Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.
May 14, 2025የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጉብኝት፣ የአረቦች ደስታና የአሜሪካ-አረቦች ሥምምነትየዩናይትድ ስቴትስና የሶሪያ መሪዎች ሲነጋገሩ ከ25 ዓመታት ወዲሕ የትራምፕና የአል ሻራዕ የመጀመሪያዉ ነዉ።ትራምፕ ፖለቲካ-ዲፕሎማሲን ከንግድ-ምጣኔ ሐብት በቀየጠዉ ጉብኝታቸዉ ለሳዑዲ አረቢያ የ142 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ለመሸጥ ተስማምተዋል።ሳዑዲ አረቢያ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ 600 ቢሊዮን ዶላር ሥራ ላይ ታዉላላች...more5minPlay
May 14, 2025አሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ከዛሬ ጀምሮ በከፍተኛ መጠን ቀነሱአሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ከዛሬ ጀምሮ ለ90 ቀናት በከፍተኛ መጠን ቀንሰዋል። ሁለቱ የንግድ ከባድ ሚዛን ተፋላሚዎች ታሪፍ የቀነሱት ከጥቂት ቀናት ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው በተስማሙት መሠረት ነው። ዶናልድ ትራምፕ በታሪፍ የጀመሩት የንግድ ጦርነት የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን እንደሚያቀዛቅዝ አስግቶ ነበር።...more10minPlay
May 14, 2025የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ለምን ይሰበስባሉ?በምንኖርበት የበይነመረብ ዓለም ጎግል ላይ በየቀኑ 8.5 ቢሊዮን የመረጃ ፍለጋዎች ይካሄዳሉ።በአሁኑ ወቅት ለብዙዎች የህይወት አንድ አካል በሆኑት የተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን እና በላፕቶፕዎቻችን ላይ በየቀኑ የምንጠቀማቸው ብዙዎቹ አገልግሎቶች ነፃ ናቸው።ነገር ግን በሌላ መንገድ የግል መረጃዎቻችንን በመስጠት ለኩባንያዎቹ ዋጋ እንከፍላለን።...more0minPlay
May 13, 2025አዲሱ የጀርመን የውጭ የፖለቲካ መርህና ሜርስከአትላንቲክ ወዲያ ማዶ ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚሹት ሜርስ ዶናልድ ትራምፕ የሚመሯት ዩናይትድ ስቴትስ ለሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ወታደራዊ እርዳታ መስጠት መቀጠሏን ይጠራጠራሉ። ከአሜሪካን ነጻ መውጣት መቻል አለብን ያሉት ሜርስ የአውሮጳ ሀገራት የመከላከያ ፖሊሲ ትብብር እንዲመሰርቱ እየጣሩ ነው።...more12minPlay
May 13, 2025ወደ ትግራይ የሚጓዙ የዉጪ መንገደኞች የገጠማቸዉ ክልከላየትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በትላንትናው ዕለት ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓመተምህረት፥ ለኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ቱሪዝም ሚኒስቴር የፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ወደ ትግራይ ለጉብኝት የሚጓዙ ቱሪስቶች ጨምሮ የተለያዩ ስራዎች ያሏቸው የውጭ ዜጎች ወደ ክልሉ እንዳያመሩ በኤርፖርቶች ክልከላ እየተደረገባቸው መሆኑ ያመለክታል።...more4minPlay
May 13, 2025ከኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች አንዳዶቹ ሲያድሙ ሌሎቹ አላደሙምከዛሬ ጀምሮ ከድንገተኛ፣ ከጽኑ ሕሙማን፣ ከጨቅላ ሕፃናት እና ከማዋለጃ ክፍል አገልግሎቶች በስተቀር ሥራ የማቆም አድማ የጀመሩ የጤና ባለሙያዎች መኖራቸውን በተለያየ የሀገሪቱ ክፍል ካነጋገርናቸው ባለሙያዎች መካከል አንዳንዶቹ ገልፀዋል።...more4minPlay
May 13, 2025የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የመካከለኛዉ ምሥራቅ ጉብኝትትራምፕ ከሳዑዲ አረቢያ በተጨማሪ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችንና ቀጠርን ይጎበኛሉ።የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት ዛሬ ሪያድ ሲገቡ ልዩ አቀባባል ተደርጎላቸዋል።ቀጠር ደግሞ «የሠማይ ላይ ቤተ-መንግሥት» የተባለ ልዩ አዉሮፕላን ለትራምፕ ሠጥታለች...more6minPlay
May 13, 2025የድጋፍ መቀዛቀዝ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ላይ ያስከተለው ሥጋትፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ እንዲያቆም ያሳለፉት ውሳኔ በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኙ ክልሎች የኤችአይቪ ሥርጭትን ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶችን አደናቅፏል። ውሳኔው የኤችአይቪ መድሐኒት በነጻ የሚቀርብላቸው ሕሙማንን ጭምር ሥጋት ላይ የጣለ ነው።...more10minPlay
May 13, 2025በጋምቤላ አምስት ስደተኞች ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን ክልሉ ፖሊስ አስታወቀየጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ አምስት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል፡፡የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡጉላ ኡጁሉ በኢታንግ ልዩ ወረዳ ውስጥ ሞተዉ የተገኙ ስደተኞችን ጉዳይ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸው የድርጊቱ ፈጻሚዎችን በመለየት ለህግ ለማቅረብ ከፌደራል ተቋማት በጋራ ጉዳዩ እየተጣራ ነው ብሏል...more4minPlay
May 12, 2025የመጀመርያዉ ነጭ ደቡብ አፍሪቃ ቡድን በትራምፕ የስደተኞች እቅድ መሰረት ወደ አሜሪካ ተጓዙየትራምፕ አስተዳደር ይፋ ባደረገዉ ፕሮግራም አማካኝነት አሜሪካ ዉስጥ የጥገኝነት መብት የተሰጣቸው ነጭ ደቡብ አፍሪቃውያን የመጀመሪያ ቡድን ደቡብ አፍሪቃን መልቀቁ ተሰማ። የደቡብ አፍሪቃ የትራንስፖርት ክፍል ቃል አቀባይን ጠቅሶ አሶሽየትድ ፕሬስ እንደዘገበዉ፤ 49 የደቡብ አፍሪቃ መንገደኞች የይለፍ ፈቃድ ተሰቷቸዉ እሁድ ምሽት ተሳፍረዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,914 episodes available.