Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
June 12, 2025የአፍሪቃ ቀንድ ሽኩቻ እና የኢትዮጵያ አቋም አንድምታኢትዮጵያ ወደ ባህር እንዳትወጣ አበክረው የሚሠሩ አካላት አሉ ሲሉ የኢፌድሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አመለከቱ ። አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የፖለቲካ ተንታኝ ግን በአፍሪቃ ቀንድ ሌላ ዙር ግጭት እንዳይከሰት መንግስታቱ አበክረው መሥራት ጠበቅባቸዋል ብለዋል ።...more0minPlay
June 12, 2025ትግራይ ክልል የእርስበርስ ግጭት እንዳይከሰት ሥጋት መፈጠሩን የሲቪክ ተቋማት ገለጹበትግራይ ክልል 'አንዣበበ' ያሉት የእርስበርስ ግጭት ስጋት እንዲቀረፍ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ሊሠራ ይገባል ሲሉ ሁለት ሲቪክ ተቋማት ባወጡት መግለጫ ጥሪ አቀረቡ። ሥጋታቸውን የገለጡት ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች እና የዴሞክራሲና ማኅበራዊ ፍትህ ድምፅ የተባሉ ሁለት ሲቪክ ተቋማት ናቸው ።...more0minPlay
June 12, 2025የፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ የሆነው ኮከስ ጥሪስድስት የፓለቲካ ድርጅቶችን ያሰባሰበው ኮከስ፦ «ለአገር አለመረጋጋት፣ ለእርስ በርስ ግጭትና ጦርነት፣ ለፖለቲካዊ ትርምስ፣ ለኢኮኖሚታዊ ድቀትና ማኅበራዊ ቀውስ መባባስ» ምክንያት ይሆናሉ በሚል የጠቀሳቸው አካሄዶች እንዲገቱ ጥሪ አቀረበ ። መግለጫውን ያወጡት የኮከስ አባል የፖለቲካ ድርጅቶች ኢሕአፓ፣ ኦፌኮ ኅብር፣ ዎብን፣ ኦነግ እና መድረክ ናቸው።...more0minPlay
June 12, 2025ታሪካዊው የያዓ መሠራ መስጊድሼህ አልፈኪ ከናይጀርያ ተነስተው በሱዳን በኩል ወደ ኢትጵያ መጥተው ያዓ መሰራ መስጂን ከመገንባታቸው በፊት በአሶሳ ለተወሰኑ ዓመታት መቆየቸውን፣ ከዚም ወደዳምቢ ዶሎ፣ጂማ፣ ትግራይና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሀይማኖት ትምህርት መስጠታቸውን ከ30 ዓመት በላይ በያዓ መሠራ መስጅድ በማገልገል ላይ የሚገኙ ሼህ መሐመድ ሳሲ ተናግረዋል፡፡...more0minPlay
June 11, 2025ከኢትዮጵያ የ2018 አጠቃላይ በጀት 24 በመቶ ገደማ ለዕዳ ክፍያ ተመደበከ2018 የኢትዮጵያ 1.93 ትሪሊዮን ብር በጀት 463 ቢሊዮን ብር ለዕዳ ክፍያ ተመድቧል። የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት “የተሟላ” የሚሉት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ ያተኮረው በጀት ለአዳዲስ ፕሮጀክቶች ገንዘብ አልመደበም። በቀጣዩ ዓመት 1.2 ትሪሊዮን ብር ገቢ ከሀገር ውስጥ ለመሰብሰብ አዳዲስ የታክስ ፖሊሲዎች ሥራ ላይ እንደሚያውል መንግሥት አስታውቋል።...more11minPlay
June 11, 2025ቲክቶክን አብዝቶ መጠቀም የማስታወስ ችሎታን እንደሚቀንስ ያውቃሉ?በአሁኑ ጊዜ እንደ ቲክ ቶክ ያሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሰዎችን ሀሳብ በመበታተን ይጠቀሳሉ።በዚህ የተነሳ በርካታ ሰዎች ከጥቂት ደቂቃዎች በላይ በአንድ ነገር ላይ ማተኮር እየተቸገሩ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ።ይህ እንዴት ይከሰታል? እንደ ቲክ ቶክ ያሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በአእምሯችን ላይ ምን ተፅዕኖስ ያሳድራሉ?...more10minPlay
June 11, 2025በደቡብ ወሎ የተፈናቃዮች መጠለያ የህክምና አገልግሎት ማጣትበአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በሐይቅ ጃሪ የስደተኞች ጣቢያ የሚገኙ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ባለፉት ስድስት ቀናት ምንም አይነት ህክምና ባለማገኘታቸዉ ህሙማን በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸዉ ተነገረ። ባለፉት አምስት ዓመታት በዮኒሴፍ አማካኝነት በመጠለያ አገልግሎት ይሰጥ የነበረዉ ክሊኒክም በበጀት እጥረት ምክንያት ሥራዉን አቋርጦል።...more4minPlay
June 11, 2025አዲሱ የአሜሪካ ረቂቅ የሐዋላ ሕግ የፈጠረው ስጋትየዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ያልሆኑ ነዋሪዎች፣ ወደ ሀገራቸው ሐዋላ ሲልኩ የ3.5 በመቶ ታክስ እንዲከፍሉ የተዘጋጀው ረቂቅ ሕግ፣ ለተጨማሪ ወጪ የሚዳርግና አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ከአሜሪካ ሐዋላ የሚልኩ አስተያየት ሰጪዎች፣ ረቂቅ ሕጉ ለተደራራቢ ወጪ የሚደረጋቸው መሆኑ፣ ስጋት አሳድሮባቸዋል።...more4minPlay
June 11, 2025የኢትዮጵያ ኢንሳይደር መገናኛ ዘዴ መሥራችና ዋና አዘጋጅ እስርበጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የዋስትና መብት ላይ ፖሊስ ለሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ በማለቱ ለነገ ጠዋት ተቀጠረ። በጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የዋስትና መብት ላይ ፖሊስ ይግባኝ በማለቱ ተጠርጣሪው ዛሬ ከቀትር በኋላ በአዲስ አበባ ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቧል።...more4minPlay
June 11, 2025የኦነግ ዋና ቢሮ መከፈትአዲስ አበባ ጉሌሌ የሚገኘው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ዋና ቢሮ ከአምስት ዓመታት በኋላ መከፈቱን ፓርቲው አስታወቀ። የቢሮው መከፈት ፓርቲውን በፖለቲካ እንቅስቃሴ ከማገዙም አልፎ ለፖለቲካ አውድ አመቺ መደላድል ለመፍጠር አንድ እርምጃ ነውም ተብሏል።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.