Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,913 episodes available.
May 17, 2025«ከቄለም ወለጋ ዞን ከ45ሺ በላይ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል» የዞኑ ንግድ ጽ/ቤትከፍተኛ የቡና ምርት ከሚገኝባቸው የኦሮሚያ ዞኖች መካከል አንዱ የሆነው የቄለም ወለጋ ዞን በዚህ ዓመት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ከቀረበው ቡና ከፍተኛ ገቢ ማስገኘቱን የቡና አቅራያዎችና አርሶ አደሮች ተናግረዋል፡፡ የዞኑ ንግድ ቢሮ እንዳለው ገቢው ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 30 በመቶ ብልጫ አለው፡፡...more4minPlay
May 17, 2025የእስራኤል ጦር ሐማስ ታጋቾችን እንዲለቅ ለማስገደድ በጋዛ ሠርጥ ከፍተኛ ወታደራዊ ዘመቻ መክፈቱን አስታወቀየእስራኤል ጦር ሐማስ ታጋቾችን እንዲለቅ ለማስገደድ በጋዛ ሠርጥ ከፍተኛ ወታደራዊ ዘመቻ መክፈቱን አስታወቀ። በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር እንዳለው ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በእስራኤል ጥቃት በጋዛ ሠርጥ 153 ሰዎች ተገድለዋል።...more0minPlay
May 17, 2025ፑቲን እና ዜሌንስኪ ፊት ለፊት እንዲገናኙ ሩሲያ እና ዩክሬን ሥምምነት ላይ መድረስ እንዳለባቸው ክሬምሊን ቅድመ-ሁኔታ አስቀመጠየሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የዩክሬን አቻቸው ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ፊት ለፊት ሊገናኙ የሚችሉት ሁለቱ ሀገራት ሥምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ብቻ እንደሆነ ክሬምሊን አስታወቀ። የሁለቱ ሀገራት ተደራዳሪዎች በቱርክ በተገናኙ በማግሥቱ ሩሲያ በሰሜናዊ ዩክሬን በምትገኘው ሱሚ በድሮን በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች ተገድለዋል።...more0minPlay
May 16, 202531 ዓመታት በዶክተርነት አገልግለው የሚከፈላቸው ከ100 ዶላር ያነሰ ነው፥ ሶማሊላንድ 4,000 ዶላር ትከፍላለች ብለዋል፦ ዶ/ር ፍስሃከ7 ዓመታት ትምህርት በኋላ በዶክተር ማእረግ ተመርቀው ለ31 ዓመታት አገልግለው በኢትዮጵያ የወር ደመወዛቸው 14 ሺህ ብር ብቻ መሆኑን ጠቅሰዋል ። ዐለም አቀፍ ዕውቅና ያልተሰጣት ሶማሊላንድ እንኳን እስከ አራት ሺህ ዶላር እንደምትከፍልም ገልጠዋል፤ ዶክተር ፍሥሃ አሸብር ። የአንድ ለአንድ የሳምንቱ እንግዳ ።...more15minPlay
May 16, 2025«እኛ ላይ የደረሰው ነገር የሚመጣው የጤና ባለሙያ ትውልድ ላይ ቀንበሩ እንዲያርፍ አንፈልግም» ወጣት ሀኪምበኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች የሚነሳው የደሞዝ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ እንደቀጠለ ነው። በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ያነጋገርናቸው ወጣት የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ፤ ጉዳያቸው መፍትሔ እስካላገኘ ድረስ ጥያቄያቸው ይቀጥላል። የሕክምና ተማሪዎችስ የወደፊት እጣ ፈንታ ምን ይሆን?...more10minPlay
May 16, 2025የቀጠለው የጤና ባለሞያዎች ጥያቄና የጤና ሚኒስቴር ምላሽሰሞኑን በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፊል ያሉትን የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ያሉት የጤና ባለሞያዎች ያነሷቸው የደሞዝ፣ የጥቅማ ጥቅም እና ምቹ የሥራ ሁኔታ ጥያቄዎች ምላሽ ካላገኙ ሙሉ አድማ እንደሚያደርጉ አስጠነቀቁ ።...more4minPlay
May 16, 2025ግቢ ልቀቁ የተባሉት ኢንተርን ሀኪሞች እና ሬዚደንቶችበሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኢንተርን ሀኪሞች እና ሬዚደንቶች የኮሌጁን ቅጥር ግቢ ለቀው መውጣታቸውን ገለጹ ። ባለሙያዎቹ ግቢውን ለቀው የወጡት ኮሌጁ በተመደቡበት የሥራ መስክ ካልተገኙ በ12 ሠዓት ውስጥ ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ ያስቀመጠውን የሰዓታት ገደብ ተከትሎ ነው ።...more4minPlay
May 16, 2025ሕወሓት በምርጫ ቦርድ መሰረዙ ሥጋት ፈጥሯል፦ የነዋሪዎች አስተያየትየኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን መሰረዙን ፓርቲው ለተለያዩ ተቋማት ባሰራጨው ደብዳቤ ኮንኖታል። ችግሩን ለመፍታት አፍሪቃ ሕብረት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራም ህወሓት በደብዳቤው ጥሪ አቅርቧል።...more4minPlay
May 16, 2025የፕሬዚደንት ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝትየዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ የሦስት አገራት ጉብኝታቸውን ዛሬ አጠናቅቀዋል ። ሣዑዲ ዓረቢያ፣ ካታር እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶችን የጎበኙት ፕሬዚደንቱ በዋናነት በኤኮኖሚ እና ዴፕሎማሲያቂ ጉዳዮች ላይ አተኩረዋል ።ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፦ በዚህ ጉዟቸው እሥራኤልን የዘለሉበትስ ምክንያቱ ምን ይሆን?...more4minPlay
May 15, 2025ህወሓት ለምርጫ ቦርድ ውሳኔ የሰጠው መልስና የፓርቲው መታገድ በፖለቲካ ተንታኝ እይታህወሓት ዛሬ ባሰራጨው ደብዳቤ የፕሪቶርያው ውል አፈራራሚዎች በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠሩ ጥሪ አቅርቧል። የሕግ ምሁሩ እና የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ሙስጠፋ ዓብዱ በህወሓት እና ፌደራል መንግስት መካከል ያሉ ልዩነቶች ወደግጭት እንዳይሸጋገሩ የፕሪቶርያውን ውል ያፈራረሙ አካላት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጭምር ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ብለዋል።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,913 episodes available.