያወራወረ አራተኛውን ቀን አስቆጠረ ፤ ሀገራቱ በታሪካቸው አይተው ያማያውቁትን ውድመት እና የሰብአዊ ቀውስ እያስተናገዱ ነው ።...more14minPlay
June 15, 2025በኢትዮጵያ አሳሳቢው የተፈናቃዮች ይዞታ ተስፋና መፍትሄውየኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል የተባለው ድርጅት በዓመታዊ ዘገባው በዓለም ላይ የተዘነጋ የመፈናቀል ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ ካላቸው መካከል ኢትዮጵያን ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። በግጭቶችም ይሁን በሌሎች ተፈጥሮአዊ አደጋዎች በኢትዮጵያ ከመኖሪያቸው ከተፈናቀሉ ሰዎች መካከል የምግብ አቅርቦት እንደተቋረጠባቸው በምሬት የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው።...more45minPlay
June 15, 2025የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያን ጨምሮ 36 ሀገራትን የጉዞ እገዳ የተጣለባቸው ዝርዝር ውስጥ የማካተት ዕቅድ አለው ተባለየፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ጅቡቲን ጨምሮ 36 ሀገራትን የጉዞ እገዳ ከተጣለባቸው ዝርዝር ውስጥ የማካተት ዕቅድ እንዳለው ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። እገዳ ይጣልባቸዋል ከተባሉት ውስጥ 25 የአፍሪካ ሀገራት ይገኙበታል። ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ኤርትራን ጨምሮ የ12 ሀገራት ዜጎች አሜሪካ ከመግባት ታግደዋል።...more0minPlay
June 15, 2025እስራኤል እና ኢራን አንዳቸው በሌላቸው ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ጨመረበሚሳይሎች እና ድሮኖች ጭምር የሚደረገው የእስራኤል እና የኢራን ውጊያ ሦስተኛ ቀኑን ሲይዝ አንዳቸው በሌላቸው ላይ ብርቱ ጥቃት ለመፈጸም እየዛቱ ናቸው።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.